TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስደሳች መልዕክት📌ቋንቋን ማወቅ ምንኛ መታደል ነው። ከአንድ በላይ ቋንቋን መቻል አዕምሮን ከማስፋት በተጨማሪ ከሰዎች ጋር ያለንን መስተጋብር ያሰፋዋል።
.
.
TIKVAH-EDU #በመጀመሪያው ዙር #አፋን ኦሮሞ እና #ትግርኛን ያስተምራል። በመፅሀፍት በመታገዝ እና ቋንቋውን በሚያቁት የቻናላችን ቤተሰቦች አማካኝነት ነው ትምህርቱ የሚሰጠው።
.
.
በቅድሚያ በሀገራችን ብዙ ሚሊዮን ተናጋሪ ያለውን #የአፋን ኦሮሞ መማማር እንጀምራለን።
.
.
የሚያውቁትን ቋንቋዎች ለማስተማር #ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች በመጡ ቁጥር ብዙ ቋንቋዎችን እንማራለን።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው!
.
.
እኛ ኢትዮጵያዊያን ባለማወቅ ብዙ ተጎድተናል። በሀገራች የሚነገሩ ብዙ ቋንቋዎች እያሉ ቀድመን የለመድነው የባዕድ ሀገር ቋንቋ ነው።
.
.
QAANQEE GADAA
ቃንቄ ገዳ
ኦሮሚኛ እንማር!

እገዛ ለማድረግ ሀሳብ ለማቅረብ የምትፈልጉ 0919 74 36 30 በማንኛውም ሰዓት መደወል ትችላላችሁ።

https://telegram.me/Tikvahethedu - ተቀላቀሉ
#update የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አማርኛና #አፋን_ኦሮሞን በመንግስት ትምህርት ቤቶች አማራጭ የትምህርት መስጫ ቋንቋ አድርጎ ለመጠቀም መወሰኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ታቦር ገ/መድህን ገልፀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን!!

ለበርካታ ወራት ተቋርጦ የነበረው የTIKVAH-ETH የቋንቋ ትምህርት ከነሃሴ 1 ጀምሮ ይቀጥላል!!

#አፋን_ኦሮሞ
#ትግርኛ
#ግዕዝ.... በቀጣይ የሚካተቱት ቋንቋዎች እንደተጠበቁ ናቸው። ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል!

ኢትዮጵያን መውደድ ማለት~ቋንቋዋን፣ ባህሏን፣ ህዝቦችን መውደድ ነው!!

@Tikvahethedu በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEWA_-Jt2zIM5COJqw
#Google

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል #አፋን_ኦሮሞ እና #ትግርኛ ጨምሮ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚናገራቸውን 24 አዳዲስ ቋንቋዎች በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝሩ ውስጥ አካቷቸዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አስሩ ቋንቋዎች በአፍሪካ የሚነገሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ፣ ትዊ፣ ባምባራ፣ ክሪዎ፣ ሉጋንዳ ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ወደ 37 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ሲሆን ከ8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች ትግርኛን ይናገራሉ።

" ለዓመታት ጉግል መተርጎሚያ የቋንቋ ልዩነቶችን በማጥበብ በመላው ዓለም የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለማገናኘት ረድቷል " ሲል የአሜሪካው ኩባንያ ገልጿል።

አክሎም አሁን ቋንቋቸው በአብዛኛው ቴክኖሎጂ ውክልና ያልተሰጣቸው ሰዎችን መርዳት ይፈልጋል ብሏል።

አሁን የተካተቱትን ቋንቋዎች ጨምሮ በጉግል ተርጓሚ የተካተቱ አጠቃላይ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 133 ደርሷል።

አዲሶቹ የተካተቱት ቋንቋዎች የቴክኖሎጂ ምዕራፍን እንደሚወክሉ ገልጾም ምሳሌ ሳይኖር የሚተረጉም የማሽን መማሪያ ሞዴል እንደሚጠቀሙ አስፍሯል።

ይህ ኮምፒውተርን ለማሰልጠንና ትርጉሞቹን በማሰባሰብ የመረጃ ቋቱን ለማካበት የሚያገለግሉ በርካታ ሰዎች ለሌሏቸው ቋንቋዎች ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ብሏል።

ነገር ግን ኩባንያው ቴክኖሎጂው ፍጹም እንዳልሆነ አምኗል።

https://telegra.ph/Google-05-12-3

#BBC/#Google

@tikvahethiopia