TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Forwarded from One pack for one child
የማይቀርበት የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ የሙዚቃ ድግስ እሁድ ነሃሴ 26 በጌትፋም ሆቴል ይደረጋል
13,000 ሺህ ህፃናትን ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ በማገዝ እየተዝናኑ ትውልድ ያስተምሩ!! መግቢያ: 12 ደብተር - 2 እስክርቢቶ - 2 እርሳስ - 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ
#onepackforonechild #onecanreallymakeadifference #music #concert #charity
@onepackforonechild
አንድ እሽግ 12 ደብተር፣ 2 እስክሪብቶ፣ 2 እርሳስ፣ 2 ላጲስ ፣ 2 መቅረጫን የሚያካትት ሲሆን ቤተሰባችን በየዓመቱ በእርስ በእርስ ትውውቅ፣ በቤተሰባዊነት፣ በጓደኝነትና በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚፈጠሩ ትስስሮች በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩ እሽጎችን እየሰበሰበ በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለተቸገሩ ህጻናት እያደረሰ ይገኛል፡ እነሆ ዘንድሮ 8ኛ አመቱን ሲያከብር ለ 13,000 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ተነስተናልና እናንተም ከጎናችን በመሆን እሁድ ነሃሴ 26 በ Getfam Hotel ተገኝተው አስደሳች የክረምት ጊዜን ከቤተሰባችን ጋር እንድታሳልፉ በአክብሮት እንጋብዛለን

#onepackforonechild #summerfun #gooddead #onecanreallymakeadifference
እሁድን በበጎ ተግባር!

#አዲስ_አበባ

💫የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ የሙዚቃ ድግስ ነገ እሁድ ነሃሴ 26 በጌትፋም ሆቴል ይደረጋል። መግቢያ: 12 ደብተር - 2 እስክርቢቶ - 2 እርሳስ - 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ - የTIKVAH-ETH የአ/አ ቤተሰቦች እንዳትቀሩ! #onepackforonechild

💫Rotaract Ethiopia በጎ ስራ ላይ የተሰማራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ለአዲሱ አመት #አልባሳት እያሰባሰበ ነው እናተም ተሳተፉ ያላችሁበት መጥተው ይወስዳሉ ደውሉላቸው Rotaract club of Atrons President Yeabsera --- +251922175164. (Or Natnael -@Natysf +251923594536, Sofonias - @SophoDarik +251 92 453 9140

#ወላይታ_ሶዶ

💫"አለን ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ" ላለፉት ሁለት ቀናት ለ800 ተማሪዎች ለትምህርት የሚሆናቸውን ቁሳቁስ እያሰባሰበ ነው። በተጨማሪ የደም ልገሳ እየተደረገ ይገኛል። ነገም ለ3ኛ ቀን ይቀጥላል። ወላይታ ሶዶ ያላችሁ የTIKVAH-ETH ተከታዮችም እሁዳችሁን ከነሱ ጋር ማሳለፍ ትችላላችሁ። ስልክ +251913776084፣ 0926172318

#ሻሸመኔ

💫የሻሸመኔ ወጣቶች ነገ የይደግ በጎ አድራጎት ማእከልን ይጎበኛሉ እንዲሁም ግቢውን ያፀዳሉ። የሻሸመኔ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ኑ እሁድን በመልካም ስራ እናሳልፍ ከሰአት 8:00 ሰአት ላይ CDI እንገናኝ ብለዋችኃል!! ስልክ፦0926940304

#ለኩ
💫በለኩ ከተማ የሚገኙ "እኔም ለወገን" የበጎ አድራጎት ማህበር አባላት የሻይ ቡና ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። የለኩ ቤተሰቦቻችን እሁድን አብራችሁ!0986241726

💫"ነገ በለኩ ፉርቃን የአበባ እና የችግኝ መተከል ስነ ስርአት ስለሚኖረን የቻላችሁ ከጥዋቱ 3 ሰአት በለኩ ፉርቃን ግቢ በመገኘት አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጀመአችን ጥሪውን ያስተላልፋል" ቢላል የለኩ ሙስሊም በጎ አድራጎት ጀመአ

#ድሬዳዋ

💫"የድሬዳዋ ስካውት ካውንስል አባላት ነን በከተማችን የሚገኙ መንገዶች በግራና በቀኝ ያሉ ጠርዞችን ነጭ እና ጥቁር ቀለም በመቀባት ለመንገዱ ውበት እንዲሁም በምሽት ለአሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲታይ በማድረግ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አንፃር የበኩላችንን እየተወጣን ነው ። ስራው ገና አልተጠናቀቀም ነገም እለተ ሰንበት ይቀጥላል።"

#ወሊሶ

💫ወገኔን ለማስተማር እሮጣለሁ በከተማችን ቅን ወጣቶች የተቋቋመው የ" we are one" የበጎ አድራጎት ማህበር ባሳለፍነው አመት "ወገኔን ለማስተማር እኔም እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ታላቅ የእሩጫ ዉድድር ማሰናዳቱ የሚታወስ ነዉ። በዘንድሮ አመትም በተመሳሳይ መሪ ቃል በአይነቱ ልዩ በሆነ ሩጫ ዝግጅቱን አጠናቆ እርሶን እየጠበቀ ይገኛል ታድያ እርሶም የሩጫ ቲሸርት በመግዛት ከአላማችን ጎን ይሰለፉ። የቲሸርቱ ዋጋ 100 ብር የቲሸርቱ መገኛ ቦታ: ፓስታ ቤት፣የኛ ህንፃ ፣ክርኪስ እናም ሁሉም ቦታ አዙረው በመሸጥ ላይ ከሚገኙ አባላቶች

በሌሎች አካባቢዎች ያሉ እንቅስቃሴዎችን እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!
💫የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ የሙዚቃ ድግስ በጌትፋም ሆቴል እየተካሄደ ነው። የዝግጅቱ መግቢያ፦ 12 ደብተር - 2 እስክርቢቶ - 2 እርሳስ - 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ - #onepackforonechild

Via #Sol/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia