TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድሬደዋ‼️

በድሬዳዋ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት የጸጥታ ማስከበር ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ እንዲረከብ መደረጉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በሰሞኑ ሁከት የተጠረጠሩ 200 ሰዎች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ድሬዳዋ እንዲገባ የተደረገው ባለፉት ቀናት በከተማይቱ የነበረው ሁኔታ ከአስተዳደሩ እና ከፌደራል ፖሊስ አቅም በላይ ስለነበር ነው።

የመከላከያ ሰራዊት ከተማይቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን ኮማንድ ፖስቶች በተለያዩ አካባቢዎች ማቋቁሙንም ጽህፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል።

የጀርመን ራድዮ የድሬዳዋ ዘጋቢ #መሳይ_ተክሉ እንደገለጸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በከተማይቱ ተሰማርተዋል። በመኪና ላይ ሆነው ከሚዘዋወሩት በተጨማሪ በየአካባቢው በተጠንቀቅ ቆመው የሚታዩ እንዳሉ ዘጋቢው ተናግሯል። የሰራዊቱ አባላት ለአደጋ ይጋለጣሉ ለተባሉ የመንግስት ተቋማት እና ድርጅቶችም #ጥበቃ እያደረጉ ነው ብሏል።

በከተማይቱ ያለው ዘጋቢያችን የመንግስት ወታደሮቹ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በድምጽ ማጉያ ሲያስጠንቅቁ ተመልክቷል። በድሬዳዋ ሰሞኑን ሲደረጉ የነበሩ የህዝቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ከሚያውኩ ድርጊቶች እንዲታቀቡም ተቃዋሚዎችን ሲያስቡም ታዝቧል።

በድሬዳዋ ላለፉት ሶስት ቀናት ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ጎማዎች በማቃጠል እና ድንጋይ በመደርደር መንገዶችን ዘግተው ነበር። በዛሬው ዕለት በከተማይቱ እንቅስቃሴዎች እንደሚታዩ የገለጸው ዘጋቢያችን መንገዶች መከፈታቸውን እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ስራ መመለሳቸውን ተናግሯል።

በድሬዳዋ ከሰሞኑ በተከሰተው ሁከት ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተጠየቁት የከተማይቱ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እና ፖሊስ “የተደራጀ መረጃ የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ:- DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia