TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BREAKING

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

#MoH #EPHI #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoH_KENYA

ትላንት ኬንያ ውስጥ ተጨማሪ አራት (4) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በመረጋገጡ የትላንትናውን ሪፖርት ጨምሮ አሁን ሪፖርት ከተደረገው ጋር አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 142 መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። የኬንያ ጤና ሚኒስቴርም ቀደም ብሎ ያወጣውን የ138 ሰዎች ኬዝ ሪፖርት በማስተካከል 142 አድርጎታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል!

በዛሬው መግለጫ ላይ የተጠቀሱት የ75 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ ሲሆን በገጠማቸው የመተንፈስ ችግር ምክንያት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኃላ በምርመራ ውጤቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከመረጋገጡ በፊት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

#MoH #EPHI #DrLiaTadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoH

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙከሚል አብደላ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው አሳውቋል።

የአቶ ሙከሚል አብደላ ህልፈተ ህይወት በኮሮና ቫይረስ እንደሆነ ተደርጎ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ #ሃሰት መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

አቶ ሙከሚል አብደላ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ ከኮቪድ-19 በሽታ #ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ምክንያትአልሆንም የኮሮና ስርጭትን እገታለሁ!

ኤ.ቲ.ኤም (ATM) ከመጠቀሜ በፊት እና በኃላ እጄን በውሃ እና በሳሙና ወይም በሳኒታይዘር አፀዳለሁ #EPHI #MoH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoH

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 1 ሺህ 311 የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

በነገው ዕለት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን ተከታዩን ብለዋል ፦

- ኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሥራ ግንባር ቀደም የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ላይ መጠነ ሰፊ ችግር አስከትሏል።

- 1 ሺህ 311 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 700 የሚሆኑት ደግሞ አገግመው ወጥተዋል፤ ቀሪዎቹ በህክምና ተቋማት ይገኛሉ።

- ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችም ለሞት ተዳርገዋል።

- ነገ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቱ የሚከበረው የሕሙማን ቀን ቫይረሱ የተገኘባቸው ወገኖቻቸውን ሌት ተቀን እያገለገሉ ላሉ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ክብርና ምስጋናን በመስጠት ይከበራል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ።

የጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ክትባቱን የወሰዱት በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በመቐለ ጠቅላላ ሆስፒታል ተገኝተው የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት ነው።

ዶ/ር ሊያ ፥ በመላው ሀገሪቱ ለኮሮና ቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከፍ ያሉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን በቀዳሚነት ያገኛሉ ብለዋል፡፡

የክትባቱ አቅርቦት በአለም አቀፍ ደረጃ ውስንነት ስላለው እና ሁሉንም የህብረተስብ ክፍሎች ማዳረስ የማይቻል በመሆኑ ህብረተሰቡ ክትባት መጣ ብሎ መዘናጋት እንደሌለበት እና ቫይረሱን መከላከያ መንግደ በአግባቡ እንዲተገብር አሳስበዋል።

#MoH
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ፦ የብቃት ምዘና ፈተናው ከመጋቢት 20-24/2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የፈተና ፕሮግራሙ ፦ • ነርሲንግ - 20/07/2013 ዓ.ም • ጤና መኮንን - 21/07/2013 ዓ.ም • ህክምና እና ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ - 22/07/2013 ዓ.ም • ፋርማሲ እና አንስቴዥያ - 23/07/2013 ዓ.ም • ሚድዋይፈሪ - 24/07/2013 ዓ.ም * የብቃት…
#Update

ዛሬ የጤና ሚኒስቴር የብቃት ምዘና ፈተና መስጠት ጀምሯል።

በህክምና ፣ ነርሲግ ፣ ጤና መኮንን ፣ አኒስቴዥያ ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጅ ፣ ፋርማሲ እና ሚድዋይፈሪ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ባለሙያዎች ከመጋቢት 20 እስከ 24/07/2013 ዓ.ም ድረስ የብቃት ምዘና ፈተና መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ፈተናው በመላው ሀገሪቱ በተዘጋጀ 38 የፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ ነው።

የፈተና አሰጣጥ ስርአቱን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ እና የሀገር አቀፋ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ከመፈተኛ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው የቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ሜ/ ኮሌጅ በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተናውን የሚወስዱት 18,926 ተመዛኞች ሲሆኑ የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት ብቃታቸውንና ክሎታቸውን ለመመዘን የሚሰጥ ፈተና ነው። #MoH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SinopharmCovid19Vaccine

የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ያበረከተው "ሲኖፋም" የተባለ 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ ገባ።

ክትባቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢውሃን አስረክበዋል። #MoH

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አጭር መረጃ ስለኮቪድ-19 ኢትዮጵያ መተግበሪያ፦

የኮቪድ ኢትዮጵያ መተግበሪያ በውስጡ ስለኮቪድ ቁጥጥር ፣ ህክምና እና መከላከል ማወቅ ያለብንን በ7 ኮርሶች የያዘ ሲሆን ስልጠናው ፦

- የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶቦት በቤት ውስጥ እራሳችንን ለይተን ለራሳችን ማድርግ ስለሚገባን እንክብካቤ እና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ ያሳውቃል።

- ስለኮቪድ-19 ክትባት ለማወቅ እና ስልጠና ለመውሰድ ይጠቅማል።

- ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር ሰራተኞች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ለማውቅ ይረዳል።

- ሰልጣኞች ስልጠና እንዳጠናቀቁ በሚመዘገቡበት የስልክ ቁጥር ባላቸው የቴሌግራም አድራሻ ስልጠናውን በአግባቡ ላጠናቀቁ እና የስልጠና መመዝኛውን ከ80 በመቶ በላይ ላስመዘግቡ በጤና ሚኒስቴር የተረጋገጠ የተከታታይ ሙያ ማጎልብቻ ነጥብ ያለው ሰርተፍኬት የሚላክላቸው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በየ3 አመት ለሚደረገው የሙያ ፍቃድ እድሳት ነጥብ ለመጠቀም ያስችላል።

- መተግበሪያውን በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከጫኑና ስልጠናዎች ካወረዱ በኋላ ኢንተርኔት የማይፍልግ ሲሆን ስልጠናውን የሚስብ እና ለመረዳት ቀላል ለማድረግ ቪድዮዎች ተካተውብታል።

- ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የኮቪድ ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲሁም የተሻለ እንክብካቤ ለመስጠት ይረዳል።

መተግበሪያውን ከየት ላግኘው ?

መተግበሪያውን በስልክዎ ለመጫንና ስልጠናውን ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ - https://bit.ly/3apv5J2

#MoH #EPHI

@tikvagethiopia @tikvagethiopiaBOT