TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
EU_Cotonou and Samoa Agreement_merged.pdf
#SamoaAgreement

ከወር በፊት ሀገራችን #ኢትዮጵያን ጨምሮ አጠቃላይ 79 የአፍሪካ እና የካረቢያንና ፓስፊክ ሀገራት / 48 ከአፍሪካ፣ 16 ከካረቢያን፣ 15 ከፓስፊክ / ሳሞአ ላይ አንድ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የተፈረመው ስምምነት " #የአፍሪካ#የካረቢያን እና #የፓስፊክ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጋር የሚያደርጉት የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር " የሚል ነው።

ስምምነቱ 22 ዓመታትን የዘለቀው " የኮቶኑ ስምምነት " ቀጣይ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህ ስምምነት ግን ብዙ ጥያቄ ተነስቶበታል። 

በቅድሚያ ስምምነቱ ላይ ጥያቄ እና ከፍተኛ ጥርጣሬ የተነሳው #ካረቢያን አካባቢ ነው። 

ስምምነቱ ፤ በካሪቢያን አካባቢ ከባህል እና ከእሴቶች ጋር የማይጣጣሙ ህጎችን በካሪቢያን ህዝብ ላይ ይጭናል በሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው በቅድሚያ የገለፁት ፦
- በትሪንዳድ እና ቶቤጎ የሚገኘው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን 
- የጃማይካ ጥምረት ለጤናማ ማህበረሰብ (JCHS) ናቸው።

በትሪኒዳድ የሚኖሩ አንድ #የሃይማኖት_አባት በሀገር ውስጥ በሚገኝ መገናኛ ብዙሃን ላይ ቃለ ምልልስ ካደረጉ በኃላ ነው ስምምነቱ ላይ #ህዝባዊ_ትችት የመጣው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባት የስምምነት ሰነዱ ' የአውሮፓ ህብረት ' " የእኛ ያልሆነን ርዕዮተ ዓለም " በአስገዳጅነት እንዲጭን የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የጃማይካ ጥምረት ለጤናማ ማህበረሰብ (JCHS) ደግሞ " ተቀባይነት የሌለውን / ውድቅ የተደረገውን አጠቃላይ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ትምህርተ ሥርዓተ ወደ ጃማይካ የመማሪያ ክፍሎች እንደሚመልስ እና የጃማይካውያንን መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ይጎዳል ፤ ከሀገሪቱ ባህልም ያፈነገጠ ነው " በሚል ጠንካራ ተቃውሞ አስምቷል።

እንዚህ አካላት፤ " በማዕቀብ ሰበብ እና ውል በማሰር " ህዝብ የማይቀበለውን #ከባህል_ያፈነገጠ ተግባር ያለማምዳል ፤ ይጭናል በሚለው ነው የተቃወሙት።

በ ' ሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲንስ ' ከዚህ ከባለ 400 ገፆች የሳሞአ ስምምነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስጋት ተሰቅስቅሶ ነበር። እሱም ስምምነቱ ፦
- ሀገሪቱ በፅንስ ማቋረጥ ፣
- በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ 
- በLGBTQ መብቶች ላይ ሀገሪቱ ህጎቿን ለማሻሻል #ትገደዳለች የሚል ነው።

ይህ ጉዳይ እና ስጋት በካረቢያን አካባቢ ከተነሳ በኃላ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ መናጋገሪያ ሆኖ ወደ አንዳንድ #የአፍሪካ_ሀገራት ተሰራጭቷል።

በተለይ ደግሞ በናይጄሪያ፣ በናሚቢያ፣  በታንዛኒያ ... የመሳሰሉ ሀገራት ውስጥ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስምምነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲገልጹ ነበር።

ምንም እንኳን በርካታ ሀገራት ስምምነቱን #በሰዓቱ ቢፈርሙም አንዳንድ ሀገራት ግን ሰነዱ ላይ ዘግይተው ነው የፈረሙት።

ለአብነት ሰነዱን ዘግይተው ከፈረሙት ውስጥ በሰነዱ ላይ በቅድሚያ ከዜጎቿ ጥያቄ የተነሳባት #ጃማይካ አንዷ እና ዋነኛዋ ስትሆን እነ ፦
* ቦትስዋና፣
* ናሚቢያ፣
* ሰኔጋል፣
* ታንዛኒያ፣
* ሶማሊያ፣
* ሩዋንዳ ዘግይተው ከፈረሙት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

➡️ ጥያቄ እና ስጋት በተነሳባቸው ሀገራት ምን ምላሽ ተሰጠ ?

➡️ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ጉዳዩ ምን ተባለ ?

➡️ ስምምነቱን በተመለከተ ፤ " ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግብረሰዶም እንታደግ ማህበር " ምን አለ ?

➡️ በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያን መስፋፋት ምን ያህል አስከፊና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ አጠቃላይ ያለውን ሁኔታ ዳሷል ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-10

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ብሔራዊ_ፈተና

" በበይነ መረብ የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ፈተናውን ለመስረቅ ጥረት አያደርጉም ብለን እንጠብቅም ፤ ያንን ለመከላከል ዝግጅት ተደርጓል  " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በበይነ መረብ / #በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሳይበር ጥቃት እንዳይሰረቅ ዝግጅት መደረጉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ " በዚህ ዓለም ምንም አይነት ችግር የሌለበት ነገር የለም። ሁሉም ነገር የራሱ የሆነ ችግር / ጉድለት ይኖረዋል ያለን ምርጫች ግን ችግሩን የመከላከል አቅም ጎን ለጎን መገንባት ነው " ብለዋል።

" በበይነ መረብ የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ፈተናውን ለመስረቅ ጥረት አያደርጉም ብለን እንጠብቅም " ያሉት ዋና ዳይሬክቲ ፥ " የሳይበር ደህንነት (ሴክዩሪቲ) ስራዎች ፦
° ሞያው ባላቸው ፣
° መሳሪያዎች ባሏቸው
° አቅም ባላቸው ተቋማት በኩል ተገቢ የሆነ ዝግጅት አድርገን እየሰራን ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ፈተናው ብዥታ ለመፍጠር የሚፈልጉ ፣ ፈተናው ላይ ጥቃት ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ማወቅ ያለባቸው ይሄ #የፖለቲካ#የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም ማንም ወላጅ ልጁን አስተምሮ የሚያደርስበት ስለሆነ ሁለት ሶስቴ ማሰብ አለባቸው ፤ ተማሪዎቹ ነገ ለሀገር እዳ እንዳይሆኑ ማሰብ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ከኦንላይን ፈተናው ጋር በተያያዘ ማንም አካል ወላጆችን " ኮምፒዩተር አቅርቡ " አላለም ፤ ሊጠየቁም አይገባም ከተጠየቅም ስህተት ነው ተብሏል።

ፈተና የሚሰጠው መንግሥት በሚያቀርበው አቅርቦት / ኮምፒየተር እንደሆነ ተመላክቷል።

ይህ ማለት የኮምፒዩተር አቅም ኖሯቸው ት/ቤታቸውን ማገዝ የሚፈልጉ ዜጎችን አይችሉም ማለት አይደለም ተብሏል።

የወረቅት ፈተናን በተመለከተ አሁን ላይ ህትመት ወደ መጠናቀቁ ሲሆን ፈተናው ልክ እንዳለፉት ፈተናዎች ደህንነቱ እንዲጠበቅ በቂ ዝግጅት መደረጉ፣ በክፍል ውስጥም ኩረጃ እንዳይኖርና ተማሪዎች በራሳቸውን ሰርተው እንዲያልፉ ካለፈው #በጠነከረ ሁኔታ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።

#Ethiopia
#NationalExam
#Grade12

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
" የሃይማኖት ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ?

በኢትዮጵያ አዲስ የተዘጋጀ " #የሃይማኖት_ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ አለ። ይህ ረቂቅ አዋጅ በርካታ ጉዳዮችን ይዟል።

አንዱ የአምልኮና የመቃብር ቦታን የተመለከተ ሲሆን ፥ ረቂቅ አዋጁ ለሃይማኖት ተቋማት የመሬት አቅርቦት በመሬት አጠቃቀምና የሊዝ ሕጎች መሠረት ይወሰናል ይላል።

ለአምልኮ ወይም ለመቃብር ቦታ በተጠየቀበት አካባቢ ለሃይማኖት ተቋሙ ለተመሳሳይ ዓላማ የተሰጠ ቦታ አለመኖሩ ወይም ደግሞ #ተጨማሪ_ቦታ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ መረጋገጥ እንዳለበትም ይገልጻል።

በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል ላይ የሚኖረው ርቀት ቢያንስ 500 ሜትር መሆን አለበትም ይደነግጋል።

ትምህርትና የሃይማኖት ተግባራትን በተመለከተ ረቂቁ ፥ መደበኛ ትምህርት በሚሰጡ የመንግሥት / የግል ተቋማት የሚሰጠው ትምህርት ሃይማኖታዊ ይዘት የሌለው መሆን አለበት ይላል።

በትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርትን ማስተማር ወይም በቡድን ማምለክ ፈጽሞ የተከለከለ ስለመሆኑ ይገልጻል።

ሌላውረቂቁ ማንነትን ለመለየት ሚያስችሉ ሃይማኖታዊ አለባበሶችን ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደማይገባ ይደነግጋል።

ከአለባበስን ጋር በተያያዘ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት " ሃይማኖታዊ ምልክቶችን እንደ ቤተ እምነቱ አስገዳጅ ሕግጋቶች #ልዩ_ሁኔታዎች እንደሚኖሩ መደንገግ ሲገባው፣ ሙሉ ለሙሉ ከትምህርትና ሥራ ገበታ የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን መያዙ አግባብ አይደለም " በማለት ለሰላም ሚኒስቴር አስተያየት ፣ ቅሬታ እና የመፍትሔ ሐሳብ ልኳል።

የመንግስት ስራ ኃላፊዎችን በተመለከተ መንግሥትን ወክለው በሃይማኖት በዓላት አከባበር ላይ መገኘት እንደማይችሉ ተቀምጧል።

በየት/ቤት ፣ በመኖሪያ ቤት እና በሕክምና ማዕከላት አካባቢ የሚደረግ አምልኮ በተመለከተም ፤ በአካባቢ ጥበቃ ሕግ የተቀመጠውን የድምፅ መጠን ያከበረ መሆን አለበት ይላል።

ካልተፈቀደ በስተቀር ማስተማርን ጨምሮ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች መፈጸም እንደማይቻልም ተቀምጧል።

የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል  ይህ በልዩ ሁኔታ በወንጌል አማኞች ላይ ጫና የሚፈጥርና ሕገ መንግሥታዊ የሆነ መሠረት የሌለው በመሆኑን መስተካከል ይኖርበታል በማለት ለሰላም ሚኒስቴር ደብዳቤ ልኳል።

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia