TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮምቦልቻ

"እኛ የኢትዮጵያ መንገዶችን ባለስልጣን የኮምቦልቻ መንገድ አውታርና ደህንነት ማኔጅመንት ሰራተኞች በዶ/ር አብይ የተጀመረውን የችግኝ ተከላ ፕሮጀክት ጀምረናል።" ሀይሉወሰን በቀለ ከኮምቦልቻ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮምቦልቻ

"በአካባቢው የነበሩ የሙስሊም ማህበረሰቦች ከኛ ጋር አብረው እየጮሁ፣ እየተጨነቁ፣ አፈርና ውሀ እየተሸከሙ እሳቱን ለማጥፋት ላደረጉት ርብርብ መድሀኒዓለም ጤና እና እድሜ ይስጥልን!" የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Dessise #Kombolcha

በዛሬው ዕለት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የ #ደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ሲሾሙ አቶ መሀመድ አሚን ደግሞ የ #ኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

የደሴ ከተማ አሰተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት 31ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

በሌላ በኩል የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ መሀመድ አሚን ኮምቦልቻ ከተማን በከንቲባነት እንዲመሩ ሾሟቸዋል።

@tikvahethiopia
#ኮምቦልቻ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በከተማው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 35 ህገ ወጥ ሞተር ብስክሌቶች በቁጥጥር ስር ዋሉን ገልጿል።

ሞተር ብስክሌቶቹ ከወልድያ ፣ መርሳ እና ሀይቅ የመጡ እንደሆነና ከኮምቦልቻ ከተማም ያሉ ሞተሮች እንደሚገኙበት ተመላክቷል።

ሞተሮቹ ሠሌዳ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ የሌላቸው ናቸው ተብሏል።

እነዚህ ሞተሮች እስከ 50,000 ብር የሚጠጋ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የተገለፀ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሞተሮች በህገ ወጥ ተግባራት የመሠማራት ዝንባሌ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከዚህ በፊትም 400 ህገ ወጥ ባጃጆች ወደ መጡበት ተመልሰዋል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ደቡብ_ወሎ በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው…
#Update

#ሰቆጣ

መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮምቦልቻ

ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው ተገልጾ መላው ነዋሪ ተረጋግቶ በንቃት አካባቢውን በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በከተማዋ እስከሁን ባለው ከ400 በላይ ባጃጆች እና 80 ሞተሮች በህግ ቁጥጥር ስር ገብተው ማጣራት ተደርጎ ወደየመጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሁሉም ነዋሪ በቀበሌና ቀጠና ብሎክ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና በእቃ ዋጋ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ደሴ

ዛሬ በደሴ ከአምስቱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚሁ መድረክ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በማሰራጨት ህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የከተማው ወጣት በሙሉ በሀሰተኛ ወሬ እና በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይረበሽ ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በመሆን አካባቢውን እና የከተማውን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

በከተማው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ተነግሯል።

#ወልድያ

ወልዲያ ከተማ አዳሯ ሰላም የነበረ ሲሆን የዛሬ ውሎዋም ሰላም ነው። አሁንም ቢሆን መላው ነዋሪ ተረጋግቶ አካባቢውን በመጠብቅ የከተማዋን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ሰቆጣ መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል። #ኮምቦልቻ ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር። በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው…
#Update

#ወልድያ

ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችው ወልድያ ዛሬ ወደ ቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷ ተገልጿል። ከከተማዋ ወጥተው የነበሩም ተመልሰዋል። መደበኛ ትራንስፖርት ፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ጀምረዋል።

ዛሬ ጥዋት ላይ አቢሲንያ እና ህብረት ባንኮች ስራ መጀመራቸው እና ሌሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል ፤ በዚሁ መሰረት ከሰዓት በከተማው ውስጥ ያሉ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

#ደሴ

ደሴ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለች ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ በመራቅ ሰላሙን ሊያስጠብቅ ይገባዋል። በሀሰተኛ መረጃ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

#ኮምቦልቻ

ዛሬም እንደትላንቱ ኮምፖልቻ ከተማ እና ነዋሪዎቿ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሆኑ አሁንም ነዋሪው ተረብሾ አካባቢውን ለቆ ፣ ንብረቱን ጥሎ እንዲወጣ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና አሉባልታዎች ሊኖሩ ይችላሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

#ሐይቅ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨ የሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን የመመለስ ስራ በከተማው አስተዳደር እየተሰራ ነው። በተጨማሪ በከተማው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲሁም የኬላ ላይ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን መላው ነዋሪ የወጡትን ክልከላዎች እና ገደቦች እንዲያከብር ተጠይቋል።

#ሸዋሮቢት

በትላንትናው ዕለት " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች የተገደሉት የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን መፈፀሙን ከተማ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Woldia በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ  ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል። ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል። ክልከላዎቹ ፦ - ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም። - ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች…
#ኮምቦልቻ

ከዛሬ ጀምሮ ኮምቦልቻ ውስጥ ሰልፍ ማድረግ አድማ መጥራት ተከለከለ ፤ የሰዓት እላፊም ታውጇል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከተወያየ በኋላ ክልከላዎች አውጥቷል።

ምን ክልከላዎች ተጣሉ ?

1ኛ. ከዛሬ ሚያዚያ 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሰልፍ ማድረግ አድማ መጥራት ተከልክሏል።

2ኛ. ከተፈቀደላቸው የመንግስት የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

3ኛ. ከተፈቀደላቸው የመንግስት ተሽከርካሪዎች እና አምቡላንሶች ውጭ ማንኛውም ባለ ሁለትና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።

4ኛ. የመጠጥእና ምግብ ቤቶችም አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ ነው ተብሏል።

5ኛ. የሰዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ የተርሃዊ ሶላት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ የተፈቀደ ሲሆን ከ3:00 ሰዓት ውጭ የማንኛውም ግለሰብ እንቅስቃሴ ተገድቧል።

6ኛ. በህግ ከተፈቀደላቸው የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ የጸጥታ መዋቅሮችን ልብስ ለብሶ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

ክልከላዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

መረጃው የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ነው።

@tikvahethiopia