ህፃን በፀሎት ብርሃኑ‼️
አሰቃቂ ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ቀደም ሲል የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በርካቶች ሌላ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ፡፡
በርካታ ቁጥር ያላቸው የደሴ ከተማዋ ነዋሪዎች የሰባት ዓመት ህጻን በአሰቃቂ ሁኔታ #የገደለው ግለሰብ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል #እርምጃ እንዲወሰድበትም ትላንት በአደባባይ ጠይቀዋል፡፡
የሟች ህጻን በጸሎት ብርሃኑ እናት ወይዘሮ አበባ ሙህዬ ልጃቸው ባለፈው ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ለጨዋታ እንደወጣች ሳትመለስ መቅረቷን ይናገራሉ፡፡
በልጃቸው ያልተለመደ መዘግየትና ወጥቶ መቀረት የተደናገጡት እናት ከአካባቢው ሰዎች ጋር በመሆን ፍለጋ ቢያካሂዱም ህጻኗ ሳትገኝ ቀርታለች፡፡
ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ህጻኗ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ አስክሬኗ መገኘቱን የገለጹት ወይዘሮ አበባ በጥርጣሬ ከተያዙት ግለሰቦች ከአንዱ ጋር በትዳር አብረው የቆዩ መሆናቸውንና አንድ ልጅ ከወለዱለት በኋላ መፋታታቸውን ተናግረዋል።
ፍቺውን ተከትሎ ግለሰቡ ለመግደል በተደጋጋሚ ሲዝትባቸው መቆየቱን ነው የጠቆሙት፡፡
ህጻኗ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ አስክሬኗ መገኘቱ እንደተሰማ ትላንት በደሴ ከተማ #አለመረጋጋት ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ወንጀሉን በፈጸመው ሰው ላይ የማያዳግምና ሌላውን ሊያስተምር የሚችል ርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንደሰን ጸጋዬ በበኩላቸው ድርጊቱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የህጻኗ አስከሬን ከትናንት በስቲያ በምትኖርበት አካባቢ ከሚገኝ ጫካ በጆንያ ውስጥ #ተጠቅልሎ መገኘቱን ተከትሎ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከጉዳዩ ጋር ግንኙት ይኖራቸዋል የተባሉ ሦስት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል፡፡
🔹ዛሬ በደሴ ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ውጥረት መረጋጋቱን ለመስማት ተችሏል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ወንጀል ነክ መረጃ‼️
የስራ ባልደረባውን #የገደለው የፖሊስ አባል #በጽኑ_እስራት ተቀጣ፡፡ በጋምቤላ ክልል ልዩ ቦታው ደንቦስኮ በተባለው አካባቢ ከምሽቱ 3፡00 በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ የስራ ባልደረባውን የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው 3 ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ተከሳሹ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሲሆን ከሌሎች አስራ ሁለት አባላት ጋር ለግዳጂ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ሙኒ ከተባለ ቦታ የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ለማደር ተገኝው ባሉበት ወቅት ሰው ለመግደል አስቦ በስናይፐር ጠመንጃ ተኩሶ ሁለት የስራ ባልደረቦችን አንደኛውን ሆዱ እና ሁለተኛውን ጭንቅላቱ ላይ በመምታት ደም ፈሷቸው ህይወታቸው እንዲያልፍ በማድረጉ እና በ3ኛ ክስ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት በሌላ ሰው አካል ወይም ጤና ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ 3ኛውን የስራ ባልደረባውን ተኩሶ ግራ ታፋውን በመምታት እንዲቆስልና የህመም ስሜት እንዲሰማው በማድረጉ በፈጸመው አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሷል፡፡
ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎትም ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ19 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት ወስኗል፡፡
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

ሰው #የገደለው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ። በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 ክልል ልዩ ቦታው አክሱም ሆቴል ጀርባ ከምሽቱ 4፡00 በሽጉጥ ሰው የገደለው የጥበቃ ሰራተኛ በፈፀመው ወንጀል በእስራት ተቀጣ፡፡
የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሐ የተመለከተውን በመተላለፍ ሰውን ለመግደል በማሰብ በጥበቃና በአትክልተኛነት የሰራ መደብ ተቀጥሮ በሚሰራበት ኤም ኤስ ኮንሰልታንት ድርጅት ውስጥ በዕለቱ ድርጅቱ የሚከፍለውን ወራዊ ደመወዝ ከወሰደ በኋላ ብዙ የድርጅቱ ሰራተኞች ደመወዛቸውን እንዳልወሰዱ ስለተረዳ ገንዘቡን ከተቀመጠበት ለመውሰድ የድርጅቱን አጥር ዘሎ እና ቢሮ ፈልቀቆ በመግባት ገንዘቡ የተቀመጠበትን ካዝና በዶማ ለመክፈት ሲሞክር የዕለቱ ተረኛ ጥበቃ የነበረው ማነው ብሎ ሲጮህ እንዳይለየውና እሱ መሆኑን እንዳይረጋገጥ በማሰብ በያዘው ሽጉጥ ወደ ሰማይ በመተኮስ ዝም እንዲል ካደረገው በኋላ ዘሎ በመውጣት መሮጥ ሲጀምር ከሚሰራበት ድርጅት ጎን የሴቶችና ህጻናት ልማት ጥበቃ የሆነው ሟች ቁም ሲለው የፈጸመው ወንጀል እንዳይገለጽ ለማድረግ ሲል ይዞት በነበረው ሽጉጥ ተኩሶ በመምታት ጨካኝና አደገኛ መሆኑን በሚገልጽ ሁኔታ የገደለው በመሆኑ በፈጸመው ከባድ የሰው ግዲያ ወንጀል ተከሷል፡፡
ዐቃቤ ህግም ከዳግማዊ ምኒሊክ የአስከሬን ምርመራ ውጤትን በማስመጣት እና ሌሎች የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናከር ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡