TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ይባብ ግቢ ተማሪዎች፦ @tsegabwolde @tikvahethiopia
ከይባብ ግቢ...

"እሄ ማስተወቅያ የወጣው በ05/05/2011 ግን ትላት ክላስ #አልገባንም። class የገቡትን ምህራን ሲየስወጡ ነበር እናም ክላስ ለገቡት ተማሪዎች ምንም አይነት #ከለላ አልተደረገም ዛሬም ክላስ የለም!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
" ... አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " - አቶ ዳመነ ተሾመ

ከጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ. ም ጀምሮ እስካሁን ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአዳማ እስከ መተሃራ ባለው አውራ ጎዳና የሚንቀሳቀሱ 5 የአገር አቋራጭ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ታግተው ተወስደው 3ቱ #በሕይወት_እንዳልተገኙ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማሕበር አመራር አባል አቶ ዳመነ ተሾመ ለዶቼ ቬለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " ታግተው ጫካ ከተወሰዱት 5 ሹፌሮች መካከል ገንዘብ ከፍለው የወጡ አሉ " ብለዋል።

አቶ ዳመነ ፤ ይህንን እገታ የፈፀሙትን አካላት ማንነት እንዳላወቁትና መንግሥትም የደረሰበት እንደማይመስላቸው ተናግረዋል።

" በኮሪደሩ ላይ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረ ነው። አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " ብለዋል።

ማሕበራቸው ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጋር ትናንት በችግሩ እና መፍትሔዎች ዙሪያ መወያየቱን ገልፀው ፤ " የሾፌሮች መታገት እና መንገላታት ይቁም። እኛ የአበል፣ የደሞዝ ጥያቄ ሳይሆን መንግሥት #ከለላ እና #ጥበቃ ያድርግልን የሚለውን ሀሳብ አንሸራሽረናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዋናነት ከአዳማ እስከ መተሃራ በምእራብ ወለጋ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ችግር ውስጥ እንደሆኑ የጠቆሙት አቶ ዳመነ አሽከርካሪዎቻችን ወደ ቤታቸው ለመግባት በየመንገዱ ችግር እየተፈጠረባቸው ወደ 21 ቀናቶችን ፈጅቶባቸዋል " በማለት የሚገጥማቸው ችግር ምን ያህል አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ አስገንዝበዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ ሬድዮ

@tikvahethiopia