TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የሚድሮክ #ለገደምቢ_የወርቅ_ማምረቻ ኩባንያን ዕገዳ እንደተነሳ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች #በዝግ ስብሰባ ገልፀዋል ተብሎ የሚነገረው ዘገባ ሐሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AU2022Summit

ህብረቱ በዝግ እየመከረ ነው።

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት #በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች እየመከረ ይገኛል፡፡

በአህጉሪቱ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በተከናወኑ ስራዎችና በተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ነው በዝግ እየመከረ የሚገኘው።

ዛሬ ምሽት ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ዶ/ር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአፍርካ ሀገራት መሪዎች የእራት ግብዣ እንደሚያደርጉ ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

- ከደቡብ አፍሪካ ፣ ፕሪቶሪያ የቀጠለው የናይሮቢው የሰላም ውይይት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም ውይይቱ እስከ ትላንት ሀሙስ ድረስ መቀጠሉን ለጉዳዩ ቅርበትና መረጃው ያላቸው አካላት ተናግረዋል።

እስካሁን ውይይቱ ስልተደረሰበት ደረጃ ምንም ይፋ የሆነ መረጃ የለም።

#በዝግ እየተካሄደ በመሆኑ ሚዲያዎችም ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለመናገር እድል አላገኙም። በውይይቱ ፍፃሜ ላይ ስለተደረሰበት ደረጃ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የፖለቲካ ተደራዳሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እየተካፈሉበት ያለው የናይሮቢው የሰላም ውይይት #አጀንዳዎች ናቸው ከተባሉት መካከል ፦

👉 የሰላም ስምምነቱን ሂደትና አፈፃፀም መከታተል፣
👉 የህወሓት ኃይሎችን ትጥቅ ስለማስፈታት፣
👉 በትግራይ ክልል ለወራት ተቋርጦ የነበረውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ስለማስቀጠል፣
👉 የመሠረታዊ አገልግሎቶች መልሶ ስለማስጀመር ይገኙበታል።

- የሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ላይ በኬንያ ፣ ናይሮቢ እየተመከረ ባለበት በአሁን ወቅት የኤርትራ ኃይሎች #በትግራይ ውስጥ መጠነ ሰፊ ዘረፋ ፣ አፈና ፣ ግድያ ፣ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ሲሉ ከህወሓት አመራሮች መካከል ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት በትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

በሽረ አካባቢ የኤርትራ ኃይሎች ሲቪሎችን / ሴቶችን ጨምሮ በዘረፋ ላይ ተሰማርተው ታይተዋል ያሉ ሲሆን በከተማው ከሰዓት እላፊ በኃላ በጨለማ ሁሉንም ክፉ ነገር እያደረጉ ነው ብለዋል።

ይህንን መልዕክት ካሰራጩ በኃላ በናይሮቢ የሚገኙት የህወሓት ተደራዳሪ እና የሰላም ስምምነቱ ፈራሚ አቶ ጌታቸው ረዳ መልዕክቱን " ክንደያ ትግራይ ናቸው " ሲሉ አጋርተዋል።

አቶ ጌታቸው ይህንን ከማለት በዘለለ ምንም ዝርዝር ነገር አልፃፉም።

- አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ትላንትና ለሊት ባሰራጫችው ፅሁፍ ፤ " አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በናይሮቢ እንደተናገሩት ፤ በፕሪቶሪያ እንደተደረሰው ስምምነት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ የሰብዓዊ እርዳታ ያለምንም እንቅፋት ይገባል ብለዋል " ብላለች።

አሜሪካ ፤ " በትግራይ፣ አፋርና አማራ የሚገኙ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያን አሁኑኑ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል " ስትል ገልፃለች።

#የመሰረታዊ_አገልግሎቶች ወደ ነበረበት መመለስ ፣ የሲቪሎች ጥበቃ እና የሰብአዊ መብቶች ተጠያቂነትን ያነሳችው አሜሪካ ስምምነቱን ለማክበርና ለመተግበር የሚወሰዱ እርምጃዎችን በአስቸኳይ በመጠባበቅ ላይ ነን ብላለች።

- ኬንያ ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የጠ/ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በአሁን ሰዓት ሰባ በመቶ (70%) ትግራይ በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝ ገልፀዋል። እስካሁን በሀገር መከላከያ ባልተያዙ ቦታዎች ሳይቀር እርዳታ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየገባ ነው ብለዋል።

ምግብ  የጫኑ 35  ተሽከርካሪዎችና መድሃኒት የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ሽረ ከተማ መግባታቸውን የገለፁት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ " በረራዎች ተፈቅደዋል፣ አገልግሎቶች እንደገና እየተገናኙ ነው ። " ብለዋል።

የሰላም ስምምነቱ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እድሎችን ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል። እርዳታን በተመለከተ ምንም አይነት እንቅፋት የለም ሲሉ አክለዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ፤ " አንዳንድ ጥግ ላይ ያሉ አካላት የአፍሪካውያን እውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት #ደስተኛ_አይመስሉም ፤ መንፈሱንም ለማበላሸት እየተሯሯጡ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia