TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ደራሲ ፍቅረማርቆስ⬇️

ታዋቂው ደራሲ #ፍቅረማርቆስ_ደስታ ከ9 አመታት ስደት በኋላ አገሩ ገብቷል። ፍቅረማርቆስ ደስታ በደቡብ ውስጥ በሚገኙት #በሃመር ብሄረሰቦች ላይ ተመርኩዞ ከቡስካ በስተጀርባ ከተሰኘው ልቦለድ መጽሃፍ ጀምሮ አያሌ መጽሃፍትን አሳትሟል።

ፍቅረማርቆስ በጎጃም ቢወለድም #በመምህርነት ወደ ሃመር ሄዶ በሃመሮች ባህልና ቱፊት ተማርኮ በባህሉም መሰረት የብሄረሰቡ አባል
ሆኗል።

ፍቅረማቆስ በሃመር ውስጥ እጅግ ተወዳጅ ሰው ነው ለ9 አመታት የተለያቸውን ሀመሮች ለማግኘት #ዛሬ ወደ ሀመር ይበራል።

ፍቅረ ማርቆስ ሀመር ሲደርስ ጠፍቶ የመጣ ሰው ከማህበረሰቡ ጋር ለመቀላቀል #መገረፍ ስላለበት በጎረምሶች ከተገረፈ በኋላ ከማህበረሰቡ ጋር ይቀላቀላል።

©አሀዱ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba🏫

የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና፣ ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን የመምህራንና የትምህርት ቤቶች አመራር ፈቃድ ቡድን መሪ ሰንደቁ ያዛቸው ፦

" በ2013 ዓ.ም የተደረገ ጥናት በአዲስ አበባ በግል ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን 24 በመቶ የሚሆኑት #በመምህርነት ሙያ ያልሰለጠኑ መሆናቸውን ያሳያል።

በመንግስት ት/ ቤቶች በማስተማር ላይ ከሚገኙት መካከል 4 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑ መምህራን ባልሰለጠኑበት የመምህርነት ሙያ በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

ይህም ለትምህርት ጥራት መጓደል ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ አለው። ችግሩን ለመቅረፍ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርት ሚኒስቴር ተቀናጅተው መስራት አለባቸው "

🏫 በአዲስ አበባ 1 ሺ 562 የግል ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲሆን በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥም ከ23 ሺህ 400 በላይ መምህራን እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

#ENA

@tikvahethiopia