TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ናዲያ ሙራድ🕊 በፈረንጆቹ 2014 በሃገሯ #ኢራቅ በጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን #አይ_ኤስ ታግታ የቆየችና #የወሲብ ጥቃት ሰለባ የሆነች ወጣት ናት። ከቡድኑ እገታ ከወጣች በኋላም ይህን መሰሉ #ጥቃት እንዲቆምና በጦርነት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ #ሴቶችን ለመታደግ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ናዲያ ላደረገችው ጥረት የዘንድሮው የኖቤል #የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
.
.
እኔ ግሌ እስካሁን ድረስ በህይወቴ ውስጥ ካየኋቸው እና ታሪካቸውን ከሰማሁ ድንቅ ሰዎች አንዷ ናት። ከእርሷ ጥንካሬን፣ ተስፋ አለመቁረጥን፣ ሰላም ወዳድ መሆንን፣ ለሰው ልጅ መኖርን ተምሪያለሁ! ዛሬ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ለናዲያ ያለኝን ትልቅ ክብር ለመገልፀ እወዳለሁ!
.
.
🕊🕊🕊ናዲያ ሙራድ🕊🕊🕊
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት አገር በቀል የሆኑ የግጭት አፈታት እሴቶችን ማጎልበት እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ። እርቅ ላይ የሚሰሩ #ሴቶችን ማፍራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል። አገር አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላም ኮንፈረንስ ''ሴቶች ዘረኝነትን በመጠየፍ ለሰላማችን ግንባር ቀደም ሚናችንን እንወጣ'' በሚል መሪ
ቃል ትላንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ " #አራ " ከሚባል ስፍራ 77 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መገልበጧ መገለጹ ይታወሳል።

በዚህም አደጋ የ5 ዓመት #ሕጻናት እና #ሴቶችን ጨምሮ 16 ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ መገለጹ አይዘነጋም።

የIOM የጅቡቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ታንጃ ፓሲፊክ ፤ የሟቾች ቁጥር ቀደም ሲል ከሰጠው መረጃ ማለትም 16 ከፍ ማለቱንና 21 መድረሱን ተናግረዋል።

የሞቱት ሁሉም #ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጸዋል።

23 ሰዎች አሁንም ድረስ የት እንደገቡ እንኳን አይታወቅም ብለዋል።

33 ሰዎች ከአደጋው እንደተረፉ ገልጸዋል።

ይህ አደጋ #38_ኢትዮጵያውን ከሞቱበት አደጋ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተከሰተ ነው።

በርካታ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ህይወታቸውን ለመቀረ ሲሉ በአደገኛው እና ህገወጥ በሆነው መንገድ ሀገራቸውን ጥለው ይሰደዳሉ ፤ በዚህም ህይወታቸውን ባህር ላይ ያጣሉ ፣ ይታሰራሉ፣ በየበረሃው ይንገላታሉ ፣ በደላሎች ታግተው ይሰቃያሉ ።

ሀገር ጥለው በህወጥ መንገድ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም።

@tikvahethiopia