TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Congratulations

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 9 ሺህ 750 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው 9 ሺህ 750 ተማሪዎችን በተለያዩ መርሀ ገብሮች እያስመረቀ ነው፡፡

በፕሬዝዳንቱ እንደተገለጸው ከተመራቂዎች መካከል 6 ሺህ 520 ያህሉ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 3 ሺህ 167 በሁለተኛ ዲግሪና 63 በሦስተኛ ዲግሪ የሚመረቁ ናቸው፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምሥራቅ አፍሪካ #ብቸኛ በሆነበት በማሪታይም አካዳሚ ጭምር በርካቶችን እያስመረቀ መሆኑን የገለጹት ዶክተር #ፍሬው_ተገኝ በትምህርት ጥራት ተወዳዳሪነቱ በየጊዜው እያደገ መምጣቱን አብራርተዋል። በሕግ ትምህርት ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1ኛ እና 3ኛ ደረጃ የያዙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሆናቸውንም በአብነት አንስተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለሕይወት ዘመን የሚበጁ ዕውቀቶችን እንዳስታጠቃቸው በመግለጽ በምክንያታዊነት የሚያምኑ ሀገር የሚገነቡ ዜጎች እንዲሆኑም ተመራቂዎቹን አሳስበዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ336 ፕሮግራሞች እያስተማረ እንደሚገኝ ያመለከቱት ፕሬዝዳንቱ ተመራቂዎችን የሕይወት ዘመን ተማሪዎች እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የድህረ ዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቀዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia