TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ250,000 ብር በላይ ድጋፍ ተደርገ🔝

በባህርዳርና በደብረ ታቦር የሚኖሩ የአስቴ ወረዳ ነዋሪዎች በቅርቡ የተቃጠሉትን ሁለት መስጅዶች ለመስራት የሚያስችል ሩብ ሚሊዮን ብርና #የሲሚንቶ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ተወላጆቹ በራሳቸው ተነሳችነት ብሩን ከመሰብሰብ ባለፈ ቦታው ደረስ በመሄድ የጎዳቱን ሁኔታ በመመልከት የአለኝታነት ድጋፋቸውን እንዳሳዩ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
በዛሬው ዕለት ገልጸዋል፡፡

ተወላጆቹ ለመስጅዶች ግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ ካስረከቡት 250 ሺህ ብር በተጨማሪም ለግንባታው የሚውል 100 ኩንታል ሲሚንቶ አበርክተዋል፡፡

ተወላጆቹ ድርጊቱን አውግዘው ምንም ዓይነት እኩይ ዓላማ ያለው አካል ትንኮሳ #ቢፈፅም የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንድነት የበለጠ ይጠናከራል እንጂ ምንም ዓይነት የሚፈጠር ነገር የለም ብለዋል፡፡

ድጋፉን ያሰባሰቡት የሁለቱም እምነት ተከታይ የወረዳዋ ተወላጆች አጥፊዎቹ ታድነው ተገቢው ቅጣት እንዲሰጣቸውም በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ጠይቀዋል፡፡

አጥፊዎችን ለመለየት ከተያዙት 6 #ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ምርመራው #ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡ የተቃጠሉት መስጅዶች ግንባታ በፍጥነት እንደሚጀመር ተመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ላይ የተቃጠለውን የጃራ ገዶ መስጅድ የአካባቢው ማህበረሰብ 27 ሺህ ብር በማዋጣት መልሶ የመስራት ሂደቱን እንደጀመረ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ለኢቢሲ አመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia