TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሶሪያ ስደተኞች በኢትዮጵያ‼️

የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ መምሪያ የኢትዮጵያን ህግ ተላልፈው #በልመና ላይ የተሰማሩ የሶሪያ ዜጎችን አሰሳ በማካሄድ ህጋዊ መስመር እንዲይዙ በማድረግ ላይ መሆኑንና እስካሁንም 118 ስደተኞችን መዝግቦ ለስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ማስረከቡን አስታወቀ፡፡

በስድስት ወር ጊዜ ውስጥም 559 #ሶሪያውያን በቱሪስት ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ጠቅሷል፡፡

በመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ አቶ የማነ ገብረመስቀል ለጋዜጣው ሪፖርተር እንደገለጹት፣ የቁጥጥርና ክትትል ሥራ በሚያከናውነው የመምሪያው ክፍል አማካኝነት ቦሌ ሚካኤል፣ ቦሌ መድኃኒዓለም፣ መርካቶ አንዋር መስጂድ፣ በእንግዳ ማረፊያዎች፣ ሆቴሎችና በሌሎችም ይገኙባቸዋል ተብለው በተጠረጠሩ አካባቢዎች አሰሳ በማካሄድ በህዳርና ታህሳስ ወሮች ብቻ 77፣ ቀደም ሲል ደግሞ 41 ሶሪያውያንን መዝግቦ ለስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር በማስረከብ ህጋዊ ስደተኞች እንዲሆኑ ማድረግ ችሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia