ገበታ ለሸገር ከዶክተር አብይ ጋር...!
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ለአዲስ አበባ ወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት አዘጋጁ።
ለእራት ምሽት ዲፕሎማቶች፣ የኩባንያ ስራ አስኪያጆች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እና ሎሎች አካላት እንዲሳተፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
የእራት ምሽቱ ለሸገር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር በሚል መሪ ቃል መዘጋጀቱ ነው የተነገረው።
ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ጥሪም አዲስ አበባን #ንፁህና #አረንጓዴ ለማድረግ ተሳትፏችሁ የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ያስችላል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፋችሁ ይህን ታላቅ አላማ #ስኬታማ በማድረግ የመዲናዋን ነዋሪዎች አኗኗር ለመቀየር ወሳኝ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
በአዲስ አበባ ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላይ የምታደርጉት ተሳትፎ ለቀጣይ ትውልድ ውብ ከተማን ለማስተላፍ በዋጋ የማይተመን ነው በማለት ገልፀዋል። በዚህ የእራት ምሽት አንድ እራትን 5 ሚሊየን ብር #ለመሸጥ ዋጋ ተቆርጦለታል።
የአዲስ አበባን ዋና ዋና ወንዞች ተፋሰስ #ለማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት እና ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በሶማሌ ክልል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈንና ክልሉን #ለማልማት የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ በድጋሚ አስታውቋል።
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ
የትግራይ ክልልን #ለማልማት በመቐለ ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ 400 ሚሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ ከእቅድ በላይ 519 ሚሊየን ብር ተገኝቷል ተብሏል። 'የክልሉ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው መድረክ ላይ የክልሉ ባለሃብቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በዛሬው መድረክ ላይ ከእቅድ በላይ የተገኘ ሲሆን፥ ገቢው ክልሉን ለማልማት በተደረገው ጥሪ መሰረት የተገኘ ነው ተብሏል።

#አማዞን
ብራዚል በአማዞን የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር ከቡድን 7 ሀገራት የተደረጋለትን የ22 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ውድቅ ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል።
የቡድን ሰባት ሀገራት መሪዎች በፈረንሳይ እያደረጉት ባለው ስብሰባ በአማዞን የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የ22 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸውን የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መግለፃቸው ይታወሳል። በአንፃሩ የብራዚል ባለስልጣናት የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ከቡድን 7 ሀገራት የተደረገላቸውን የ22 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መቃወማቸው ነው የተገለጸው።
ይሁን እንጂ በለስልጣናቱ ድጋፉን የተቃወሙበትን ምክንያት ከመግለጽ ተቆጥበዋል ነው የተባለው። በሌላ በኩል የብራዚል ፕሬዚዳንት ቦልሶናሮ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስታያየት፥ ፈረንሳይ ብራዚልን እንደ ቅኝ ግዛት የምታይበትን መንገድ ኮንነዋል።
የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈርናንዶ አዝቬዶ ኢ ሲልቫ በበኩላቸው ፥ በአማዞን ደን ላይ የተከሰተው ሰደድ እሳት ከሀገሪቱ ቁጥጥር ውጭ አለመሆኑን ተናግረዋል። በደኑ ላይ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠርና በአካባቢው የሚሰሩ ወንጀሎችን ለመከላከልም 44 ሺህ በላይ ወታደሮች በቦታው መሰማራታቸውን አንስተዋል።
ሀገራቱ ድጋፍ ለማድረግ #መስማማታቸውን ያመሰገኑት ሚኒስትሩ፥ ድጋፉን በአውሮፓ የሚገኙ ደኖችን መልሶ #ለማልማት ያውሉት ዘንድ አሳስበዋል። ሚኒስትሩ አክለውም ብራዚል ማንኛውንም ሀገር ደኖችን እንዴት መንከባከብ፣ መጠበቅ እንዲሁም ከጉዳት መካላከል እንደሚቻል የማስተማር አቅም ያላት መሆኑን አስገንዝበዋል።
Via fbc