TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ይቅርታ/Forgiveness!

ከሰው ፍጥረት ሁሉ በስብዕና ከፍታ ላይ የወጣው ይቅር ባይ #ልብ ያለው ሰው ነው።

ይቅርታ የልብን ሸክም ይቀንሳል፥ የፈጣሪን ውዴታ ያስገኛል። ይቅር ስንባባል ስኬት ትቀርበናለች፥ ውድቀት ይርቀናል። የውድቀት መርከብ በይቅርታ ባህር ላይ ትንሳፈፋለች።

ነገሩ እንዲህ ነው... The #Weak can never #forgive. Forgiveness is the attribute of the strong. ይቅርታ ማድረግ የጠንካሮች ባህሪ ነው።

Only the #brave know how to forgive...A coward never forgive; it is not in his nature. ይቅርታ አላደርግም ማለት #ከፈሪዎች ተርታ ያሰልፈናል። መጀመሪያ ለገዛ #ራሳችን #ይቅር እንበል፥ ከዚያ እርስ በርሳችን ይቅር እንባባል። በመካከላችን ምንም ቅራኔ ከሌለ የስኬት መርከባችን በ ብርሀን ፍጥነት/Speed of light ልክ ትፈጥናለች፥ ትጓዛለች።

ይቅር እንባባል ሁሌም!!

ክፉ አይንካችሁ #ሰላም_እደሩ!

©Biyya Koof Lammii Koof
@tsegabwolde @tikvahethopia
#update ከፍራንክፈርት የተነሳው በፕሮፌሰር ብርሀኑን ነጋ እና አንዳርጋቸው ፅጌ የተመራው የአርብኞች ግንቦት 7 ልዑክን የያዘው አይሮፕላን #በሰላም አዲስ አበባ አርፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቦሌ አየር ማረፊያ⬆️

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮችን አቀባበል ለመዘገብ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ የሄዱ ጋዜጠኞች #እንዳይገቡ ተከለከሉ። የ170 ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር ለፀጥታ ኃይሎች የተሰጠ ቢሆንም ስማቸው #ተመርጦ የተከበበ ብቻ እንዲገቡ ተደርጓል። ጋዜጠኞች ገብተው ቪዲዮ የሚቀርጹ ወይም በተቃራኒው ያልገባላቸው ሚዲያዎች አሉ። የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምርጫውን ለምን እና በምን መስፈርት እንዳደረገ የጥበቃ ሰራተኞች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል። “ያልተከበበ አይገባም” ብለዋል።

©ኢሳት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ስታዲየም⬆️

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮችን ለመቀበል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሚደረገው ዝግጅት ተጠናቋል። በስታዲየሙ በሚደረገው አቀባበል በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

©ECAD
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦነግ⬆️

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ አመራሮች መስከረም 5/2011 አዲስ አበባ እንደሚገቡ የኣቀባበል ኣስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

ለኦነግ አመራሮች ከቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ጀምሮ ኣቀባበል እንደሚደረግላቸው ኣስተባባሪ ኮሚቴው ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኮሚቴው እንዳለው በዚያው ዕለት ለኦነግ አመራሮችና ከውጭ ለሚመጣው የኦነግ ሰራዊት #በመስቀል አደባባይ ልዩ ኣቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡

በአቀባበል ስነስርኣቱ ላይ የኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ #በብዛት ይሳተፋል ብሏል ኮሚቴው፡፡

#ኦነግ በቻርተር ጊዜ የተዘጋብኝን #ጉላሌ ያለውን ቢሮዬን ኣድሼ መቀመጫዬን አዲስ አበባ ኣደርጋለሁ ብሏል፡፡

ከሌሎች የኦሮሞ ፖሊትካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው ገልፆ፤ ከኦሮሞ ፌዴራልስት ኮንግረስ ጋር #ጥምረት ለመፍጠር ውይይት ላይ ነኝ ብሏል፡፡

©OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር የሆኑት ፕሮፌሰር #ብርሀኑ_ነጋ እና አቶ #አንዳርጋቸው_ፅጌ አዲስ አበባ ገብተዋል።

©ECADF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETV Zena Live! የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች መግልጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia