TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " - ፕ/ር መስፍን አርአያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

አሁንም " ወደ ምክክር መድረኩ ኑ " ያለው ኮሚሽኑ ፤ ለታጠቁ አካላት ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና በኮሚሽኑ እንደሚያመቻች ገልጿል።

ይህ የተሰማው በምክክር ጉባዔው የሚሳተፉ የኦሮሚያ ክልል ማህበረሰብ ተወካዮች የማጠቃለያ ልየታ መድረክ በሻሸመኔ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።

" በትጥቅ ትግል ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ #ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " ያሉት ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ " የሚያዋጣን ይሄ ነው ፤ በየታች ድረስ ሄደን ያገኘነው ህዝባችን ሰላምን እንደሚፈልግ ነው የገለጸለን  " ብለዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ሒሩት ገብረስላሴ በበኩላቸው ፥ እንዲህ አይነት ምክክር ትልቅ ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል።

" ይህን አጋጣሚ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ሊጠቀሙበት ይገባል " ብለዋል።

" በተለይ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ አካላት ወደ መድረኩ ሊመጡና ሀሳባቸውን ሊገልጹ ይገባል ፤ እነሱ መጥተው በሚሳተፉበት ጊዜ ኮሚሽኑ ተገቢውን #የዋስትና_ጥበቃ /safe space/ የሚያመቻች ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዶቼቨለ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia