TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ትምህርት ሚኒስቴር⬇️

ኢትዮጵያ ለ12 አመታት የምትሰራበት የትምህርት ፍኖተ ካርታ ረቂቅ ለህዝብ ውይይት ሊቀርብ ነው ተብሏል፡፡

የትምህርት ፍኖተ ካርታው ባለፉት ሁለት አመታት ጥናት ሲደረግበት መቆየቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር #ጥላዬ_ጌቴ ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ ፍኖተ ካርታው ላይ ለመወያየት በዘርፋ ላይ የተሰማሩ ከ1 ሺ 300 በላይ ባለ ድርሻዎች መጋበዛቸውንም ተሰምቷል፡፡

ውይይቱም ከነሐሴ 14-18 2010 ዓ/ም ይቆያል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ትምህርት ለ12 አመታት የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ውይይት መክፈቻ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንደሚሆን ዶር ጥላዬ ጌቴ አሳውቀዋል።

©ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትምህርት ሚኒስቴር⬇️

የትምህርት ፎኖተ ካርታው የመወያያ ረቂቅ ሠነድ እንጂ ፖሊሲ ሆኖ አልጸደቀም አለ ትምህርት ሚኒስቴር፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ረቂቅ የጥናት ሠነድ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እያወያየ ነው፡፡

ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉትን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሄ ሰጭ ሀሳቦችን ማቅረብ ነው የውይይቱ ዓላማ፡፡

ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ ለአ.ብ.መ.ድ እንደተናገሩት ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ተደርጎ በማህበራዊ ድረ ገጾች የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡ እንደ ሚኒስትሩ መረጃ በተጠናው ረቂቅ ሠነድ ላይ እየተመከረ እንጂ ድምዳሜ ላይ ተደርሶ ይፋ የተደረገ መረጃ የለም፡፡

ረቂቁ የትምህርትና ሥልጠና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ፣ አግባብነትና ጥራትን እንዲያረጋግጥ ታስቦ ነው እየተመከረበት ያለው፡፡

©አ.ብ.መ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት⬇️

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከሰቱ #የጸጥታ ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል እንዲቻል በአገር አቀፍ ደረጃ ህዝባዊ ውይይት እንደሚካሄድ የትምህርት ሚንስትር ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላማዊና ደህንነታቸው የተረጋገጠ ለማድረግ ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር መወያየታቸውንም አክለዋል።

ባለፈው የትምህርት ዘመን በተወሰኑ የመንግስት የከፍተኛ ተቋማት በተነሱ #ግርግሮች ምክንያት የሰው ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ ይታወሳል።

የትምህርት ሚንስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በተለይ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥቅምት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ህዝባዊ #ውይይት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይካሄዳል።

“በትምህርት ተቋማት ውስጥ የተማሪዎች ዋነኛ ተግባር መማርና መመራመር ነው” ያሉት ሚንስትሩ፤ መንግስት ተቋማቱ ከማንኛውም የጸጥታ ችግር ነጻ ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ ከመቸውም ጊዜ በላይ አበክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ጎን ለጎን የጸጥታ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እና ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ስለ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጸጥታ ችግሮችና #መፍትሄዎቻቸው መወያየታቸውንም
አውስተዋል።

ይህም መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት መስጠቱን እንደሚያሳይ ገልጸው፤ ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚቀላቀሉ ተማሪዎች ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ከመመለሳቸው በፊት ውይይት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደው ውይይት በርካታ ጠቃሚ ግብአቶች የተገኙበት እንደነበረ ጠቁመዋል።

በቅርቡ ፍኖተ ካርታውን በተመለከተ “የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት ትልቅ ህዝባዊ ውይይት በአዳማ ከተማ ይዘጋጃል” ብለዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት የተገኙ ግብዓቶችን በማካተት ፍኖተ ካርታው እንደሚሻሻልም ገልጸዋል።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መግቢያ ያሟሉ 149 ሺህ ተማሪዎች በተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውን ከትምህርት ሚንስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር‼️

ትምህርት ሚኒስቴር ነገ #በፍኖተ_ካርታው ዝግጅት ዙሪያ ጋዜጣዊ #መግለጫ ይሰጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ለቀጣዮቹ 15 ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን አጠቃላይ የትምህርት ፍኖተ ካርታ እያዘጋጀ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተገልጧል፡፡

የፍኖተ ካርታው ዝግጅት ለሚመለከታቸው አካላት በየደረጃው ለውይይት ቀርቦ ግብዓት እንደተሰጠበት ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የፍኖተ ካርታው ዝግጅት የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት ነገ በትምህርት ሚኒስትር የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 3፡00 ስዓት ጀምሮ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ውጤትን የተመለከተ መግለጫ!

የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስትሩ ሚኒስቴር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ምክትል ዳይሬክተሮች ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ እና አቶ መሳይ ደምሴ፣ እንዲሁም የየክልሎች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ጋረደው የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ቶላ ባሪሶ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ይልቃል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተከታታይ #ውጤቱን በተመለከተ በጋራ በተላለፈው #ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁም መሰረት በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያጋጠመ ችግር መኖሩን በተለይ በደንብ ጥሰት ዙሪያ #በማረጋገጫ የተያዘባቸው ተማሪዎች ውጤት መሰረዙ እና በደንብ ጥሰቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በየደረጃው ተጠያቂ የሆኑበት ሁኔታን እንዳለ ሆኖ፤ ፈተናዎቹ ከሰጡባቸው ቀናት ሀሙስና አርብ ማለትም በ6 እና 7/10/2011ዓ.ም ከተሰጡት ፈተና ውጤቶች በተለየ ከቅዳሜና እሁድ በኋላ ሰኞ እና ማክሰኞ ማለትም በ10 እና 11 10/2011ዓ.ም በተሰጡት ፈተናዎች በግልጽ የታየ የውጤት ግሽበት መኖሩ በመረጋገጡ የዩንቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥቡ በአራቱ የትምህርት ዓይነቶች ላይ መሰረት ያደረገ እንደሚሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ እነዚህም እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ፊዚክስ ለተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆኑ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ጂኦግራፊ ለማህበራዊ ሳይንስ ይሆናሉ፡፡

ይህም ሲሆን ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ሊገነዘቡ የሚገባቸው ተማሪዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመምህርነት ሙያ ለመማር ከመረጡ ተማሪዎች ውጪ ለዩንቨርስቲ መግቢያ ብቻ የሚያገለግልና የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ተብለው ዩንቨርስቲ እንደሚገቡና ከአንድ ዓመት የፍሬሽማን ኮርሶች በኋላም በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት የፈለጉትን የትምህርት ፊልድ መርጠው መማር የሚችሉ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የተከሰተውን #ግሽበት በተመለከተም የማጣራት ሂደቱን የሚያካሂድ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሆነ ኮሚቴ መቋቋሙን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ያሳወቁ ሲሆን ተጠያቂው አካል አስተማሪና የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

በመግለጫው ማጠቃለያም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ እንደገለጹት የመቁረጫ ነጥቡን በተመለከተ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች የተፈተኑ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የሚታይላቸው መሆኑንና በጥቂት ቀናት ውስጥ በኤጀንሲው የሚገለጽ መሆኑን እንዲሁም በታየው የውጤት ግሽበት ምክንያት የተያዙት የተማሪዎች ውጤቶች #እንደሚለቀቅ ጨምረው አሳውቀዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች መካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በመመዘኛነት የማያገለግሉ ውጤቶች፦

በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•ባዮሎጂ፣
•ኬሚስትሪ እና ስነ-ዜጋ (Civics) ፈተናዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመቀላቀል በመመዘኛነት #አያገለግሉም

በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•የታሪክ (History)፤
•ኤኮኖሚክስ እና ስነ-ዜጋ ፈተናዎች ውጤቶች #ውድቅ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዘሪሁን ዱሬሳ (ዶ/ር) እንዳሉት ባለፈው ሰኔ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመቀጠል በእንግሊዘኛ፣ ሒሳብ እና አፕቲቲዩድ ውጤቶቻቸው ይለካሉ።

ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ፊዚክስ፣ ከማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ የጂኦግራፊ ፈተናዎች ለመመዘኛነት ተመርጠዋል።

ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ «ተማሪዎችንም ፍትኃዊ በሆነ መልክ ሊያወዳድር እና ከእነሱ ችሎታ ባሻገር ምንም መበላለጥን ሊያስከትል የማይችል ሆኖ ስላገኘንው እነዚህን ተጠቅመን ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ መመደብ እና የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት ወስነናል» ብለዋል።

ከ322 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከሰኔ 6 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የተቀመጡበት ይኸው ፈተና ችግር እንደነበረበት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚዓብሔር «ሰኔ 6 እና 7 የተፈተኑት ፈተና ትክክለኛ ይዘት አለው። ሰኔ 10 እና 12 [የተፈተኑት ፈተናዎች ውጤት] ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ሲታይ የመጨመር ባሕሪ ሲያሳይ የተወሰነ ቦታ ላይ ግን ከሚጠበቀው በላይ ጋሽቦ ሔዷል» ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ «መቁረጫ ነጥቡ የት ይሆናል የሚለውን ኤጀንሲው ለተማሪዎች እና ለወላጆች፤ ለዩኒቨርሲቲዎች ግልፅ የሚያደርግ ይሆናል» ብለዋል።

የመንግሥት ባለስልጣናቱ ውሳኔ ቀድሞም ቀውስ ውስጥ በገባው የትምህርት ዘርፍ ተጨማሪ የውዝግብ መነሾ ሆኗል። ለመመዘኛነት አያገለግሉም ተብለው ውድቅ የተደረጉት የፈተና ውጤቶች ችግሮች ምንድናቸው? በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምን አይነት ችግሮች ተፈጠሩ? #ተጠያቂውስ ማነው ለሚሉ ጥያቄዎች ባለሥልጣናቱ በግልፅ የሰጡት ማብራሪያ ባይኖርም ጉዳዩ ጠቅላይ ምኒስትሩ በሚመሩት አጣሪ ኮሚቴ ጉዳዩ ይመረመራል ተብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia