TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዱራሜ‼️

በደቡብ ክልል በዜጎች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ሞትና መፈናቃል ያሳቆጣቸው #የዱራሜ_ከተማ ነዋሪዎች አደባባይ መዉጣታቸዉ ተነገረ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ዛሬ በከተማው ስታዲየም በመሰባሰብ መንግሥት የዜጎችን በህይወት የመኖር ህገ መንግሥታዊ መብት ሊያስከብር ይገባል ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ሠልፈኞቹ በቅርቡ ከከፋ ዞን ዴቻ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የሞት አደጋ የደረሰባቸው ነዋሪዎችን ለማሰብ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ያካሄዱ ሲሆን ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ቤተሰቦችም የገንዘብ ፤ የቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።

የሰልፉ አስተባባሪ አቶ #ደሳለኝ_ዳለሎ በሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች በዋናነት ሁለት መሠረታዊ መልዕክቶችን ያስተላለፉበት ነው ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

በደቡብ ክልል #ከፋ_ዞን ዴቻ ወረዳ ታጣቂዎች በሰፈራ መንደር በተሰባሰቡ የከምባታ ማህበረሰብ አባላት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በማድረስ ላይ እንደሚገኙ የከንባታ ጠንባሮ ዞን መስተዳድር ማስታወቁ አይዘነጋም። እስከአሁን በጥቃቱ 32 ሰዎች ሲሞቱ ከ 35 ሺህ በላይ የሚሆኑት መፈናቀላቸው ይታወቃል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

እናስተውል!

/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

አሁን ላይ ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ በእርግጥ በጣም ወደ #ከፋ ሌላ መንገድ ሊወስደን እንደሚችል በዚህ ወቅት መገንዘብ ካልቻልን ችግር ውስጥ ነን። #የመበታተን እና #የመጠፋፋት ምልክቶች እያየን ነው። ቤተሰብ ያለው ስለቤተሰቡ ያስብ፣ ሀገሩን የሚወድ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨንቀው፣ ህይወቱን የሚወድም እንዴት እሆናለው ብሎ ያሰላስል።

በስሜታዊነት እና በደመ ነፍስ የሚደረጉ ድርጊቶች እና የሚወሩ ጉዳዮች እዚህ አድርሰውናል። እነዚህ ነገሮች አሁኑኑ ካልተገቱ ሀገራችንን በምናውቃት መልኩ #በቅርቡ ላናገኛት እንችላለን።

ፖለቲከኞች ህዝብ ላይ #አትቆምሩ፣ ህዝቤ ፖለቲካ ቀነስ አርገህ ስራህ ላይ አተኩር፣ አክቲቪስቶች አደብ ግዙ፣ እኔን ጨምሮ ጋዜጠኞች ለማንም ሳንወግን ስራችንን እንስራ።

አሜን!

/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

ሰላም ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!!

🗞ቀን ሃምሌ 8/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia