TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢንጂነር ታከለ ኡማ⬇️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጀነር ታከለ ኡማ #በጎርፍ አደጋው ተከትሎ ህዝቡና ተቋማት ላደረጉት ህይወት የመታደግ ርብርብ #ምስጋና አቀረቡ፡፡

በአቃቂ ክፍለከተማ የደረሰው የጎርፍ አደጋ እጅግ ከባድና አሳዛኝ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ሆኖም ግን በክቡራን ወገኖቻችን ህይወት ላይ ምንም አይነት የህይወት አደጋ አለመድረሱ ለሁላችንም እፎይታ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ክቡሩን የወገንን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ላደረጉት የኢ.ፌ.ድ.ሪ የአየር ሀይል፤ የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት፤ ለአዲስ አበባ አሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠር ባለስልጣን፤ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽንና ከምንም በላይ ደግሞ ለአከባቢው ነዋሪና ህብረተሰብ ያላቸውን ጥልቅ የሆነ አክብሮትና ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ኢንጀነር ታከለ እንደ አስተዳደር ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳይከሰቱ የጥንቃቄና የመፍትሄ እርምጃዎችን ጨምሮ የከተማውን የወንዝና ተፋሰስ ስራዎችን #በማልማት ከችግር ምንጭነት ይልቅ የከተማው የውበት ምንጭ እንዲሆኑ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia