TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ታማኝ በየነ⬇️

ለአርቲስት #ታማኝ_በየነ የሚደረገው አቀባበል በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ጠየቀ።

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ቅዳሜ #ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ጠዋት 1 ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የኃይማኖት አባቶች አቀባበል ያደርጉለታል።

የኮሚቴው አባል አቶ #የሺዋስ_አሰፋ እንደተናገሩት በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ ከመንግሥት የፀጥታ አካላት በተጨማሪ ኀብረተሰቡ ራሱንና አካባቢውን በመጠበቅ የአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የዜግነት ግዴታ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ በበኩላቸው የተለያዩ ዝግጅቶች የሚካሄዱ ሲሆን በዕለቱ ትያትር ቤቶች የባህል ሙዚቃና ውዝዋዜ ያቀርባሉ፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባለው ልዩ የእንግዳ ማረፊያም ታማኝ በየነ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየረ ማረፊያ እስከ ብሄራዊ ትያትር ቤት ድረስ አድናቂና ደጋፊዎቹ የአዲስ አበባና የተለያዩ አካባቢ ሰዎች በሰላማዊ ህዝባዊ ትዕይንት አቀባበል ያደርጉለታል ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል።

በብሄራዊ ትያትር ቤት ጥሪ የተደረገላቸው ከ1 ሺህ በላይ እንግዶች በተገኙበት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እንደሚቀርቡም ገልጸዋል።

እሁድ ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ከተለያዩ ዘርፎች የተመረጡ ሰዎች ንግግር ያደርጋሉ፤ አርቲስት ታማኝ በየነም የምስጋናና አጠቃላይ መልዕክት ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖረው ዝግጅት 25 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአርቲስቶችን ፍቅር፣ ተስፋ እንዲሁም አንድነትን የሚያበስሩ የጥበብ ሥራዎች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ወደ አሜሪካ ‘ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ’ በሚል መርህ ተጉዘው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የአርቲስት ታማኝ በየነ ወደ አገር ውስጥ መግባት የድልድዩን መጠናከር የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ታምራት ገለታ⬆️

”ባለአውሊያ” እና ”ባለከራማ” ነኝ በማለት ከአሥር ዓመት በላይ በጥንቆላ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው አቶ ታምራት ገለታ #ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ”ጥፋተኛ” ብሎ ንብረቶቹም ተወርሰው ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ መወሰኑ የሚታወስ ነው

በአንድ ወቅት እጅግ አነጋጋሪ የነበሩት ከጥንቆላ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ለእስር የተዳረጉት አቶ ታምራት ገለታ ባሳለፍነው ሳምንት በምህረት መለቀቃቸውን ካፒታል የእንግሊዘኛው ጋዜጣ ዘግቦታል።

©ድሬትዩብ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ 📈 ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ 👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም 👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም 👉 ከባድ…
#ነዳጅ

ከነገ #ሐምሌ_23 ቀን 2014 ዓ.ም - #ነሐሴ_30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የአውሮፕላን ነዳጅን በሚመለከት ግን በወቅታዊ የዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ በመጣው አዲስ አበባ ላይ በሊትር 84 ብር ከ42 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑንም ገልጿል።

ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ የአሠራር ሥርዓት በነሐሴ ወር በተመሳሳይ እንደሚቀጥልም የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ተመዝገቡ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፤ የሃይማኖት ድርጅቶች አስተምህሮታቸውን በመገናኛ ብዙኃን እንዲያደርሱ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከሰኔ 27/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ማንኛውም የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ እስከ #ነሐሴ_13_ቀን_2014 ዓ.ም ድረስ https://www.eservices.gov.et/ በሚለው ፖርታል ውስጥ በመግባት ወይም #በአካል_በመቅረብ ማመልከትና ፈቃድ መውስድ እንዳለበት ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

Via @EthMediaAuth