TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን በስራ ማቆም #አድማ ላይ ለሚገኙት #ሰራተኞች በነሀሴ 24 እንዲፈርሙ አቅርቦላቸው የነበረው #የይቅርታ ፎርም ከላይ የምትመለከቱትን ይመስላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገ-ወጥ ንግድ⁉️

በቦሌ አየር መንገድ ተቀጥረው የሚሰሩ አንዳንድ #ሰራተኞች ያላቸውን ነፃ ቲኬት በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት በሚመላለሱበት ወቅት ህገወጥ ንግድ ውስጥ ገብተዋል ተባለ፡፡

ይህ የተገለጸው በዛሬው እለት ክብርት የገቢዎች ሚንስትር ወ/ሮ #አዳነች_አቤቤ በቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተው የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ከአየር መንገዱ የስራ ሃላፊዎች ጋር በነበራቸው ውይይት እንደተገለጸው አንዳንድ የአየር መንገዱ ሰራተኞች በሳምንት ከአራት እስከ አምስት ጊዜ ያህል ወደ ዱባይ፤ ታይላንድ እና ቻይና በማቅናት የተለያዩ የንግድ እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት እየነገዱ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ሌሎች ህጋዊ ነጋዴዎች ለስራችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው ሲሉ ቅሬታ አሰምቷል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ይህ አይነቱ ድርጊት የአየር መንገዱን አለም አቀፋዊ መልካም ገጽታ የሚያጠፋ እና ህገወጥ ድርጊት ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም እንደዚህ አይነት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን ደረጃ በደረጃ ተጠያቂ የማድረጉ ስራ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም እነዚህን እና ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመናበብ እና በቅንጅት መስራት
እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሔሊኮፕተር ተከሰከሰ‼️

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን አቢዬ ግዛት #ተከስክሶ ሶስት ሰዎች ሞቱ። በአደጋው የሞቱት #ሶስት ሰዎች የሔሊኮፕተሩ የበረራ #ሰራተኞች ናቸው። ከቆሰሉ ስምንት ተሳፋሪዎች ሶስቱ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

የምዝገባ ቁጥሩ UNO 379P የሆነው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል (UNISFA) ቅጥር ግቢ ውስጥ በተከሰከሰበት ቅፅበት 23 መንገደኞች ጭኖ ነበር። የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል እንዳስታወቀው ኤምአይ ስምንት (MI-8) የተባለው ሔሊኮፕተር በተከሰከሰበት ቅፅበት ካዱግሊ ከተባለ ቦታ ወደ አቢዬ በመቀየር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች አሳፍሮ ነበር። 

በአደጋው ስምንት መንገደኞች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሶስቱ በአስጊ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአስጊ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙት ተሳፋሪዎች በካዱግሊ በኩል ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውንም አክሎ ገልጿል። በመግለጫው መሠረት ቀሪዎቹ አምስት መንገደኞች በአቢዬ በሚገኝ ሆስፒታል እገዛ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ሔሊኮፕተሩን ለመከስከስ ያበቃው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሐና ጉዳዩ እየተመረመረ መሆኑን ተናግረዋል። "ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተፈጠረው ክስተት እጅግ አዝነናል። በአደጋው ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን" ብለዋል ሜጀር ጄኔራል ገብሬ። 

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር የተከሰከሰው መደበኛ የወታደሮች ዝውውር መርኃ-ግብር ተሰማርቶ በነበረበት ወቅት መሆኑን የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ያወጣው መግለጫ አትቷል። ለተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ወታደሮች #በብቸኝነት ያዋጣቸው ኢትዮጵያ 4,500 አባላት ያሉትን ኃይል አሰማርታለች።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፍቅር #ጉዟችንን በተመለከተ...

በTIKVAH-ETH በኩል #የተሰባሰቡት ወጣቶች ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የተውጣጡ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ቀለም የያዙ ናቸው። ሁሉም ወጣቶች እናት ሀገራቸውን የሚወዱ እና በሀገሪቱ ላይ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ከሳምንት እስከ ሳምንት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ፤ የትምህርት እና የግል ጊዜያቸውን ትተው ለሰላምና ፍቅር የሚጓዙ ናቸው። ለዚህም ሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ #ሊያመሰግናቸው ይገባል።

ዩኒቨርስቲዎችን በተመለከተ፦

#StopHateSpeech በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄድ ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ ከተማሪዎች ጋር የሚደረግ #ውይይት እና #ንግግር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ነው። ምክንያቱም ወጣቶች ከጥላቻ እና ከስሜታዊነት ርቀው ሀገር መገንባትና ለህዝብም #ተስፋ የሚሰጡ ዜጎች እንደሆኑ ማስመስከር ስለምንፈልግ ነው።

ይህ ጉዞ እና እንቅስቃሴ ከየትኛውም አይነት የፖለቲካ አመለካከት ነፃ የሆነ፤ ከየትኛውም ድርጅትም ሆነ ቡድን ገለልተኛ የሆነ በወጣቶች የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ወጣቶቹም ትክክለኛ የሀገሪቱን ቅርፅ የያዙ በፍቅር እና በንግግር የሚያምኑ ሀገሪቷን ከጥላቻ አላቀው ትልቅ ሀገር የመገንባት ህልም ያላቸው ናቸው።

√ወጣቶቹ የሰላምን አርማ ይዘው በየሄዱበት የሚሰብኩት ስለፍቅር እና መተባበር እና መተጋገዝ ብቻ ነው። በሚዘጋጁት መድረኮችም የጥላቻ መዘዞችን ማስገንዘብ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸውን እንዲያሻሽሉ ማስገንዘብ ነው።

√ውይይቶች በጠቅላላ የሚደረጉት #በወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች #መካከል ብቻ ነው። ሌላው ተናጋሪዎች ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው አካላት ብቻ ናቸው።

በቀጣይ ምዕራፍ 2፦ ከዩኒቨርሲቲ #አመራሮች እና #ሰራተኞች ጋር ተመሳሳይ መድረክ ይኖረናል።

ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ #ሰራተኞች የእድገት መሰላልና የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ ተደረገ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia