TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ? ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው…
#ትግራይ #አማራ

" እኔ #ከሪፈረንደም ውጭ መፍትሄ ያለ አይመስለኝም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትግራይ እና አማራ በኩል ላለው ችግር " ዘላቂው መፍትሄ ህዝባዊ ሪፈረንደም " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅለይ ሚኒስትሩ ፥ ከዚህ ቀደምም በትግራይ እና አማራ ላለው ችግር ዘላቂ መፍትሄ " ህዝቡ ህዝበ ውሳኔ ሲያደርግ " እንደሆነ በተደጋጋሚ እንደተናገሩት ጠቁመዋል።

" የሆነን ሰዎች እዛ ተቀምጠው ፣ እዛ ተቀምጠው ሲናገሩ አይደለም። ህዝቡን መልሰን ህጋዊ በሆነ መንገድ ዓለም እያየው ሪፈረንደም አድርገው ወደሚፈልጉት ቢጠቃለሉ ከዚያ በኃላ ለጥያቄ አይመችም " ብለዋል።

" አሁን ላይ ግን ሪፈረንደም የሚባል ነገር አይፈልገም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " እራሱ ነዋሪው ሳይሆን ሌላ ሰው ነው መወሰን የሚፈልገው እዚህ እየመጣ ጥያቄ ያቀርባል ' አልተፈታም ' እያለ እኔ ደግሞ አቅጣጫ አስቀምጫለሁ እንዲፈታ " ሲሉ ተናግረዋል።

እሳቸው ያስቀመጡት አቅጣጫ በመጀመሪያ የተፈናቀውለው ህዝብ እንዲመለስ ከዛ ህዝቡ እንዲወስን (ሪፈረንደም እንዲያደርግ) መሆኑን ተናግረዋል።

" ሪፈረንደም ከተደረገ በኃላ ህዝቡ የወሰነውን እናክብርለት ፤ እኔ እዚህ ሆኜ መወሰን አልችልም " ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ " በትግራይ በኩል ስናነጋግር ያለው ናሬሽን እና በአማራ በኩል ስናነጋግር ያለው ናሬሽን በጣም የተራራቀ ነው ምንም የተቀራረበ አይደለም ለማቀራረብ የሚቻለው ህዝቡ እራሱ ሲወስን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ (ሪፈረንደም) ውጭ ለጊዜው ሌላ #መፍትሄ ያለ እንደማይመስላቸውም ገልጸዋል።

" ህዝቡ እንዲወስን ከተደረገ የተረጋጋ አካባቢ ይፈጠራል " ብለዋል።

" እያባላን ያለው የቦታ ችግር አይደለም እኛን የሚያባላን እንደ ንብ ቀፎ ውስጣችን የሚጮኸው ጩኸት ነው እንጂ ሀገሩማ በቂ ነው ቢሰራበት ቦታዎቹ ክፍት ናቸው መንገድ የላቸው ፣ ቤት የላቸው ክፍት ናቸው ' አልገባሁም ገባሁ ' እንጨቃጨካለን እንጂ የቦታ ችግር የለም ቦታው ላይ የሚስራት ችግር ነው የሚያጨቃጭቀን " ብለዋል።

@tikvahethiopia