TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ ሥራ አጦች📈

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አጦች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።

በመዲናዋ የሥራ አጦች ቁጥር በመቶኛ እየጨመረ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱትሪ ልማት ቢሮ የሥራ ዕድልና የሥነ ምግብ ዋስት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ ሰምቷል።

ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ እንዲያስረዱ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው ተከታዮችን ነጥቦች አንስተዋል።

- ሥራ አጡ በጣም ሰፊ ነው።

- አዲስ አበባ የአገሪቱ ዋና ከተማ እደመሆኗ መጠንና አጎራባች አካባቢ ካለው የጸጥታ ችግርም አንፃር በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወደ ከተማ ውስጥ በሰፊው የሚገቡ አሉ። እዚህም የከተማውን ማህበረሰብ ከሥራ ዕድልም አንፃር የሚሻሙ ናቸው።

- የከተማው ወጣት አለ። የከተማው ሥራ አጥ የሥራ ዕድል በጥራትም በስፋት እዲፈጠርለት ይፈልጋል፤ በዚህ መካከል እኛ መፍጠር የምንችለው የሥራ እድል እና ከተማ ውስጥ ያለው የሥራ አጦች ቁጥር አይጣጣምም።

- የራሱ የከተማው ነዋሪ አለ፣ በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማ ውስጥ የሚገባም አለ። እነዚህን ሁለቱን አጣጥሞ የሚጠበቀውን ያክል የሥራ ዕድል መፍጠር በጣም ፈታኝ ነው።

- የሥራ አጥ ቁጥሩ አምና ስንጀምር ስብጥሩ በጣም ዝቅተኛ ነበር። ወደ 17 በመቶ አካባቢ የነበረው አሁን አድጎ ወደ 22 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል የሥራ አጥ ቁጥር ምጣኔው።

- እኛ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ወደ አንድ ድርጅት እናወርዳለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን እየጨመረ ነው የሚያሳየው። የዚህ መጨመር ምክንያቱ የተለያየ ቢሆንም አንደኛው ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ያለመቻልን ያሳያል።

- እኛ እየፈጠርን ያለነውና የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚገባው ሥራ አጥ ቁጥሩ ሰፊ ነው ይሄ አልተመጣጠነም።

- የሰው ሀይላችን እስኪልድ ማን ፓወር አይደለም በጣም የሰለጠነ ብቁ ሞያተኛ የሆነ የሰው ሀይል እጃችን ላይ የለም።

-  የሰው ሀይላችን ሥራ አጡ በተለይ የትምህርት ደረጃው ዝቅተኛ ነው፤ ይህን ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ያለው የሰው ኃይል አሰልጥኖ የክህሎትና የሙያ ባለቤት አድርጎ ወደ ኢንስትሪዎቹ ማስተሳሰርን ይጠይቃል።

በሌላ በኩል ፤ ሥራ ያገኙ ሰዎች ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎች የሚከፈላቸው #ደመወዝ_በጣም_አነስተኛ በመሆኑ የቤትና ኪራይና አስቤዛ እንኳ ማሟላት እንደማይችል በተደጋጋሚ ቢገልጹም መፍትሄ እያገኙ እንዳልሆነ፣ ሥራ አጥ የሆኑትም የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ይደመጣል።

ይህንን በተመለከተ አቶ ፍስሃ ምን አሉ ?

" ኢንዱስትሪዎቹ የሚከፍሉት ደመወዝ ዝቅተኛ ነው የእነርሱ ምክንያት ደግሞ እምታቀርቧቸው ሰዎች ሙያቸው ከዚህ በላይ አያስከፍልም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ "  ብለዋል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ማብራሪያ ያገኘው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር  ልህቀት አካዳሚ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ለተገኙት አቶ ፍስሃ ጥበቡ ጥያቄ አቅርቦ ነው)

ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia