TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጋሞ ጎፋ ዞን⬇️

በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራያና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሀገራችን ታዋቂ አርቲስቶች ስላደረጉት ድጋፍ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር ምስጋና አቀረበ፡፡ አርቲስት #ቴዎድሮስ_ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/፣ አርቲስት #ታማኝ_በየነ እና አርቲስት #አስገኘው_አሽኮ/አስጌ ደንዳሾ/ በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ
ልዩ ዞን ቡራያና አካባቢው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ተጎጂዎችን በመጠለያ ተገኝተው ስላጽናኑና ስለረዷቸው በጋሞ ጎፋ ዞን ሕዝብ
ስም አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል...

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት በአርባምንጭ ከተማ እና አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ከሚገኙ አድባራት እንዲሁም ከማህበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ዙሪያ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራያና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች 200 ሺህ ብር በማሰባሰብ #ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ምንጭ፦ የጋሞ ጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia