#ማስታወሻ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።
ከተሰጠው ቀነ ገደብ በኋላ መረጃዎችን ያልሰጡ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ አይችሉም።
ባንኮች ባለፉት 6 ወራት መመርያው በሚጠይቀው መሥፈርት መሠረት የደንበኞቻቸውን መረጃ እየሰበሰቡ ነው፡፡
ይህንኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ተከትለው ደንበኞቻቸው በግንባር ወደ ባንክ ቀርበው በመመርያው መሠረት አስፈላጊ መረጃ እንዲሰጡ እያደረጉ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ ደንበኞች በመመርያው መሠረት ወደ ባንክ በመሄድ መረጃ እየሰጡ አይደለም ተብሏል።
በዚሁ የቀነገደቡ ማብቂያ ሳምብት ባንኮች በስልክ ጭምር እያስተናገዱ ነው።
ባንኮች መረጃ ሰብስበው እንዲያጠናቅቁ የተሰጣቸው ጊዜ የሚጠናቀቀው የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲሆን ከየካቲት 21 ቀን 2014 በኋላ መረጃዎቻቸውን ለባንክ ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ አይችሉም።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ [NBE] የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር አያሌው መረጃቸውን ባለመስጠት አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ የሚደረጉት ደንበኞች አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉት በአዲሱ አሠራር መሠረት በመመርያው የተቀመጠውን መረጃ ሲሰጡ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የባንክ ኃላፊዎች በተለይ #ቼክ የሚያንቀሳቅሱ የባንክ ደንበኞች፣ በብሔራዊ ባንክ ድንጋጌ መሰረት መረጃውን ቀርበው ካልሞሉና በዚሁ ምክንያት አካውንታቸው የማይንቀሳቀስ ከሆነ ይከፈል ያሉት ቼክ የማይከፈል መሆን ጋፀው ለማይቀረው ነገር በቶሎ የሚፈለግባቸውን ይሙሉ ማለታቸውን ሪፖርተር አስነብቧል።
ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-02-25
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል። ከተሰጠው ቀነ ገደብ በኋላ መረጃዎችን ያልሰጡ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ አይችሉም። ባንኮች ባለፉት 6 ወራት መመርያው በሚጠይቀው መሥፈርት መሠረት የደንበኞቻቸውን መረጃ እየሰበሰቡ ነው፡፡ ይህንኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ተከትለው…
#NBE
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2014 ተጠናቋል።
መረጃዎችን ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ሆነዋል (በሚሊዮን ሊቆጠሩ ናቸው ተብሎ ይታመናል) ፤ አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉትም በመመሪያው መሰረት መረጃ ሲሰጡ ብቻ ነው።
የ " መታወቂያ እድሳት " ግን እንቅፋት የሆነባቸው ብዙ ናቸው ለእነሱ የታሰበ ነገር ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።
ባንኮች ደንበኞቻቸው መረጃ እንዲሞሉ ላለፉት 6 ወራት ያህል በዋና ዋና ሚዲያዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ፣ በባንኮች የማስታወቂያ ቦርድ ላይ ጥሪ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን አንዳንድ ባንኮች በመጨረሻው ሳምንት በስልክ እየደወሉ ለመቀበል ጥረት አድርገዋል።
ከቀነገደቡ መጨረሻ በፊት የባንክ ኃላፊዎች በመመርያ የተደነገገውን ማስፈጸም ከባድ ሥራ በመሆኑ መረጃ የማሰባሰቡ ሥራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል የሚል አስተያየት ቢሰጡም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምላሽ ሳይሰጥ ጊዜው አልቋል።
በዚሁ አጋጣሚ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የግጭት ፣ የጥላቻ መልዕክቶች፣ ፌዝ ፣ ስድብ እና አሉታዊ ነገሮች ለብዙሃን በፍጥነት እና በብዛት ሼር ከማድረግ ይልቅ ወሳኝ ጠቃሚ መልዕክቶች የማጋራት ልምድና ኃላፊነት ሊጨምር ይገባል።
ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጠቃሚ መልዕክቶችን በአግባቡ ብናጋራ መረጃ ላልሰማው ወገናች እንዲሰማ እንዲሁም ደግሞ በመጨረሻ ቀናት ከሚፈጠር ወከባ ብዙ ሰዎችን መካከል ይቻላል።