TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አማራ ክልል⬇️

በአማራ ክልል በዚህ ዓመት በትራፊክ አደጋ የ1 ሺህ 1 መቶ ሀምሳ ሁለት(1152) ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ባለፈው አመት በክልሉ በታራፊክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ከጠፋ ሰዎች ቁጥር አንፃር የዘንድሮው በልጦ ተገኝቷል። ባለፈው ዓመት በትራፊክ አደጋ 1 ሺህ ዘጠና ስድስት(1096) ሰዎች ህይወታቸው ያለፈው፡፡

በሌላ በኩል⬇️

▪️በክልሉ በዚህ አመት 8 መቶ 57(857) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል። ባለፈው ዓመት ደግሞ 7መቶ 96(796) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል፡፡

የችግሩን አሳሳቢነት ለማሳወቅ ፣ ለመጠየቅ እና እውቅና ለመፍጠር ከህጻን እስከ አዋቂ የሚሳተፍበት #ሰልፍ ነገ በዋና ከተማዋ #ባህርዳር መዘጋጀቱን ከአማራ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በሴኔጋል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የሚሰጠውን "Royal Order of the Lion" የተሰኘውን የክብር ሽልማት ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

©etv
@tikvahethiopia @tsegabwolde
"ክፉ ሰው እንጂ ክፉ ብሄር የለም!"

~ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ~

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን እየታየ ያለው ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ “አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ መስዋዕትነት ከፍለዋል” ኢትዮጵያዊያን ዕውቅና ለመስጠት ሥራ መጀመሩን አንድ የሽልማት ድርጅት አስታውቋል።

ይህ ለውጥ እንዲመጣ ከሰባት ዓመት ሕፃን ልጅ እስከ አዛውንት ሕይወታቸውን ገብረዋል ያሉት የዕውቅናው ሥርዓት አዘጋጆች ዕውቅናው እነዚህንና በአመራር ላይ ያሉ ሰዎችንም እንደሚያካትት ገልፀዋል።

©VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️የቀድሞው #የኢህዴን መስራች እና ሊቀመንበር አቶ #ያሬድ_ጥበቡ በትላንትናው ዕለት ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል፡፡

ፎቶ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት የከዱ (የኮበለሉ) አባላት እና የፖሊስ አመራሮች መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን #ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጁ መሰረት እስከ ግንቦት 30/2010 ዓመተ ምህረት ድረስ ከሰራዊቱ የከዱ አባላትና አመራሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የኮበለሉት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ከነሀሴ መጨረሻ ጀምሮ በመጪዎቹ ስድስት ወራት በምህረት አዋጁ መሰረት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በኮሚሽኑ የህግ ጉዳይ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲል_አሻግሬ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ በከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ በፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች በመገኘት ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፥ በክልል የሚገኙት ደግሞ ለክልላቸው ፍትህ ቢሮ ሪፖርት በማድረግ በምህረቱ ተጠቃሚ መሆኑን እንደሚችሉ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ አባላት እና አመራሮች ከዚህ ቀደም የወሰዱትን ደብዳቤ ተመላሽ በማድረግ በምትኩ ሌላ የስንብት ደብዳቤና የስራ ልምድ ማግኘት እንደሚችሉ ታውቋል።

የምህረቱ ተጠቃሚ የሆኑ አባላት የወሰዱትን የመንግስት ንብረት ሪፖርት ለሚያደርጉበት ተቋም በመመለስ የነጻነት የምስክር ወረቀት መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።

ሆኖም በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ ፖሊሶች ወደ ስራ ቦታ እንደማይመለሱ የስራ አመራር ውሳኔ እንዳሳለፈ ኮማንደር ፋሲል አሻግሬ አስታውቀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahehiopia
#update የአንበሳ ግቢ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ #ሙሴ_ክፍሎም ከሀላፊነታቸው ተነሱ፡፡ ስራ አስኪያጁ ከዛሬ ጀምሮ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ በደብዳቤ የገለፁላቸው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ተከለ ኡማ መሆናቸውን ተሰምቷል፡፡

©sheger 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ ቴሌኮም⬇️

የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎችን ባሉበት ቦታ ሆነው ማስመዝገብ የሚያስችል አገልግሎት ስራ ላይ ማዋሉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በዚህም ደንበኞች ወደ ኢትዩ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላትም ሆነ ሌላ ቦታ #ሳይሄዱ ባሉበት ሆነዉ #ቀፎዎችን ማስመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል።

በመሆኑም ደንበኞች ማንኛውንም ቀፎ ገዝተው ከመጠቀማችሁ በፊት ሲም ካርድ በማስገባት መሞከርና መስራቱን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

የቀፎውን ሁኔታ ለማረጋገጥ ወደ *868# በመደወል እና 1ን በመጫን ቀጥሎም በቀፎ መለያ ቁጥር የሚለውን አማራጭ በመምረጥ የቀፎውን የቀፎ መለያ ቁጥር በማስገባት የተፈቀደ መሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ተጠንቀቁ⬇️

በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ ግዛት ውስጥ የሌላ አገር ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ኢትዮጰያውያን ራሳቸውን #እንዲጠብቁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ኤምባሲው ለዜጎቹ ድጋፍ እያደረገ ነው
በእስከአሁኑ ጥቃት አንድ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ ሲያልፍ አንድ ሌላ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ሃኪም ቤት እያገገመ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከአገሪቱ መንግስት ጋር በመሆን በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቆም እየሰራ እንደሚገኝም አመልክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ በአካባቢው ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

በፕሪቶሪያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ለሚፈልጉ በስልክ ቁጥሮች 0123462110፣0123462947 መረጃ ማግኘት እንደሚችሉም ገልጿዋል፡፡

ምንጭ፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia