አሳዛኝ ዜና📌በዛሬዉ ዕለት ከረፋዱ 5፡30 የመከላከያ አየር ሀይል ሄሊኮፍተር 14 #የመከላከያ ሰራዊታችን ባልደረቦች እና 3 ሲቪል ሰዎችን አሳፍሮ ከድሬዳዋ ቢሾፍቱ መብረር ላይ እያለ ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ኤጄሬ ቀበሌ ላይ ባጋጠመዉ መከስከስ አደጋ በበረራዉ ላይ የነበሩ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። የአደጋዉ መንስኤም በመጣራት ላይ ይገኛል።
📌በዚህ አደጋ ህይወታችዉን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መፅናናትን እንመኛለን።
©አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikahethiopia

ኢንጂነር አይሻ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አሕመድ ባዋቀሩት አዲስ የካቢኔ አባላት ውስጥ #የመከላከያ_ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ የሚባል ዜጋ የለም "ኢትዮጵያ ለሁሉም #እኩል የሆነች አገር ናት" ብለዋል። ይህ ደግሞ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋል እንደሌለበት ገልፀው፤ "ፖለቲከኛም፣ ጤነኛም ሆነ በሽተኛ መሆን የሚቻለው #አገር ስትኖር ነው" ብለዋል።
በየትኛውም ደረጃ ያለ ማንኛውም የመንግሥት አመራር ላይ ያለ ሰው ገለልተኛ መሆን እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ አይሻ፤ "ይህን ደግሞ በሚያንፀባርቁት ሐሳብም በድርጊትም ማሳየት ይገባቸዋል።"ብለዋል።
ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት(ፂዮን ግርማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

Audio
Alamata-Kobo-11-5-2018
በአላማጣ ከተማ ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የኢትዮጵያ ክልሎችን ከሚያገኛኙ አውራ መንገዶች አንዱ የሆነው የአላማጣ ቆቦ መስመር ዝግ ሆኖ ቆይቷል። ከትላንት በስትያ #የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ በመግባት መንገዱ እንዲከፈት ማድረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
©voa
@tsegabwolde
©voa
@tsegabwolde
ደምቢ ዶሎ🔝ላለፉት ወራት በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ወደ ቆየችው ደምቢ ዶሎ ከተማ #የመከላከያ_ሰራዊት የገባ ሲሆን፣ የሰራዊቱን መግባት የተቃወሙ ግለሰቦች መንገድ የመዝጋት ሙከራ ማድረጋቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። የብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት የሰላም ዕጦት በታየባቸው የምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የፌድራል ሀይሎች እንዲሰማሩ መወሰኑ ይታወቃል።
ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahevhethiopia
ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahevhethiopia
#Update ከኢትዮ ኤርትራ ድንበር የተንቀሳቀሱ #የመከላከያ_ሰራዊት አባላት በጎንደር በኩል ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሲሄዱ ማየታቸውን elu ከአይን እማኞች ተነግሮኛል ሲል ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️
#የመከላከያ_ሰራዊት መዋቅር #እንዲሻሻል ተደረገ ከአሁን ቀደም 6 የነበረው የእዝ ብዛት ወደ 4 ተቀንሷል።
4ቱ እዞች የምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ሰሜን ናቸው። #የባህር_ሀይልን የሚያደራጅ ኮሚቴና የልዩ ዘመቻ እዝ ተዋቅሯል።
ይህንንም መሰረት በማድረግ የአዳዲስ አመራር ምደባ መካሄዱን ዛሬ የልዩ ዘመቻ አዛዥ ሌቴናል ጄኔራል ሞላ ኃይለማርያም መግለጫ ሰጥተዋል።
via-fbc

#update በጊንቢ ከተማ ሁለት ወጣቶች #በታጠቀ ኃይል #መገደላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ከትላንት በስቲያ አንድ በጉልበት ሥራ የሚተዳደር ወጣት ሲገደል፣ ትላንት ደግሞ የአእምሮ ጤና እክል ያለበት ወጣት ተገድሏል፤ ይላሉ የዓይን እማኞች፡፡ ከትላንት በስቲያ እና ትላንት ከተማውማዋ በከፍተኛ የጦር መሣሪያ ድምፅ ስትታመስ መቆየቷን ነዋሪዎች ተናግረዋል፤ የአካባቢው ኮማንድ ፖስት በበኩሉ #የመከላከያ_ሰራዊት ማንንም አልገደለም ብሏል፡፡
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ መማክርት🔝
#የመከላከያ_መማክርት (ካውንስል) ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ውይይት አድርጓል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊት በሕጋዊ መዕቀፎች፣ በአደረጃጀት፣ በመፈጸም ብቃትና በትጥቅ ከፍተኛ የለውጥ ጎደና ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህንን ለውጥ በሁሉም ደረጃ ተፈጻሚ ከማድረግና ወደታች ከማውረድ አንፃር የተገኙ ተጨባጭ ውጤቶች፣ የታዩ ክፍተቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
ውይይቱን የመሩት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሲሆኑ፣ መከላከያ እስከሁን ያደረጋቸው የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎች ምን ያህል ርቀት እንደተጓዙ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
መከላከያ የአገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ቴክኖሎጂን የሚታጠቅ፣ በራሱ አቅም መጠገን፣ ማሳደግ ብሎም መፍጠር የሚችል እንዲሆን በርካታ የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡
መከላከያ ከቴክኖሎጂ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውና እንደ ሌሎች አገራት ከራሱም አልፎ ለሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ምንጭ መሆን የሚችል እንዲሆን ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ተገምግመዋል፡፡
መከላከያው በሁሉም ደረጃዎች የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ተዋጽኦ የጠበቀ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትም ተገምግመዋል፡፡
የአገሪቱን ውስጣዊና ካባቢያዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ የሰራዊት አሰፋፈር እንዲኖር የተጀመረው እንቅስቃሴ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም የመከላከያ ሰራዊት አሰፋፈር ወቅታዊ፣ ተጨባጭና ታሳቢ ስጋትን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚወናወን በመሆኑ ሕብረተሰቡም በዚህ መልኩ እንዲረዳው ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡
ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ድሬዳዋ‼️
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳሰበ፡፡
በድሬድዋ ከተማ ግጭት የተፈጠረው ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የጥምቀት ማግስት የቃና-ዘገሊላ በዓልን በሚያከብሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች በፈጠሩት ረብሻ ሳቢያ ነው፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን በስልክ ለአብመድ እንደተናገሩት በዕለቱ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ችግር በሁለት እና ሦስት ቀናት ወደ ተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ተስፋፍቷል፡፡
‹‹ሃይማኖታዊ በዓሉን በመረበሽ የድሬዳዋ ከተማን አንድነት መሸርሸር እና አገራዊ ሰላምን ለማደፍረስ ታስቦ የተሠራ ነው›› ብለዋል ከንቲባው፡፡ ግጭቱን ሃይማኖታዊ መልክ እንዲኖረው ለማድረግ ፀብ የማጫር ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ አካላት መኖራቸውንም ገልፀዋል፡፡ ከክብረ በዓሉ ቀደም ብለው ጭምር ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበርም ነው አቶ ኢብራሂም የጠቆሙት፡፡
ቀደም ብሎ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግም ሌላ የግጭት አጀንዳ እንደተነደፈ አስታውቀዋል፡፡ እንደ ከንቲባው ገለጻ ችግሩን የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የጎሳ እና የፖለቲካ መልክ ለማስያዝ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡
ሰላም በመደፍረሱ ምክንያት የዝርፊያ ወንጀሎች እየተባባሱ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡
በተለይ ወደ ባንኮች ተደራጂቶ የመሄድ አዝማሚያ መኖሩን፣ መንገድ የመዝጋት፣ የግለሰቦች ቤትና ንብረት የማውደም እና የተወሰኑ የመንግሥት ተቋማት ላይ ጉዳት የማድረስ ሁኔታዎች በከተማዋ መስተዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡
የከተማዋን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ‹‹ለዚህም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ ነው፡፡ ከግጭቱ ጀርባ ስውር አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ከ80 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ለሕግ የማቅረብ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ነው ያሉት ከንቲባው፡፡
‹‹ችግሩ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ #የመከላከያ_ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊሶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል›› ያሉት ከንቲባው ዛሬ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አስታውቀዋል፡፡
‹‹አንድ ስፍራ ብቻ አሁንም ችግሩ አለ፤ የፀጥታ ኃይሎች ሰላም ለማስከበር ወደ ስፍራው አቅንተው ሰላም የማስከበር ሥራ እየሠሩ ነው›› ብለዋል አቶ ኢብራሂም፡፡
ድርጊቱ የድሬዳዋን ሕዝብ የዘመናት አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡
በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው #የሀሰት_ወሬ የድሬድዋን ከተማ ብቻም ሳይሆን የሀገሪቱን ሰላም #ለማደፍረስ እንደ ቤንዚን የሚጠቀሙ ስውር የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው አካላት በመኖራቸው መጠንቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

የድሬዳዋ ወጣቶች‼️
የዓመታት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻቸው #በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው በድሬደዋ ወጣቶች ባካሄዱት ሰልፍ ጠየቁ፡፡
ወጣቶቹ በተለያዩ የከተማው አስተዳደር አካባቢዎች በመዘዋወር ባካሄዱት ሰልፍ ጥያቄያቸውን ባሰሟቸው መፈክሮች አስተጋብተዋል፡፡
በዚህም ድሬዳዋ ሁሉም ብሔሮችና ብሔረሰቦች በፍቅር በአንድነትና በእኩልነት የሚኖሩባትን መሆኗን ጠቅሰው አብዛኛውን ወጣትና ህዝብ ያገለለ የመንግስት መዋቅርና አሰራር ሊፈርስ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በተግባር ላይ ያለው የፖለቲካ የስልጣን ክፍፍልና አሰራር የአብዛኛውን ህዝብና ወጣት ከልማት ተጠቃሚነት ያገለለ መሆኑን ወጣቶቹ ገልጸዋል፡፡
መዋቅሩ ወጣቱን ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር የዳረገው በመሆኑ በፍጥነት እንዲቀየር ጠይቀዋል፡፡
በሰልፉ የተካፈለው ወጣት ሰለሞን መክብብ በሰጠው አስተያየት የአስተዳደሩ ከንቲባ ወጣቶችን ለማናገር የያዙትን ቀጠሮ መሰረዛቸው በወጣቶቹ ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን ተናግራል፡፡
”እኛ ሁሉም ወጣቶች የሚሳተፉበት ውይይት ነው የምንፈልገው ፤ የወጣቶች ወኪል እየተባለ አዳራሽ የሚሰበሰበው እኛን ስለማይወክሉ የውክልና ውይይት አንፈልግም” ብሏል፡፡
”አንድም ባለስልጣን ቀርቦ #ያናገረን የለም፤ ከተማዋ መሪ የላትም፤ የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን” ያለው ደግሞ ሌላው የሰልፉ ተካፋይ ወጣት ሲሳይ አየለ ነው፡፡ በሁሉም መስክ አድሏዊነት የሌለው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ጠይቋል፡፡
የኢዜአ ሪፖርተር በከተማው ተዘዋውሮ እንደተመለከተው ዛሬ በከተማ የተካሄደው ሰልፍ ካለፉት ሁለት ቀናት የበለጠ አብዛኛውን የከተማው አካባቢ ያዳረሰ ነው። በነበረው ግርግር በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና አገልግሎት መሰጪዎች መሰተጓጎላቸውን ተመልክቷል፡፡
በጤና ጣቢያዎችና በድል ጮራ ሆስፒታል የኢዜአ ሪፖርተር ባደረገው ቅኝት የተጎዱ ሰዎች ህክምና አግኝተው ሲመለሱ አይቷል፡፡
#የመከላከያ_ሠራዊት አባላት የወጣቶቹ ቁጣ በሰላማዊ መንገድ ለማብረድና ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት በሰልፍ አድራጊዎችና በሌላም ህብረተሰብ ዘንድ በአዎንታዊ ጎኑ ድጋፍ አግኝቷል፡፡
በአሁን ሰዓት ሰራዊቱ በድንጋይ የተዘጉትን መንገዶች በማጽዳት ለተሸከርከሪዎች ክፍት እንዲሆኑ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ