TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ሙስጠፋ ማን ናቸው?⬆️

አቶ ሙስጠፋ ሙሐሙድ ዑመር በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሶማሌ ክልል #ጊዜያዊ መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ሙስጠፋ በክልሉ በስልጣን ላይ ያለዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አባል ባይሆኑም በጊዜያዊነት ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሥልጣን የቆዩትን አሕመድ አብዲ መሐመድን ተክተው ለመጪዎቹ ሁለት አመታት ክልሉን ይመራሉ።

በርዕሰ-መሥተዳድርነት እንዲያገለግሉ መመረጣቸው እስከተሰማ ድረስ ከነ ቤተሰቦቻቸው ኬንያ ይኖሩ የነበሩት አቶ ሙስጠፋ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶማሊያ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በመስራት ላይ ነበሩ።

ኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ የሕጻናት አድን ድርጅትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ አገልግለዋል።

አቶ ሙስጠፋ የተወለዱት ከጅጅጋ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ በምትርቀው አዋሬ የተባለች አነስተኛ ከተማ በ1964 ዓ.ም. ነው። ትምህርታቸውን በደገሐቡር እና በሐረር የመድሐኒዓለም ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪቸውን በኤኮኖሚክስ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዚያው በኤኮኖሚክስ ከለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ በተልዕኮ ትምህርት አግኝተዋል።

ከዚህ ቀደም የሶማሌ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የዶክተር አብዱል መጂድ ሑሴን መምህራን ማሰልጠኛ ማዕከል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ከኢትዮጵያ ለምን ወጡ⬇️

አቶ ሙስጠፋ በቅርቡ ከሥልጣናቸው የተነሱት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር የክልሉን የርዕሰ-መሥተዳድርነት ሥልጣን ሲቆጣጠሩ ነው የሶማሌ ክልልን የለቀቁት።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኤኮኖሚክስ ተማሪ ሳሉ የአቶ ሙስጠፋ ጓደኛ የነበሩት አቶ ዚያድ አሕመድ የቀድሞው ርዕሰ መሥተዳድር አብዲ መሐመድ ዑመር "ያደርሱባቸው የነበረውን ችግር #ሸሽተው" ከነ ቤተሰቦቻቸው #ኬንያ ለመግባት መገደዳቸውን ያስታውሳሉ።

ከሁለት አመታት በፊት አቶ ሙስጠፋ በክልሉ መንግሥት ላይ የሚሰነዝሩትን ተቃውሞ እንዲያቆሙ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ አሻፈረኝ በማለታቸው የምኅንድስና ባለሙያ #ወንድማቸው ፋይሰል ኦማር በልዩ ፖሊስ ከደገሐቡር ከተማ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ #መገደላቸው ይነገራል። አቶ ዚያድም "ውጪ ያሉት አራማጆች በአብዲ ኢሌ ላይ ወይም በነበረው አገዛዝ ላይ ተቃውሞ ካሰሙ ወይም አንድ ነገር ካደረጉ ቤተሰቦቻቸው ይታሰራሉ ወይም ይገረፋሉ። አቶ ሙስጠፋም ወንድማቸውን ያጡት በዚህ አጋጣሚ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ዚያድ የድሮ ጓደኛቸው የሶማሌ ክልልን ለመምራት ይመረጣሉ የሚል ቅድሚያ ግምት አልነበራቸውም። "አልጠበቅኩም። እሱ የውጪ ሰው ነው። የፓርቲ አባልም አልነበረም" ይላሉ። አቶ ሙስጠፋ ከዚህ ቀደም ክልሉን ይመሩ የነበሩት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ የለውጥ አቀንቃኝ ነበሩ። በክልሉ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጋልጡ የቀድሞውን አስተዳደር
የሚሞግቱ ጽሁፎች በሶማሊኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሲፅፉ ቆይተዋል። በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይም የጎላ ተሳትፎ ነበራቸው።

የሶማሌ ክልል ፖለቲካን በቅርብ የሚከታተሉት አቶ ዚያድ ተመራጩ ፕሬዝዳንት በርካታ እና ውስብስብ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው አልዘነጉም። "የሕግ የበላይነት፣ ሰላም እና መረጋጋት መምጣት አለበት። ሥራ አስፈፃሚው፣ ሕግ አውጪው እና ሕግ ተርጓሚው ሪፎርም ይፈልጋል" ይላሉ አቶ ዚያድ።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ (DW Amharic)
@tsegabwolde @tikvahethiopia