TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.2K photos
1.58K videos
216 files
4.31K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በአሁኑ ባለው የትግራይ ቀውስ " አሸናፊም ሆኖ ተሸናፊ የለም " አሉ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ። እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው ያሉ ሲሆን " የሚጠበቅ ማስተካከያ ቢኖርም እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ…
#Tigray

የትግራይ ህዝብ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም ጥሪ ቀረበ።

ጥሪውን ያቀረቡት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው።

ጥቆማ የሚቀርብበት አድራሻ በኢሜል
[email protected] መሆኑ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥቆማው መቼ ተጀምሮ እንደሚያልቅ እንዲሁም በህዝብ ጥቆማ የተመረጠው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት እንዴትና መቼ ይፋ እንደሚሆን አስመልክተው በዝርዝር ያሉት የለም።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አሕመድ  (ዶ/ር) በትግርኛ ቋንቋ ምንድነው ያሉት ?

" ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጥቆማ አስመልክቶ ለመላው የትግራይ ህዝብ የቀረበ  ጥሪ !

በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 62(9)፣ እንዲሁም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ ለመግባት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር  359/1995 መሰረት እንዲሁም በትግራይ አሳታፊ ጊዚያዊ አስተዳደር በሚመለከት የተደነገገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 533/2015 መሰረት የቆመው ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመታት መቆየቱ ይታወቃል።

በአዋጅ 359/1995 አንቀፅ 15(3)  መሰረት ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለሁለት ዓመት ብቻ እንደሚቆይ ይደነግጋል። ይሁን እንጂ በተጨባጭ ምክንያቶች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ ማራዘም ይቻላል። ከላይ በተጠቀሱት ህጎችና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር የተቀመጡለት ተልእኮዎች አጠናቅቆ በህዝብ ለተመረጠ መንግስት ሃላፊነቱ ማስረከብ ይገባ ነበር።

ይሁን እንጂ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሰጡት ዋና ተልእኮዎች በተወሰነለት ጊዜ ማጠናቀቅ አልቻለም።

ከተሰጡት ዋና ተልእኮዎች አንዱ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠር ነው። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህንን ቁልፍ ተልእኮ ባለማሳካቱ ምክንያት ዕድሜውን ለአንድ ዓመት ለማራዘም አስገድዷል።

የፌደራል መንግስት መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ ለማራዘም ፣ ፓለቲካዊ ፣ አስተዳደራዊና የህግ ስራዎች በማከናወን ላይ የሚገኝ ሆኖ ከዚሁ ጎን ለጎን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት መሾም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝተዋል።

በደንብ ቁጥር 533/2015 አንቀጽ 3(2) መሰረት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት የመሾም ሃላፊነት የጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ቢሆንም ህዝብ በምርጫ መሪዎቹ እስኪመርጥ ድረስ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመምረጥ በኩል ተሳትፎ እንዲኖረው አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተልእኮዎች በብቃት መፈፀም ይችላሉ ሰላምና ደህንነት ያረጋግጣሉ የምትሉዋቸው እጩዎች በ
[email protected] የኢሜል አድራሻ ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ከዛሬ ጀምራችሁ ጥቆማችሁን መላክ እንደምትችሉ እናሳውቃለን። "

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

" ህዝበ ሙስሊሙ ጾሙ የተሟላ እንዲሆን በየቀኑ ለአገርና ለህዝብ ከልብ የመነጨ ዱዓ ማድረግ አለበት " - ሀጂ መሐመድ ካሕሳይ

በትግራይ መቐለ ከተማ " ኢፍጣራችን ለሰላማችን " በሚል መሪ ቃል ኢስላማዊ የጎደና ላይ የኢፏጣር ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።

በኢፍጧር ስነ-ስርዓቱ ላይ በርካታ የአስልምና እምነት ተከታዮች ተሳትፈውበታል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ሀጂ መሐመድ ካሕሳይ ፤ ረመዷን ማለት የመቻቻል፣ የመከባበርና ያለንን ለሌላ ማከፋል መግለጫ ነው ብለዋል።

" የኢፍጧር ስነ-ስርዓት በጋራ ከመብልና ከመጠጥ በዘለለ የአንድነታችን መግለጫ ነው " ያሉት ዋና ፀሀፊው " ህዝበ ሙስሊሙ ጾሙ የተሟላ እንዲሆን በየቀኑ ለአገርና ለህዝብ ከልብ የመነጨ ዱዓ ማድረግ አለበት " ብለዋል።

የኢፍጧር ስነ-ስርዓቱ ተፈናቃይ ወገኖች በማሰብና በማሰባሰብ መካሄዱንም ተናግረዋል።  

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - Destsi Woyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቋወመ። ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፥ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚነንስትር  ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ  ለቀጣይ አንድ ዓመት ስልጣኑ የሚራዘመውን የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመራ ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም አስመልክቶ ያወጡትን መልዕክት " የተናጠል ውሳኔና ተግባር " ሲል ተቃውሟል።     " የፕሪቶሪያ ሥምምነት ከተፈረመ…
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ ምንድነው ያሉት ?

ከትግራይ ክልል " ለስራ " በሚል ምክንያት ከወጡ 20 ቀናት ያስቆጠሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን ለህክምና አንዴ ወደ ዱባይ ሌላ ጊዜ ወደ ባንኮክ ተጉዘዋል እየተባለ ሲነገርባቸው ነበር።

ትላንት እሁድ በሰዓታት ልዩነት ሁለት መልእክቶችን አጋርተዋል።

አንዱ ለህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የሚል ሲሆን ፤ ሌላኛው ለተቀናቃኞቻቸው " ድሉ የህዝብ ነው " የሚል ጠንካራ ትችት አዘል መልእክት ነው።

" ላለፉት 20 ቀናት በትግራይ እየታየ ያለው ፓለቲካዊ ቀውስ ' ስልጣን ወይ ሞት ' የሚል ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት የደሎተው ሴራ መጨረሻው ምዕራፍ ማሳያ ነው " ብለዋል።

ይህ ደሞ አንዳንድ የተሻለ ስምና ዝና ያላቸውን ግለሰቦችም ለስህተት የዳረገ ፍፃሜ ነው በማለት ተግባሩ አጣጥለውታል።

ፕሬዜዳንቱ " ኋላቀር ቡድን " ሲሉ የገለፁት አካል የጊዚያዊ መንግስቱ መዋቅር በመጣስ ማህተም ከተቆጣጠረ በኋላ በመጀመሪያ እርምጃው በትላለቅ ከተሞች ለደጋፊዎቹ በስፋት መሬት አከፋፍሏል ፤ ገቢ የሚያስገኙለትን የሽያጭ ስራዎች ፈፅሟል ብለዋል።

" መሬት ከመሸጥና ከማከፋፈል አልፎ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው መመለስና ግዛታዊ አንድነት ማረጋገጥ ከመፈክር በዘለለ ጣጣው አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ኋላቀር ቡድን " ሲሉ የገለፁት አካል ሁለተኛ ትኩረቱ ወደ
#ፌደራል እየተመላለሰ የፕሬዜዳንት ስልጣን እንዲሰጠው መለመን ሆኗል ሲሉ አብራርተዋል።  

" ቡድኑና አሽከሮቹ በህልምና በቀልባቸው የማይለቁዋቸው ሁለት አጀንዳዎች መሬትና ስልጣን ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቡድኑ የሚያስተባብራቸው አካላት የተፈናቃዩ ተስፋና የወጣቱን ህልም በመቀማት ወደ ሁለተኛ ዙር ትርምስ ሊከቱን ታችና ላይ በማለት ስለሚገኙ ህዝቡ ሃይ ሊላቸው ይገባል " ሲሉ አክለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩትን ጠንከር ያለ ፅሁፍ " ድል የህዝባችን ነው " ሲሉ ቋጭተውታል።

#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ታስረው ይቅረቡ " - ፍርድ ቤት ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የቀረበውን ክስ ፍርድ ቤት ቀርበው መልስ እንዲሰጡ የተፃፈላቸውን ትእዛዝ " አንቀበልም " ያሉ አካላት ታስረው እንዲቀርቡ የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት አዘዘ። ፍርድ ቤቱ ጥር 19/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ፤ ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ ክስ የቀረበባቸው 4 ርእሰ መምህራን የአክሱም ከተማ ፓሊስ አስሮ እንዲያቀርባቸው ፍርድ ቤቱ አዟል።…
#Tigray የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት  ፤  " በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ የተደረገው የሂጃብ መልበስ ክልከላ እስከ አሁን አልተነሳም " ሲል አሳውቋል።

ይህን ያሳወቀው ትላንት በመቐለ በተካሄደው የዒድ ሶላት ወቅት ነው።

ምክር ቤቱ ዋና ፀሓፊ ሀጂ መሀመድ ካሕሳይ " የሂጃብ መልበስ ክልከላ እስከ አሁን አልተነሳም " ያሉ ሲሆን " አሁንም ጥያቄያችን እንዲመለስ ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

የሃይማኖት መቻቻልና መከባበር የአንድ አገርና ህዝብ መልካም ጌጥና መለያ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

ክልከላው " የሃይማኖት እኩልነትና የመማር መብት የሚፃረር ነው " ያሉ ሲሆን   ምክር ቤቱ ጉዳዩ በህግ እየተከታተለው እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመተባበር ታሪካዊውና ሃይማኖታዊውን የአልነጃሺ መስጂድ በማልማት የቱሪስቶች መዳረሻ ለማድረግ ያለመ " አልነጃሺ 00 " በማለት የተሰየመ ፕሮጀክት ግንባታ ለማካሄድ ጥናት ማጠናቀቃቸው ተነግሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" ትግራይ ከተደገሰላት የባሰ አዘቅትና አዙሪት የምናድንበት ጊዜ አሁንና አሁን ብቻ ነው " አለ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን።

አቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ቡድን ባወጣው መግለጫ  "ልዩነቶቻችን በይደር በማቆየት ቂምና ቁርሾ ቀርፈን እኔነትንና ጠቅላይነት አስተሳሰብ ከውስጣችን በማስወገድ ትግራይ እናድናት " ብሏል።

ትግራይ ከገባችበት ቀውስና አጣብቂኝ " ያድናታል ብዬ አምኜበታለሁ  " ያለውን የመፍትሄ ሃሳብ ለውይይት ማቅረቡ ያስታወቀው ቡድኑ ከቀረበው የተሻለ ክልሉን ማዳን የሚችል የመፍትሄ ሃሳብ ካለ ለማዳመጥ ዝግጁ መሆኑ ገልጿል።

ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩትን ህወሓት በግልፅና ጠንካራ ቃላት የተቸም ሲሆን ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለአንድ ዓመት መራዘሙ በመቀበል የሚከተሉት ሦስት የመፍትሄ ሃሳቦች አቅርበዋል :-

- ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሁሉም አመለካከቶች በማቀፍ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማእከል በማድረግ መዋቅሩ ተጠናክሮ በአስቸኳይ መቋቋም አለበት።

- ዕድሜውን የተራዘመው ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋም የሚያስችል ሁሉም አመለካከቶችና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈራራሚዎች ያካተተ ፓለቲካዊ ውይይት ይቅደም።

- የትግራይ ሰራዊት ታጣቂዎች ወደ ማረፍያ ካምፓቸው ተመልሰው የሰላምና የፀጥታ ስራ ሙሉ በሙሉ በህዝባዊ ፓሊስ ይተካ ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር እስከ ቀበሌ ድረስ ህዝብ ነፃ ሆኖ በመረጣቸው አስተዳዳሪዎች እንዲመራ ፣ ተግባሩ በአንድ ወር ውስጥ እንዲከናወን።

... ብሏል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት የህወሓት ቡድን ከደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ቡድን ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" ሦስት ሳምንት ሳይሞላው የሦስት ወር ደመወዝ በሃሰት ማህተም በመጠቀም ከድርጅቱ የብር ካዝና አለአግባብ መመዝበሩ አረጋግጫለሁ " - ጋዜጠኛ ሓለፎም ንርአ

➡️ " ጉዳዩ በህግ የተያዘ ነው " - አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ


የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 አከባቢ በ136ኛው የንጉስ ነገስት ሃፀይ ዮሃንስ መታሰብያ ዝግጅት ተገኝተው መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በዚያው ወደ አሉላ አባነጋ የአውሮፕላን ማረፍያ በመሄድ ወደ አዲስ አበባ ከተጓዙ 22 ቀናት ተቆጥረዋል።

አዲስ አበባ ሆነው የፕሬዜዳንትነት መጠሪያቸው ቢጠቀሙም ላለፉት 22 ቀናት መቐለ በሚገኘው ቢሯቸው ገብተው የከወኑት አንዳች የህዝብ አገልግሎት የለም።


ፕሬዜዳንቱ " ለስራ " በሚል ምክንያት ከመቐለ ትግራይ ከወጡ በኋላ በክልሉ ያሉት ሚድያዎች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ?

የዚህ መረጃ ዋና የምልከታና የትኩረት ነጥብ ይኸው ጉዳይ ነው።

ባለፉት ሦስት ሳምንታት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ከነበሩት ሦስት ሚድያዎች ፦
- የትግራይ ቴሌቪዥንና ሬድዮ
- የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥንናሬድዮ
- 104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ለውጦች ተከስተዋል።

ከለውጦቹ አንዱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ለሚድያዎች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሁም መጋቢት 22 በግላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያሰራጩት፣ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም በእሳቸው ስም የሚመራ ህወሓት ያወጣውን መግለጫ በሦስቱ ሚድያዎች አልተሰናገደም።

በድምፂ ወያነ ፣ ትግራይ ቴሌቪዥንና ሬድዮ በግልፅ የተደረገ የአመራር ለውጥ ባይኖርም የትግራይ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ ተሻለ በቀለ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ከመቐለ መወጣታቸውን ተከትለው ወጥተው ዛሬ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም ወደ ቢሯቸው መመለሳቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ለማረጋገጥ ችሏል።

ለሦስት ሳምንታት ያህል ከመቐለ የመውጣታቸው ምክንያት በትግራይ ከተፈጠረው ቀውስ ተያይዥነት ይኑረው አይኑረው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ አልቻለም።

በቀድሞ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሚድያ ፍቃድ አግኝቶ በመቐለ ከተማ አስተዳደር ስር እንደሚተዳደር የሚነገርለት 104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ደግሞ " እኔ ነኝ ስራ አስኪያጅ " የሚል ክርክር ከተነሳበት መቆየቱ ይታወቃል።

የፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ከመቐለ ከተማ መውጣት ተከትሎ " በመቐለ ከተማ አስተዳደር ተሹሚያለሁ " በሚል የይገባኛል ጥያቄ በሚድያዎች ጭምር በግልፅ ሲያቀርቡ የቆዩት ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ የቆዩትን የኤፍ ኤም ጣብያው ስራ አስኪያጅ ሓለፎም ንርአ በመግፋት ጣቢያውን ተቆጣጥረውታል።

" አካሄዱ ህገ-ወጥ ነው " በማለት የታቀወሙትና " አሁንም እኔ ነኝ ህጋዊ ስራ አስኪያጅ " በማለት የሚሞጉቱት ጋዜጠኛ ሓለፎም ንርአ የኤፍ ኤም ጣብያው የባንክ ሂሳብ እንዲዘጋ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ መስራት ቤት የድርጅቱን ማህተም በመጠቀም ፅፈዋል።

መጋቢት 16/2017 ዓ.ም በፃፉት " የ ይታገድልኝ " ጥያቄ እሳቸው የሬድዮ ጣብያው ህጋዊ ስራ አስኪያጅ መሆናቸው በመጥቀስ የሚድያው ፈራሚዎች እንዳይቀየሩ በማሳሰብ ከእውቅናቸው ውጪ ማንኛውም የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ይታገድልኝ ብለዋል።

ስራ አስኪያጁ የእገዳ ደብዳቤ  ከመፃፉ በኋላ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባጋሩት ሰፊ ሃተታ ፤ ሬድዮ ጣብያውን " በህገ-ወጥ መንገድ ተቆጣጥሮታል " ሲሉ የከሰሱት ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ " ሦስት ሳምንት ሳይሞላው የሦስት ወር ደመወዝ በሃሰት ማህተም በመጠቀም ከድርጅቱ የብር ካዝና አለአግባብ መመዝበሩ አረጋግጫለሁ " ብለዋል። የብር መጠኑ ግን በይፋ አላስቀመጡም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ስለ  ቀረበባቸው ክስ ማብራርያ እንዲሰጡ ወደ አቶ  ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ በተደጋጋሚ ደውሎ ነበር።

" ጉዳዩ በህግ የተያዘ ነው " ከሚል አጭር ምላሽ ውጪ ዘርዘር ያለ በቂ ማብራርያ ሊሰጡ አልፈገሉም።

በአጠቃላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ከመቐለ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ በክልሉ በሚገኙ ሚዲያዎች ግልጽ የሆኑ ለውጦች ታይተዋል።

በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ትግራይ ክልልን ለመምራት የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ቆይታው መጋቢት 5/2017 አብቅቷል። ቆይታው ለአንድ አመት እንዲራዘም የሚፈቅድ አዋጅም ፀድቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray : በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ከባባድ ፆታዊ ጥቃቶችና ሞት የሚፈፅሙ ተከሳሽና ወንጀለኞች ጉዳዮች በሚከታተሉና ህጋዊ ውሳኔ በሚሰጡ ዳኞች ላይ በተለያየ መንገድ የሚገለፅ ጫና እየደረሰ ነው ሲል የትግራይ የዳኞች ማህበር አማረረ።

ማህበሩ ከባባድ ወንጀሎች ለሚከታተሉና ህጋዊ ውሳኔ ለሚሰጡ ዳኞች አስፈላጊውን የደህንነትና የፀጥታ ከለላ እንዲሰጥ አበክሮ ጠይቀዋል።

ማህበሩ በላከው መግለጫ ፤ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ከባባድ ፆታዊ ጥቃቶችና የሞት ጉዳዮች የሚከታተሉ ውሳኔ የሚሰጡ ዳኞች ስራቸውን ነፃና ገለልተኛ ሆነው ለመከወን እጅግ ተቸግረዋል ብሏል።

" ዳኞቹ ስራቸውን ተረጋግተው በሰከነ የህግ አካሄድ እንዳይመለከቱ በተለያዩ መንገዶች ጫና እየደረሰባቸው ነው ስለሆነም ላለባቸው የደህንነታቸው አደጋ በቂ ከለላ በማጣታቸው ምክንያት ስራውን ከማቆማቸው በፊት የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በመመካከር ችግሩ በአፋጣኝ መፍታት አለበት " ሲል አሳስቧል።

" ከጦርነቱ በኋላ የትግራይ ዳኞቸ በከፍተኛ ፓለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ቅርቃር ውስጥ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ ጥያቄያቸው ይመለስላቸው " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

በፌደራል እና በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ዳኞች የሚያገኙት የደመወዝ ጭማሪና ጥቅማ ጥቅም የክልሉ ዳኞች እንደተነፈጉ ገልጾ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሌሎች ክልሎች እየተተገበረ ያለውን የጥቅማ ጥቅም አሰራር ለመመለስ " በጥናት ላይ ነኝ " በማለት ከአንድ ዓመት በላይ ማስቆጠሩ ልክ አይደለም ሲል ወቅሷል።

የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት  የአገሪቱ ህግና የትግራይ ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የዳኞች የጥቅማጥቅም ፣ የደመወዝ ፣ የደህንነትና መሰል ጥያቄዎች እንዲመልስ ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወስኗን።

በትግራይ መምህራን ማህበር ጠበቆች የቀረበውና በጦርነቱ ጊዜ ያልተከፈለ የ17 ወራት የመምህራን ደመወዝ ሲመለከት የቆየው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ውሳኔውን ሰጥቷል።

ተከሳሾቹ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ፣ የፋይናንስ  ቢሮ ፣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም የገንዘብ/ የፋይናንስ ሚንስቴር ሲሆኑ ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ ቆይቷል።

ፍርድ ቤቱ የቀረበለት ክስ መርምሮ የመምህራኑ የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወስኖ ፋይሉ ወደ መዝገብ ቤት መልሶታል። 

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደሚቀበሉትና እንዳረካቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪ መምህራን ውሳኔው ቶሎ በመተግበር በከፋ ሁኔታ የሚመገኙ መምህራን መታደግ ይገባል ብለዋል።

ተከሳሾቹ ውሳኔው በማስመልከት እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

መምህራን ያካተተ የ17 ወራት ያልተከፈለ የመንግስት ሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ የመከፈል ጥያቄ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት የጀመረ ነው።

በቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዳይታይ የሚከልክል መምሪያ እስከማውጣት ደርሶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

ፎቶ፦ Tigrai TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት በሦስት ጀነራሎች ላይ የተቀመጠው ጊዚያዊ እግድ በአዲሱ  ፕሬዜዳንት ተሽሯል።

በአራተኛው ጀነራል የተወሰነው ከሃላፊነት የማንሳት ውሳኔም ተሰርዟል።

የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦
- በጀነራል ምግበይ ሃይለ
- በጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊስ
- በጀነራል ማሾ በየነ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ጀነራል ፍስሃ ኪዳኑ ፈንታ በአቶ ጌታቸው ረዳ በተፃፈ ደብዳቤ ከስራ ገበታቸው እንዲነሱ መወሰኑ  ይታወሳል።

በቀድሞ ፕሬዜዳንት የተቀመጠው ጊዚያዊ እግድና ከስራ የማሰናበት ውሳኔ በአዲሱ የጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።

አዲሱ ፕሬዜዳንት ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ጊዚያዊ እግዱና የስራ ስንብቱ ከመሰረዛቸው በተጨማሪ ፤ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊው በስራ ገበታቸው እንዲቀጥሉ የሚያፅና የሹመት ደብዳቤ ፅፈዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት በሦስት ጀነራሎች ላይ የተቀመጠው ጊዚያዊ እግድ በአዲሱ  ፕሬዜዳንት ተሽሯል። በአራተኛው ጀነራል የተወሰነው ከሃላፊነት የማንሳት ውሳኔም ተሰርዟል። የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦ - በጀነራል ምግበይ ሃይለ - በጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊስ - በጀነራል ማሾ በየነ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወሳል።…
#Tigray

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ እንደ አዲስ የተዋቀረው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ስራ እንደጀመረ ተነግሯል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ የነበረውን የካቢኔ ቁጥር ከ27 ወደ 21  ፤ ሁለት ምክትል ፕሬዜዳንት የነበረውን ወደ አንድ እንዲወርድ ያደረጉት ፕሬዜዳንቱ እስካሁን ምክትላቸው ማን እንደሆነ በይፋ አላስታወቁም።

ይሁን እንጂ ከደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የህወሓት ሃይል ሰፊ ቁጥር ያለው የካቢኔ አባል ያካተቱ ስለመሆኑ ተነግሯል።

ምክትላቸው  የህግ ምሁርና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኣማኒኤል አሰፋ አደርገው መሾማቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ጨምሮ በርካቶች በመፃፍ ላይ ይገኛሉ።

አንዳንዶች  " አዲሱ የጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የወጣቱ የለውጥ ጥያቄ የሚመልስ አዲስ ካቢኔ አላዋቀሩም " በሚል ነቄፌታ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ አዲሱ ካቢኔ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ " ትግራይ በአሸናፊና ተሸናፊ የፓለቲካ ቅኝት ከገባችበት አዘቅት መውጣት አትችልም " ብለዋል።

" ባለፉት ሁለት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዓመታት በርካታ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ተፈፅመዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ጥሩውን ለራስ መጥፎውን ለሌላ መስጠት አይቻልም ድሉም ውድቀቱም የጋራ ነው ከእልህና ህዝብንና አገር ከሚጎዳ ፓለቲካዊ አካሄድ እንውጣ "  ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።  

" የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች የሚመሰገኑበት መድረክ ይዘጋጃል " ያሉት ፕሬዜዳንቱ ጥሪውን ተቀብለው እንዲገኙ ከወዲሁ በይፋ የግብዣ ጥሪ አቅርበዋል።

የቀድሞ ፕሬዚዳንትና አመራሮች ይመሰገኑበታል የተባለው የምስጋና ስነስርዓት መቼ እና የት እንደሚዘጋጅ የተባለ ነገር የለም።

በሌላ በኩል ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ተፈናቃዮች የሚገኙበት ስቃይና ሰቆቃ ባወሳ ንግግራቸው " በዚሁ ዓመት ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ይሰራል ፤ በማቆያ ጣብያ የሚቆዩት ደግሞ አኗኗራቸው እንዲሻሻል ትኩረት ይደረጋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

@tikvahethiopia