TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#BGI #PurposeBlack

" ነገ ጥዋት መግለጫ እንሰጣለን "- ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያን አ/ማ

በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ ተቋርጧል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በባከልን ኢሜል የሽያጩ ውል የተቋረጠው ፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ነው።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ምን አስተያየት አለው የሚለውንና የሚሰጠው ምላሽ ይኖር እንደሆነ ለድርጅቱ ኃላፊዎች ስልክ ደውለንላቸው የነበረ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ነገ ጥዋት 2 ሰዓት ይፋዊ መግለጫ / ምላሽ እንደሚሰጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ድርጅቱ የሚሰጠውን መግለጫ ተከታትለን መረጃ እንልካለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BGI #PurposeBlack " ነገ ጥዋት መግለጫ እንሰጣለን "- ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያን አ/ማ በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ ተቋርጧል። ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በባከልን ኢሜል የሽያጩ ውል የተቋረጠው ፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል…
#PurposeBlack

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

- የቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ ውልን በውልና ማስረጃ በኩል ለመፈጸም ዝግጁ ነን።

- ቢጂአይ ኢትዮጵያ የመንግስትን ግዴታ ቀድሞ ባለመወጣቱ በውል እና ማስረጃ መፈራረም አልተቻለም። ከታክስ ጋር በተያያዘ ክሊራንስ አልጨረሱም።

- ቢጂአይ ብዙ ማሟላት ያለበትን ዶክመንት አላሟላም። በዚህ ምክንያት በውል እና ማስረጃ ለመፈራረም አልፈለጉም።

- ለቢጂአይ 1 ቢሊዮን 150 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈፅመናል። ቀሪውን ገንዘብ በውልና ማስረጃ ስንፈራረም ለመክፈል ዝግጁ ነን።

- ክፍያው በ3 ዙር የሚፈፀም ሲሆን 2ኛው ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በውልና ማስረጃ ስንፈራረም ነው። ይህ ቀድሞ በፈጸመው ውል ላይ ተቀምጧል።

- ከታክስ ነፃ የሆኑበት ወረቀት ከቀረበ በውልና ማስረጃ እንፈራረማለን። እኛ ተገቢውን ዶክመት ካሟሉ በሁለተኛ ዙር የሚጠበቅብንን 2.5 ቢልየን ብር ለመክፈል ዝግጁ ነን።

- ቅዳሜ የካቲት 23 /2016 ዓ.ም በውልና ማስረጃ እንዋዋል የሚል ደብዳቤ ልከንላቸው ነበር። እነሱ ሕጋዊ  መስፈርቶችን ማሟላት ባለመቻላቸው ውሉን አቋርጠናል የሚል መግለጫ ትናንት አውጥተዋል።

- እኛ ብሩን ለመክፈል ዝግጁ ነን በውልና ማስረጃ የማይፈራረሙ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንወስዳለን።

- ኃላፊነቱን እየተወጣ ያልሆነው በውልና ማስረጃ እንዲፈፀም ኃላፊነቱን ያልተወጣው ቢጂአይ ኢትዮጵያ እንጂ እኛ አይደለንም።

- አሁንም ግዢውን ለመፈፀም ዝግጁ ነን።

- ሌላ አማራጭ መሬቶችን ገዝተናል። መሰረት እየጣልን ነው። በገባነው ቃል ቤቶቹን በሚቀጥሉት 5 አመታት ሰርተን እናስረክባለን።

- ከመንግስት በሊዝ ስምምነት እንዲሁም 30/70 በሚል ስምምነት በግዢ ሂደት ላይ ያሉ መሬቶችም አሉ።

- ቤት ለመሸጥ ቃል ለገባንላቸው ደንበኞች ቤቱን እናስረክባለን።

በትላንትናው ዕለት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በላከልን ኢሜል አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ መቋረጡን ማሳወቁ ይታወሳል።

የሽያጩ ውል የተቋረጠው ፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ እንደሆነ መግለፁ አይዘነጋም።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PurposeBlack ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ምን አለ ? - የቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ ውልን በውልና ማስረጃ በኩል ለመፈጸም ዝግጁ ነን። - ቢጂአይ ኢትዮጵያ የመንግስትን ግዴታ ቀድሞ ባለመወጣቱ በውል እና ማስረጃ መፈራረም አልተቻለም። ከታክስ ጋር በተያያዘ ክሊራንስ አልጨረሱም። - ቢጂአይ ብዙ ማሟላት ያለበትን ዶክመንት አላሟላም። በዚህ ምክንያት በውል እና ማስረጃ ለመፈራረም…
#PurposeBlack

የፐርፐርዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በአሁን ሰዓት #አሜሪካ ሀገር እንደሚገኙ ተነግሯል።

" አሜሪካ የሚገኙት ለስራ ነው " ያለው ድርጅቱ የፊታችን ሀሙስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱና መግለጫም እንደሚሰጡ አመልክቷል።

ዛሬ መግለጫ ሰጥተው የነበረው የድርጅቱ የቦርድ አባል እና የህግ አማካሪ ዶ/ር ኤርሚያስ ብርሃኑ ናቸው።

ፐርፐዝ ብላክ ከቤቶቹ ግንባታ እና ከአክሲዮን ባለቤቶች ጋር በተያያዘ ምን አለ ?

- ለቤቶች ግንባታ ሌላም መሬት መግዛቱን ገልጿል።

- አሁን በገባው ቃል መሰረት ቤቶቹን በሚቀጥሉት 5 አመታት ሰርቶ እንደሚያስረክብ አመልክቷል። 

- " #ወሰን " አካባቢ ለቤቶች ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል ብሏል።

- የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያን አክሲዮኖች የገዙ ዜጎች ብራቸው #እንደማይመለስ ገልጿል። ነገር ግን ባለ አክሲዮኖች አክሲዮናቸውን መሸጥ ይችላሉ ብሏል።

- በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ለ1 ሺ ባለ አክሲዮኖች የአክሲዮን ሽያጭ ካደረገ በኋላ የአክሲዮን ሽያጭ ማቆሙን ገልጿል።

- በተለዩ ቦታዎች መሬት እና ንብረትን ከግለሰቦች በመግዛት ፣ መሬት እና ንብረቱን አፍርሶ በመስራት እና ከባለሃብት ጋር አብሮ በማልማት በ3 አማራጮች ግንባታ ለመጀመር የሚጠቀማቸው አማራጮች መሆናቸውን አሳውቋል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " መጀመሪያ 250 ሚሊዮን ብር ከዛ 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ጠየቁን " - ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀገር ጥለው አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ዛሬ አሜሪካ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል። " ከሀገረ የወጣሁት በግፈኞች ምክንያት ተገድጄ ነው " ብለዋል። ባልፈው የግላቸውን ጨምሮ የድርጅቱ የባንክ አካውንቶች በሙሉ በመንግስት…
#PurposeBlack

የፐርፐዝ ብላክ ኢ ቲ ኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሥራ አስፈጻሚዎቹ ስልጣንን አለአግባብ በመገልገል እና ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው ዛሬ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በማኅበሩ ተጭበርብረናል ያሉ ባለአክሲዮኖች ለፖሊስ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ምርመራ ተጀምሮ የአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ማኅበሩ መሀል ሜክሲኮ ላይ ገና በእጁ ባላስገባው መሬት እና ይዞታ ቤት ገንብቶ ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት በ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ እና በራሪ ወረቀቶች በማስተዋወቅ ከሕዝቡ ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱን በተለያየ መንገድ ከሕብረተሰቡ ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎች ያመላክታሉ ተብሏል።

በዚህ መነሻም ሥራ አስፈጻሚዎቹ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፍትሕ ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍስሃ እሸቱ ከወራት በፊት ሀገር ጥለው አሜሪካ መግባታቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia