TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለመሰናበቻ ዶክተር አብይ ጠ/ሚ ከመሆኑ በፊት (የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር) እያለ የተናገረውን ወደናተ ላድርስ።

📌ይህ የዶ/ር ንግግር ከዚህ ቀደም በቤታችን ተለጥፎ ነበር(ጠ/ሚ ከመሆኑ በፊት)

"ታሪክ መማሪያ ሲሆን፣ ለነገ ድልድይ የምንሰራበት ሲሆን ጠቃሚ ነው፡፡ ታሪክ ዛሬን የሚያበላሽ ከሆነ ግን አደገኛ ነው፡፡ አሁን ያለው የኢትዮጵያን ፖለቲካም ሲታይ በአብዛኛው መልካም ነገርን የሚደምር አቅም ሳይሆን ያለችውን ትንሽ ስንክሳር፣ ያለችውን ትንሽ ጥፋት የሚያጎላና የበለጠ ችግር ለመፍጠር የሚታትር ሆኖ ይታያል፡፡ ይሄ አደገኛ ነው፡፡ በተለይ ወጣቱ በከፍተኛ ደረጃ ማስተዋል የሚገባው ነገር ከታሪክ ተምሮ ራሱን ለመለወጥ ራሱን ለማሻሻል የማይጠቀምበት ከሆነ ታሪክ የጥፋት ምንጭ ከሆነ ታሪክ አይደለም፡፡ አሁን ያለው ወጣት ሌላ አገር የለውም፡፡ አሁን ያለው ወጣት ሌላ የሚያስባት አገር ካለች ለመማር፣ ገንዘብ ለማግኘት ይሆናል እንጂ የመጨረሻ ማረፊያው የራሱ አገር ናት፡፡ ይቺን አገር በትክክል አሁን መቀበል፣ መረከብ፣ መስራት በዚያም መገልገልና መልሶም ለሚቀጥለው ማስረከብ ግዴታው መሆኑን ማሰብ አለበት፡፡ ወጣቱ በምክንያት የሚሞግት፣ ነገሮችን በምክንያት የሚያይ… ባልታመነ መረጃ፣ ባልታመነ ዳታ ለፀብ ራሱን የሚያዘጋጅ ሳይሆን እውነተኛ መረጃም ቢመጣ ሁለት ሶስት አመራጮችን አይቶ ለተሻለ ነገር ራሱን ማዘጋጀት አለበት፡፡ ሁልጊዜ ወደኋላ መለስ ብለን የምናየው ነጋችንን ለመስራት መሆን አለበት፡፡ ነጋችንን የሚያበላሽ ኋላ ተገቢ ስላይደለ፣ መሆንም ስለሌለበት ወጣቶች ከማንም በላይ ይሄ አገር የእነሱ ነው፤ መጠበቅ ያለባቸው፣ መንከባከብ ያለባቸው እነሱ ናቸው፤ ያላቸውን ጉልበት በመደመር ለልማት፣ ለሰላም፣ #በጣም_ውብ ለሆነች #አገር ቢገለገሉባት ጠቃሚ ነው የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡"

◾️ዶክተር አብይ አህመድ (የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia