THIQAH
13K subscribers
2.61K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
ግሪክ ባጋጠማት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጠወቀጥ በሀገሪቱ ቱሪዝም እንቅስቃሴዋ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮባታል ተባለ፡፡

ከቀናት በፊት በውጭ ቱሪስቶች በስፋት የሚጎበኘው የሳንቶሪኒ ደሴት ለተከታታይ ሰባት ጊዜ  በሬክተር ስኬል ከ4 እስከ 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎ ባለስልጣናት የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋውን ተከትሎ ከ11,000 የሚበልጡ ነዋሪዎች ከሳንቶሪኒ ደሴት መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡  
#france24

@ThiqahEth
👍14
ዩክሬን የመሬት ስር ማዕድኗን ለአሜሪካ ለመስጠት ተስማማች፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኪቭ በጦርነቱ ከአሜሪካ የተደረገላትን ድጋፍ ለማካካስ ማዕድኗን መስጠት እንዳለባት ባቀረቡት ሀሳብ መሰረት ዛሬ ተፈጻሚ መሆኑን ነጩ ቤተመንግስት አስታውቋል፡፡

17 አይነት ናቸው የተባሉት ማዕድናቶቹ 500 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ይገመታሉ ተብሏል፡፡

ማዕድናቶቹ ለኤሌክትሪክ መኪና ምርት፣ አውሮፕላን ሞተር፣ የህክምና ቁሳቁስ፣ ለነዳጅ ማጣያና ሌሎች የሚሳዔልና ራዳር ምርት እንደሚያገለግሉ ተገልጿል፡፡  
#france24

@ThiqahEth
😡38😁21😢8🤔6👍5😱32
"ብዙ ሀገራት ከአለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) አባልነት እንደሚወጡ ተስፋ አደርጋለሁ" - ኔታንያሁ

የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያም ኔታንያሁ ወደሀንጋሪ በማቅናት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ኔታንያሁ "የእርሰዎ አመራር ለእስራዔልና ለአይሁድ ህዝብ የሰጠውን አክብሮት አመሰግናለሁ፤ ሁሉም የድሞክራሲ ወዳጆች ይህን በሙስና የተጨማለቀ ተቋም እንደሚታገሉት አምናለሁ" ብለዋል፡፡

ሀናጋሪ የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ኔታንያሁን በቁጥጥር ስር እንድታውል ብትታዘዝም በተቃራኒው ከአባልነት መውጣቷ አስታውቃለች፡፡

ኦርባን በበኩላቸው የአለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ያወጣውን የእስር ትዕዛዝ "ፖለቲካዊ አላማን ያነገበ ነው" ሲሉ ተችተዋል፡፡
#france24

@ThiqahEth
👍35😡27🤔31😱1😢1
"ህንድ በካሽሚር ግዛት ጥቃት መፈጸሟ የማይቀር ነው" - ፓኪስታን

የፓኪስታን ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አታውላህ ታራር ኢስላማባድ ስለ ጥቃቱ "ታማኝ የደህንነት መረጃ" አላት ሲሉ ተናግረዋል።

ታራር አይቀርም ላሉት ጥቃት ሀገራቸው ፓኪስታን "ወሳኝ ምላሽ" ትሰጣለች በማለት አስጠንቅቀዋል።

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ "ሙሉ የዘመቻ ነፃነት" ሰጥተዋል በማለትም ወንጅለዋል።  
#france24

@ThiqahEth
👍17🔥1
ፑቲን እና ዘለንስኪ ከጦርነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊገናኙ ነው ተባለ።

ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን አቻቸው ቮለድሚር ዘለንስኪ ጋር "ቀጥተኛ ውይይት" ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።

የቀጥታ ውይይቱ ሜይ 15 በመጪው ሀሙስ'ለት እንዲደረግ ቀነገደብ ተቆርጦለታል ተብሏል።
#france24

(ጉዳዩን ተከታትለን መረጃ እናቀብላችኋለን)

@ThiqahEth
🔥11👍65🥰3😁3🤔2🙏1
"አዲስ፣ አካታች እና ሰላማዊ ሶሪያን ማየት እንፈልጋለን"  - ካጃ ካላስ

የአውሮፓ ህብረት በሶሪያ ላይ የጣላቸውን ማዕቀቦች ለማንሳት ተስማማ።

ህብረቱ በጦርነት የተጎዳችውን ሶሪያን መልሶ ለመገንባት ያግዛል በማለት ነው የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን ለማንሳት የወሰነው።

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ካጃ ካላስ፣ "አዲስ፣ አካታች እና ሰላማዊ ሶሪያን ማየት እንፈልጋለን" ሲሉ በኤክስ ገፃቸው አስፍረዋል።

ህብረቱ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው አሜሪካ በሶሪያ ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች እንደምታነሳ ካስታወቁ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።
#france24

@ThiqahEth
👍18🥰21🤔1😡1
"የተሰጠኝን ኃላፊነት ለመልቀቅ ወስኛለሁ" - ኤለን መስክ

የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ቢሊየነሩ መስክ ከመንግስት ኃላፊነት ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስታወቁ።

"በነበረኝ ጊዜ አላግባብ የሚባክኑ ወጭዎችን እንድቀንስ እድል የሰጡኝን ፕሬዝዳንት ትራምፕን አመሰግናለሁ" ሲሉ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በፕሬዝዳንት ትራምፕ የመንግስት አቅም ድፓርትመንት (DOGE) ኃላፊ ተደርገው የተሾሙት መስክ በአሜሪካ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚሰሩ ሰራተኞችን መቀነሳቸውና አንዳንዶቹን ቢሮዎች ከነአካቴው በመዝጋት ሰራተኞች እንዲበተኑ ማድረጋቸው ከፍተኛ ትችት አስከትሎባቸዋል።  

በወቅቱ የአሜሪካ አስተዳደር ተፅዕኖ ፈጣሪ ናቸው የሚባሉት መስክ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በውጭ ሀገራት ላይ በሚጥሉት ታሪፍ የተነሳ የድርጅታቸው ቴስላ ምርቶች በአለማቀፍ ገበያ ከእስከዛሬው በተለየ መልኩ ለኪሳራ ተዳርገዋል።
#france24

@ThiqhEth
24👏9😱3😡3😢2
ትራምፕ 500,000 ስደተኞችን እንዲያባርሩ ከፍተኛው ፍርድቤት ወሰነ።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድቤት የአራት ሀገራት ማለትም ኩባ፣ ሀይቲ፣ ኒካራጉዋና ቬንዙዌላ ስደተኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ መብትን አንስቷል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የነበራቸው 350,000 የቬኔዙዌላ ስደተኞችን ከሀገር እንዲያስወጡ ፍቃዱን ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ከሀገር የሚያስወጣቸው ስደተኞች ብዛት አንድ ሚሊዮን ደርሷል ተብሏል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፕሬዚዳንቱን የስደተኞች በኃይል ማስወጣት እርምጃ የሰብዓዊ መብት አያያዝን ይጣረሳል በሚል ሲቃወም ቆይቷል።
#france24

@ThiqahEth
😢157😡2
ዩክሬን በ11 የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎቿን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች።

ዜጎቹ እንዲለቁ ማሳሰቢያ የተሰጠባቸው ሁሉም ቀበሌዎች ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ውሳኔው ሩሲያ በነዋሪዎቹ ላይ የምታደርሰው የቦምብ ጥቃት ባለመቋረጡ የተላለፈ መሆኑ ተገልጿል።
#france24

@ThiqahEth
😢11🤔43🕊3😱1
"ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ አይደለም" - አሜሪካ

"ማዕቀቡ በግፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው" - የአውሮፓ ህብረት

አሜሪካ "ገለልተኛ ተቋም አይደለም" ባለችው በአለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አራት ዳኞች ላይ ማዕቀብ ጣለች።

ዳኞቹ በአሜሪካ የሚገኝ ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል።

የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ፣"ማዕቀቡ በግፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው" ሲል ማዕቀቡን ተችቷል።

ህብረቱ "የዳኝነት ባለሙያዎቹ ያለጫና በነፃነት መስራት ይኖርባቸዋል" ሲል የአሜሪካን ውሳኔ ተቃውሟል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ ላይ ያወጣውን የእስር ማዘዣ ተቃውመዋል።  
#france24

@ThiqahEth
😢138👏6🤔3🙏1
THIQAH
#Update "በበረራ ከጀመርን ከ30 ሰከንድ በኋላ የሚረብሽ ድምፅ ተሰማ፣ ወዲያውኑ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፣ ነገሮች በፍጥነት ነው የተፈጠሩት" - ታዕምረኛው ራመሽ 242 ሰዎችን ጭኖ ነበር የተባለው አውሮፕላን በመከስከሱ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው በስፋት ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል ተብሏል። ቪሽዋሽ ኩማር ራመሽ የተባለው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ግለሰብ በህይወት በመገኘቱ…
"የተሰማው ዜና አሳዛኝ ነው፤ መንግስታችን ጉዳዩን በቅርበት ይከታተላል" - አውስትራሊያ

ከህንድ ወደ እንግሊዝ ሲበር የነበረው አውሮፕላን በደረሰው አደጋ የ241 ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ የሀገራት መሪዎች አስተያየት ሰጥተዋል።

ምን አሉ?
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ "በተፈጠረው አደጋ ከፍቶናል። ከቃላት በላይ ልብ ሰባሪ ነው፣ ለተጎጂ ቤተሰቦች ሀዘኔን ለመግለጽ እወዳለሁ።"

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር፣ "ብዙ እንግሊዛዊያንን ይዞ የነበረው አውሮፕላን መከስከሱ አስደንግጦናል፣ በዚህ የጭንቅ ጊዜ ከተጎዱት ቤተሰቦች ጎን እቆማለሁ።"

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሸሪፍ፣ "ሀዘኔን መግለጽ እፈልጋለሁ፣ በእውነቱ ልብ ሰባሪ ነው።"

የባንግላዴሽ ጊዚያዊ መሪ መሀመድ የኑስ "በየትኛውም ጊዜ ከህንድ ህዝብና መንግስት ጎን መቆማችንን እንገልፃለን።"

የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን፣ "ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሞድ አውሮፓ በዚህ የሀዘን ጊዜ ከእርስዎ እና ከህዝቡ ጋር ይቆማል።"

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ "በአውሮፕላን አደጋው የተሰማኝን ሀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ፣ መፅናናትን እመኛለሁ።"

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳን፣ "ለተጎጂ ቤተሰቦችና ለጠቅላይ ሚኒስትር ሞድ መፅናናትን እመኛለሁ።"

የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንኖቶኒ አልባኔዝ፣ "የተሰማው ዜና አሳዛኝ ነው፤ መንግስታችን ጉዳዩን በቅርበት ይከታተላል።"

የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካኤል ማርቲን፣ "በአውሮፕላን አደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦቻቸውን ማሰብ ያስፈልጋል" በማለት ሀዘናቸውን ገልጸዋል። 
#france24

@ThiqahEth
13🙏4
የቡድን 7 አባል ሀገራት ስብሰባ በካናዳ መካሄድ ጀመረ።

የኢራንና የእስራኤል ግጭት እንዲሁም የንግድ ጦርነት መጧጧፍ የስብሰባው አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በአልበርት ከተማ የተሰባሰቡት መሪዎቹ  ትራምፕ በተለይ በንግድ ዙሪያ ያልተጠበቀ ውሳኔ ሊያሳልፉ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ መሆናቸው ተገልጿል። #france24

@ThiqahEth
🤔54🕊2😡2
"ኢራን በ12 ቀኑ ጦርነት የተወሰኑ የኑክሌር ማብላያ ቁሳቁሶች ወድመውባታል" - ዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ

"ኢራን የዩራኒየም ምርትን በወራት ውስጥ ልትመልስ ትችላለች" - ተመድ

ኢራን በእስራኤል እና አሜሪካ ከደረሰባት ጥቃት በኋላ በቅርቡ በአዲስ መልኩ ዩራኒየም የማምረት ስራ እንደምትጀምር የተመድ ኑክሌር ተቆጣጣሪ ቡድን አስታውቋል።

ቡድኑ አክሎ፣ "ኢራን የዩራኒየም ምርትን በወራት ውስጥ ልትመልስ ትችላለች" ሲል ገልጿል።

የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ራፋይል ግሮሲ ደግሞ፣ "ኢራን በ12 ቀኑ ጦርነት የተወሰኑ የኑክሌር ማብላያ ቁሳቁሶች ወድመውባታል" ብለዋል። 
#france24

@ThiqahEth
16👏2🤔2😱1🙏1
የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኔታንያሁን የፍርድ ቤት ቀጠሮ አራዘመ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተራዘመው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኔታንያሁ ክስ እንዲቋረጥ ጥሪ ማቅረባቸው ከተሰማ ከቀናት በኋላ ነው።

ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ባይገለፅም በዚህ ሳምንት ይዞት የነበረውን ክስ የማድመጥ ቀጠሮ ላልታወቀ ጊዜ ማራዘሙ ተሰምቷል።

አሁንም ቢሆን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በአሜሪካ ጫና የመጣ ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለበርካታ አመታት የቆየ የሙስና ክስ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
#france24

@ThiqahEth
16🤔7😡4🕊2
የደቡብ አውሮፓ ሀገራት በከፍተኛ ሙቀት እየተሰቃዩ ነው ተባለ።

የሙቀት መጠኑ ከእስካሁኑ በተለየ መልኩ 40 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ ወይም 104 ድግሪ ፋራ ናይት መድረሱ ተመላክቷል።

ጣሊያን፣ ስፔን እና ግሪክ በዋናነት በከፍተኛ ሙቀት የተጎዱ ሀገራት ሆነዋል ተብሏል።
#france24

@ThiqahEth
12😢6😱3🕊2🤔1😭1
አሜሪካ የሶሪያን መንግስት ከሽብርተኝነት ዝርዝር አወጣች።

የትራምፕ አስተዳደር የበሽር አላሳድን መንግስት በሀይል አስወግዶ ስልጣን ላይ የሚገኘው የፕሬዝዳንት አህመድ አልሻራ ሀያት ታህሪር አልሻም (HTS) መንግሥት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲወጣ መወሰኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርክ ሩቢዮ አስታውቀዋል።

ሀያት ታህሪር አልሻም (HTS) በአለማቀፍ ሽብርተኝነት የተፈረጀው የአልቃይዳ ክንፍ ነው በሚል በሽብር ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ ተካቶ ቆይቷል።
#france24

@ThiqahEth
🕊169🙏2
ለ43 አመታት ካሜሩንን የመሩት ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ አስታወቁ።

የ92 አመቱ የካሜሩን ፕሬዚዳንት ቢያ ለስምንተኛ ጊዜ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ቢያ በቅርቡ በገጠማቸው የጤና እክል ከህዝብ ርቀው እንደቆዩ ተገልጿል።

ፖል ቢያ ከእድሚያቸው አንፃር ሀገር መምራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ያሉ የሀገሪቱ ዜጎች የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ ተቃውመዋል።

ካሜሩን ከሶስት ወራት በኋላ ጥቅምት ላይ ብሄራዊ ምርጫ ታካሂዳለች ተብሎ ይጠበቃል።
#france24

@ThiqahEth
😡177😭4👏3🤔3🕊2
"ፈረንሳይ ፍልስጤም ሀገር እንድትሆን ያቀረበችውን እቅድ አንቀበልም" - አሜሪካ

ፍልስጤም በመጪው መስከረም የሀገርነት እውቅና ማግኘት አለባት ሲሉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ በቀጠናው ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘው ሉዓላዊነት ሲረጋገጥ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ፣ "ለሀማስ እድል የሚሰጥ ትርጉም የለሽ" ሲሉ የማክሮንን ንግግር አጣጥለውታል።

"ፈረንሳይ ፍልስጤም ሀገር እንድትሆን ያቀረበችውን እቅድ አንቀበልም" በማለትም ገልጸዋል።
#france24

@ThiqahEth
😡20👏193🕊3🙏1
እስራኤል ለሦስት ቀናት "ታክቲካዊ" ያለችውን የተኩስ አቁም አወጀች።

የእስራኤል ጦር ከዛሬ ጀምሮ በቀጣዮቹ ሦስት ቀናት ለ10 ሰዓት ያክል ግጭት እንደሚያቆም ገልጿል።

ይህ ውሳኔ በእስራኤል ክልከላ ምክንያት ወደ ጋዛ እርዳታ ባለመግባቱ የረሃብ አደጋ ተጋርጧል መባሉን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለተመድ በፃፉት ደብዳቤ በጋዛ ለተከሰተው ረሃብ መንግስታቸው ላይ የሚደርሰው ውንጀላ እንዲቆም ጠይቀዋል።  #france24

@ThiqahEth
🤔54🕊4🙏2👏1
በቻይና ድንገተኛ ጎርፍ የ30 ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ ከ80,000 በላይ አፈናቀለ።

በቤጂንግ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ወደ ሀቤይ፣ ጂሊን እና ሻንዶንግ ግዛቶች ተስፋፍቷል ተብሏል።

ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በምዩን ከተማ እንደሆነ ተመልክቷል።

በሦስቱም ከተሞች ትላልቅ የመሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። #xinhua #france24

@ThiqahEth
😢136🙏4🤔2😱2