THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ሲካሄድ የነበረው ውይይት መጠናቀቁን ሁለቱም ወገኖች አረጋገጡ።

በዚህም፣ "ውይይቱ በጣም ውጤታማ እና ገንቢ ነበር" ስትል አሜሪካ ገልጻለች።

ኢራን በበኩሏ፣ "ድርድሩ በብዛት ያተኮረው በኑክሌር ፕሮግራም እና ማዕቀብን ስለማንሳት ብቻ ነው" ብላለች።

ሀገራቱ በቀጣይ ሳምንት በድጋሚ ለመወያየት ቀጠሮ መያዙን ገልጸዋል። 
#morningstar #digitaljournal

@ThiqahEth
👍9🥰2🤔2
በካምቦዲያ እና ታይላንድ ጦርነት የሟቾች ቁጥር ወደ 33 ከፍ ማለቱ ተገለጸ።

በካምቦዲያ በኩል 13 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 71 የሚሆኑት ተጎድተዋል ተብሏል።

በታይላንድ በኩልም በተመሳሳይ 6 ወታደሮችን ጨምሮ 14 ንጹሐን በድምሩ 20 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

በዚህ ጦርነት ከታይላንድ 138,000 ዜጎች፣ ከካምቦዲያ ደግሞ 35,000 ዜጎች መፈናቀላቸው ተመልክቷል።

የሁለቱ የደቡብ እስያ ሀገራት ጦርነት ከተቀሰቀሰ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል።  #digitaljournal

@ThiqahEth
8🕊3😱1😢1😡1