''የሆነ ቀን ዩክሬን የሩሲያ ሆና ልናያት እንችላለን'' - ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የዩክሬንን ባለስልጣናት፣ ''ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ ላያደርጉም ይችላሉ፤ አንድ ቀን የሩሲያ ሊሆኑ ይችላሉ ላይሆኑም ይችላሉ'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ ዩክሬን በጦርነቱ ከአሜሪካ የተደረገላትን ወደ 500 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ድጋፍ፤ ያሏትን ማዕድናት በካሳ መልክ እንድታቀርብ አዘዋል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንድሪ የርማክ በበኩላቸው፣ ከሩሲያ ጋር ለሚደረገው ስምምነት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፤ የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ #aljazeera #associatedpress
@ThiqahEth

"ለገጠመን የኑሮ ውድነት ችግር ጥብቅ የሞነታሪ ፖሊሲ መከተል ግድ ይለናል'' - የህንድ ባንክ
ህንድ ሁሉም ባንኮች ወለድ እንዲያቆሙ አዘዘች፡፡
የህንድ ማዕከላዊ ባንክ የኢኮኖሚ ቀውስን ለመግታት በሚል ለመጀመሪያ ጊዜ የባንክ ወለድ እንዲቀር ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡
የባንኩ ገዥ ሳንጃይ ማልሆትራ፣ ''ለገጠመን የኑሮ ውድነት ችግር ጥብቅ የሞነታሪ ፖሊሲ መከተል ግድ ይለናል'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ማልሆትራ፣ ''የዋጋ መረጋጋትን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እና የፋይናንስ መረጋጋትን ለመፍጠር የማክሮ ኢኮኖሚክ መሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል'' ብለዋል፡፡
በህዝብ ቁጥር ከዓለም አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው እስያዊቷ ሀገረ ህንድ የምጣኔ ሃብት እድገቷ ላለፉት አምስት ተከታታይ አመታት እየቀነሰ መምጣቱን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡ #aljazeera

ኒውዝላንድ፣ ''ኢንቨስተርስ ፕላስ ቪዛ (IPV)'' የተሰኘ አዲስ የቪዛ አገልግሎት አስተዋወቀች፡፡
አዲሱ የቪዛ ሲስተም ለኢንቨስተሮች ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን (FDI) ለመሳብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
''ኒውዝላንድ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ለማሳየት ይጠቅማል'' ያሉት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና እድገት ሚኒስትር ኒኮላ ዊሊስ፣ አዲሱ ኢንቨስተርስ ፕላስ ቪዛ (IPV) ከመጪው ሚያዚያ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡
የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ኢሪካ ስታንፎርድ፣ ''አዲሱ የቪዛ ፕሮግራም በዚህ በሰለጠነ ዓለም ኢኮኖሚ ካፒታልን ለመሳብ ይጠቅማል'' ብለዋል። #nairametrics

ፈረንሳይ በአይቮሪ ኮስት ያለውን ብቸኛውን የጦር ሰፈር "ለቃ ልትወጣ ነው" ተባለ፡፡
ፈረንሳይ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኘውን ብቸኛውን የፖርት ቦውት የጦር ሰፈር በቅርቡ አሳልፋ እንደምትሰጥ ተዘግቧል፡፡
ፈረንሳይ ጦሯ እንደምታስወጣ ያስታወቁት አይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታሬ ናቸው፡፡
ውሳኔው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከቀድሞ ቅኝ ገዥ ፈረንሳይ ጋር ያላቸውን ወታደራዊ ግንኙነት የማቋረጥ ሂደት አካል ነው ብለዋል፡፡ #rtl

"ዩክሬን በድርድሩ ሂደት ግዛቶችን ለመቀያየር ተዘጋጅታለች'' - ፕሬዜዳንት ዘለንስኪ
''ሩሲያ የግዛት መቀያየር ሃሰብን ፈጽሞ አትቀበለውም'' - ድሜትሪ ሜድቬዴቭ
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት የሰላም ድርድር ከስድስት ወራት በፊት የተቆጣጠረችውን የኩርስክ ክልል ይዞታዎች ለመመለስ መዘጋጀቷን ተናግረዋል፡፡
''በምላሹም ሩሲያ ኬርሶን፣ ሉሃንስክ እና ዛፓሮዥያን ለቃ እንደምትወጣ እንጠብቃለን'' ብለዋል ዘለንስኪ፡፡
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ድሜትሪ ፔስኮቭ ደግሞ፣ ''ሩሲያ ግዛቶቿን የመለዋወጥ ሀሳብ ኑሯት አያውቅም፤ ወደ ፊትም አይኖራትም'' ብለዋል፡፡
በሩሲያን ግዛት የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮች ''ወይ ይወጣሉ ወይ ይደመሰሳሉ'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡ #kyivpost #thenewarab

''ሀማስ ታጋቾችን እስከ ቅዳሜ ድረስ ካልለቀቀ ስምምነቱ ይፈርሳል'' - እስራዔል
''እስራዔል ስምምነቱን ቀድማ ስለጣሰች ታጋቾችን የመልቀቅ እቅዴን አዘግይቸዋለሁ'' - ሀማስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኒታንያሁ እስራዔላዊ ታጋቾች እስከ ቅዳሜ እኩለቀን ድረስ ካልተለቀቁ እስራዔል እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቀዋል፡፡
ኒታንያሁ ከብሄራዊ የጸጥታ ኮሜቴው ጋር ባደረጉት ስብሰባ በአሁኑ ወቅት 76 ዜጎች በሀማስ እገታ ስር መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ሀማስ በበኩሉ፣ እስራኤል ስምምነቱን ቀድማ ስለጣሰች ታጋቾችን የመልቀቅ እቅዴን አዘግየቸዋለሁ" ብሏል።
ወደ ፊትም ዝርዝር መረጃዎች እንደሚያሳውቅ ገልጾ፣ ለስምምነቱ መጣስ እስራዔልን ተጠያቂ አድርጓል፡፡#scroll

ኮንጎ ለሩዋንዳ አየር መንገድ የአየር ክልሏን ዘጋች፡፡
ድሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለኤም 23 "አማጺ ቡድን ትደግፋለች" በማለት የምትከሳት ሩዋንዳን በስሟ የተመዘገቡ አውሮፕላኖች የአየር ክልሏን መጠቀም እንዳይችሉ ሙሉ በሙሉ ዘግታለች፡፡
የሩዋንዳ አየር መንገድ በበኩሉ ደህንነታቸው የተጠበቁ አማራጮችን እያማተረ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ሩዋንዳ፣ "የኮንጎ መንግስት ለገጠመው ውድቀት በሩዋንዳ ላይ እያሳበበ ነው" ስትል የሚቀርብባትን ውንጀላ አጣጥላለች፡፡
ሩዋንዳ በ2022 ወደ ኮንጎ የምታደርገውን በረራ በራሷ ውሳኔ አቁማ ነበር፡፡ #allafrica

''በየአመቱ ወደ 400,000 የሚጠጉ ህጻናት በካንሰር በሽታ ይያዛሉ'' - ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም
በመላው ዓለም በካንሰር በሽታ የሚጠቁት ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)፣ ዓለም ዓቀፍ የጤና ጉዳዮችን አስመልክቶ በበይነመረብ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ቴዎድሮስ በመግለጫቸው፣ ''ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 90 % የሚሆኑ ህጻናት የመዳን እድል ሲኖራቸው በታዳጊ ሀገራት ግን የመዳን እድል ያላቸው ህጻናት 30 % ብቻ ናቸው'' ሲሉ አብራርተዋል፡፡
የመካከለኛ ገቢ እና አነስተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የህይወት አድን ህክምና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
"በየዓመቱ ወደ 400,000 የሚጠጉ ሆጻናት በካንስር በሽታ ይይዛሉ" ሲሉም ተናግረዋል። #peoplesgazette

የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።
ከአውሮፓውያን 2005 ጀምሮ ጅቡቲን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ዩሱፍ፣ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሔደውና ብርቱ ፉክክር በታየበት፣ እስከ ሰባተኛ ዙር ድረስ በዘለቀ ምርጫ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ በማግኘት ማሸነፍ ችለዋል።
የ60 አመቱ ዩሱፍ፣ የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን በማሸነፍ ኮሚሽኑን ለአራት ዓመታት እንዲመሩ ተመርጠዋል።
መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ በአፍሪካ አህጉር ለረጅም ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ብቸኛ ሰው ናቸው። #au #radiotamazuj

አሜሪካ 1600 ከባድ ቦምቦችን ለእስራኤል ላከች።
MK-84 የተሰኙ ከባድ ቦምቦችን የጫኑ መርከቦች በዛሬው እለት በእስራኤል የአየር ሀይል ዋና ቢሮ ተራግፈዋል።
በተያያዘ መረጃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ እስራኤል ይገኛሉ።
ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ ጋር ባደረጉት ውይይት በጋዛ የተኩስ አቁም ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል።
በአዲሱ ኃላፊነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የመጡት ማርክ ሩቢዮ በቀጣይ ወደ ሳዑዲ በማቅናት ከከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። #ynetnews #ashiraqalawusat

በሱዳን በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 200 ንጹሐን ተገደሉ፡፡
የሱዳን ጦር ጥቃቱን የፈጸመው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሆኑን የሀገሪቱ ጦር ቢያስታውቅም ከወደ "አማጺ ቡድኑ" በኩል ግን እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የለም፡፡
በዋይት ናይል ግዛት የተፈጸመው ጥቃት ለተከታታይ ሦስት ቀናት የቆየ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
ከሀገሪቱ ጦር ጋር የጦርነት ፍልሚያ ውስጥ የሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አብዛኛውን የምዕራብ ሱዳን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል። #timeslive