በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን ልኡክ የወላይታ ሶዶ ከተማን በዲጂታል ሶሉሽኖች ለማዘመን ያለመ ውይይት ከወላይታ ሶዶ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ እና ኃላፊዎች ጋር አድርጓል።
ዋና ስራ አስፈጻሚያችን የቴክኖሎጂን ትሩፋት አሟጦ በመጠቀም ተቋማትን በዲጂታል መፍትሔዎች በማዘመን የዜጎችን ሕይወት ለማቅለል ኩባንያችን ለሚያደርገው ጥረት የመስተዳድሩ እና የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በከተማዋ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት እውን ለማድረግ በተጀመረው ስራ፣ ቢሮዎችን በስማርት ኦፊስ ማዘመንን ጨምሮ የአገልግሎት ክፍያዎች፣ ትምህርት፣ የግብር አሰባሰብ፣ ቱሪዝም እና የከተማዋን ደህንነት በዲጂታል በማዘመን ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን ረገድ እንዲሁም በማህበራዊ ኃላፊነት በወላይታ የተከናወኑ ተግባራት በመስተዳድሩ የተደነቀ ሲሆን ይህም በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#Wolaita #SmartCity #GSMA #ITU #WorldBank #OECD

👍74❤19👏9🙏9💯4👌3😁1
እነሆ #5G በወላይታ ሶዶ!
በወላይታ ሶዶ የ5ጂ ሞባይል አገልግሎት ጅማሮ በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች አብስረናል!
የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ (5G) አገልግሎት መጀመር በወላይታ ሶዶ ማብሰራችንን ተከትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የታደሙበት፣ በከተማዋ ህዝብ አብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ ጅማሮ ማብሰሪያ የመንገድ ላይ ትርኢት መርሐ ግብሮችን አከናውነናል፡፡
የ #ወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እንዲሁም ለነበረን ስኬታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!
#5ጂ_በወላይታ_ሶዶ
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#5G #Wolaita #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF

👍76❤12👏3