telebirr
269K subscribers
5.1K photos
102 videos
78 files
1.71K links
Easy, Fast, Convenient, and Secure.

One App for All your needs!

Download the telebirr SuperApp

📱 126 (SMS)

🌍 https://www.Ethio telecom.et/telebirr
Download Telegram
#5ጂ በቢሾፍቱ ተጀመረ!!

ኩባንያችን የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የሆነው የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ ማስጀመሩን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል!

በዛሬው እለት ይፋ ያደረግነው የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ ኩሪፍቱ ወተር ፓርክ፣ በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ሰንሻይን፣ ግራር ሜዳ እና የረር የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር የሚገኙ አካባቢዎች የሚሸፍን ነው፡፡

የአገልግሎቱ ተግባራዊ መሆን እያደገ የመጣውን የደንበኞች ዳታ ፍላጎት ለማስተናገድ ከማስቻሉ ባሻገር ተሞክሮን የሚጨምሩ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ የዜጎችን ህይወት ለማዘመን እና ቢዝነስን ለማቀላጠፍ እንዲሁም አዳዲስ የዲጂታል ሥራ እድሎችን በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል፡፡

የ5ጂ አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነት ያለው፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን በእጅጉ በመቀነስ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎችን ከማዘመን በተጨማሪ ለሀገራችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ እንደ ግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት ያሉ ዘርፎችን አሰራር በማቀላጠፍ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፡፡

ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስችሉ ቀፎዎች በመጠቀም በእጅግ ፈጣኑ ኔትወርክ አስደሳች ተሞክሮ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡

ቀደም ሲል የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂግጂጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና እና አርባ ምንጭ ከተሞች ማስጀመራችን ይታወሳል፡፡

አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!


#ዲጂታል_ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ላይ

ለተጨማሪ: https://bit.ly/48PskNK
#Bishoftu #5G
👍14032😁9👏5🤩3👌3
የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን በማስመልከት የተለያዩ ደማቅ የመንገድ ላይ መርሐ ግብሮች አከናውነናል!

የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን ማብሰራችንን በማስከተል ከከተማዋ ነዋሪዎች እና ደንበኞቻችን ጋር በአብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ መንገድ ላይ ትርኢት እና የኮንሰርት መርሐ ግብሮች ተካሄደዋል፡፡

#ቢሾፍቱ ከተማ ሕዝብ፣ የከተማ መስተዳድር እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች የ5ጂ መርሐ ግብራችን ደማቅ እና ስኬታማ እንዲሆን ስላደረገላችሁልን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#5G #ቢሾፍቱ

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #Bishoftu #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍7112👏4😁3
ኢትዮ ቴሌኮም የስማርት ሲቲ (ስማርት ቢሾፍቱ) ፕሮጀክትን ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ!

የስማርት ቢሾፍቱ ፕሮጀክት በምዕራፍ ከተማዋን ለማዘመን የሚያስችል የክላውድ፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ያለው ኢንተርኔት፣ የኦፕቲካል ፋይበር እና ሌሎች የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ የመዘጋጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት እና የግብር አሰባሰብ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማዘመን እንዲሁም አስተማማኝ ደህንነት ያላት ከተማን ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አጽንኦት ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ሁሉንአቀፍ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባሻገር ክፍያዎችን በቴሌብር በቀላሉ በማስፈጸም ውጤታማነትን በእጅጉ ለማሳደግ የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤን ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተብራርቷል።

በተለይም ከተማዋን ለቱሪዝም መዳረሻነት፣ ለኮንፍራንስ ከተማነት፣ ለኢንዱስትሪ (Economic zone) እና ኢንቨስትመንት ያላትን አቅም በማሳደግ ተወዳዳሪነትን እንደሚጨምር እና የቢዝነስ እንቅስቃሴን በማሳለጥ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያሻሽል ተገልጿል።

#SmartCity #Bishoftu #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #GSMA #ITU
👍8024🙏4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን ማብሰራችንን በማስከተል ከከተማዋ ህዝብ ጋር በአብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ መንገድ ላይ ትርኢት እና የኮንሰርት መርሐ ግብሮች አካሄደናል፡፡

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #Bishoftu #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍5411👌2
በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን የሥራ አመራር ከቢሾፍቱ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ እና ኃላፊዎች ጋር በጋራ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኘውን የልማት እንቅስቃሴ ጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፣ የከተማ ማስዋብ እና አረንጓዴ ልማት የተመለከቱ ሲሆን የኮሪደር ልማቱ ከኩባንያችን መሰረተ ልማት ዝርጋታ ጋር በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑን በማድነቅ ይኸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አክለውም ኩባንያችን በልማቱ ከመስተዳድሩ ጋር በቅርበት በመስራት የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን እያዘዋወረ መሆኑን በመግለጽ የሚዘዋወሩ መስመሮችን ከነባሩ የኮፐር መስመር ደረጃውን ወደ ጠበቀ ፋይበር መሰረተ ልማት የማዘመን ሥራ እያከናወነ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በኩባንያችን እውን የተደረገው የ5ጂ አገልግሎት፣ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ስምምነት በከተማዋ ከሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ጋር ተደምሮ ከተማዋን ለቱሪዝም መዳረሻነት፣ ኮንፍራንስ ማእከልነት፣ ኢንዱስትሪ፣ ኢንቨስትመንት እንዲሁም ለነዋሪዎች ምቹ እና ተመራጭ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እና ተወዳዳሪነትን እንደሚጨምር ተገልጿል።

#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#SmartCity #Bishoftu #GSMA #ITU #WorldBank #OECD
👍5916👌2🤩1🙏1