Crohn's & Colitis Ethiopia
648 subscribers
52 photos
1 video
7 files
44 links
Crohn's & Colitis Ethiopia aims to serve as a hub for patients and families with IBD to learn, share and support eachother. Disclaimer: all information is for educational purposes only.
Questions? Talk to us at @IBDETHIOPIA
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ #አረንጓዴሻይ

አረንጓዴ ሻይ በየሱቁ እና ሱፐር ማርኬት የሚገኝ የሻይ አይነት ሲሆን ሻይ ቅጠሉ በተለያየ መልኩ ታሽጎ ለተጠቃሚ ይቀርባል።

ይህ ሻይ በቻይና፣ ጃፓን የመሳሰሉት አገራት ላይ ለብዙ ሺህ አመታት ሲጠቀሙበት ኖረዋል። የዚህ ሻይ ጥቅም በብዙ ሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ ማስረጃ ሲኖር ለልብ፣ ለአንጀት ጤና እንዲሁም ኮሌስትሮል የመቀነስ ሀይሉ፣ ካንሰር የመከላከል እንዲሁም የአንጀት ቁስለት ላይ ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር ቀርቧል።

አረንጓዴ ሻይን በቀን ስንት ግዜ ልጠቀም፣ ለኔ ይሆናል ወይ እንዲሁም ሻዩን ከመውሰድ በእንክብል መልክ ተዘጋጅቶ የቀረበው የአረንጓዴ ሻይ ከ ሻይ ቅጠሉ የሚለየውን ነገር ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማንበብ ይችላሉ።

የአረንጓዴ ሻይ ጣዕም ለማይወዱ እንዲሁም ለየት ባለ መልኩ መጠቀም ለሚሹ ከ ክሮንስ እና ኮላይተስ ግሩፕ የተወጣጣ ለየት ያሉ የሻይ፣ የጁስ የመሳሰሉትን አማራጮችን በቅዳሜ ለት @ibdeth ላይ ይዘን እንቀርባለን።

ተጨማሪ ለማንበብ https://telegra.ph/Green-Tea--Our-Gut-07-13

@tikvahethmagazine @ibdeth
#quickfact #አረንጓዴሻይ

አረንጓዴ ሻይ ስንጠጣ ከምንጠቀማቸው አማራጭ አሰራር መካከል የተወሰኑትን ዛሬ ወደናንተ ይዘን ቀርበናል።

እርሶ ከሚወዱት ቅመም ወይም ፍራፍሬ ጋር በመቀላቀል የአረንጓዴ ሻይን ጥቅም በተለያየ የአሰራር መንገድ ያግኙ።

የአረንጓዴ ሻይን ጣዕም ለማይወደው ወይም አልፎ አልፎ ለውጥ ባለ መልኩ ለመጠቀም አማራጮች ሲኖሩ ስኳር መጨመር ግን አይመከርም። ከስኳር ይልቅ ማር መጠቀም ይመከራል ሻዩ ለጤና ያለውንም ጥቅም ከፍ ያደርገዋል።

ስለአማራጮቹ የሚገልጹ ምስሎቹን ለማየት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ⬇️⬇️⬇️

https://telegra.ph/Green-Tea-Variations-07-15