FBC (Fana Broadcasting Corporate)
205K subscribers
63.3K photos
902 videos
23 files
55.4K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
ማዕከሉ የዲኤንኤ ምርመራና የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል – ም/ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፎረንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከል ለጎረቤት ሀገራትም የዲኤንኤ ምርመራና የአቅም ግንባታ ስልጠና አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ የተመረቀው የፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከል እንደ ሀገር የተጀመረው የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ሪፎርም በርካታ ስኬቶች…

https://www.fanabc.com/archives/271278
አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት ሂደት ኪነ-ጥበብ ትልቁን ሚና ይጫወታል – አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት ሂደት ጥበብ ትልቁን ሚና ይጫወታል ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለፁ፡፡ ‘ባህልና ኪነ ጥበብ ለህዝቦች አብሮነት እና ገፅታ ግንባታ’ በሚል መሪ ሀሳብ ከህዳር 7 እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ለሶስት ወር የሚቆይ ንቅናቄ በባህልና ስፖርት…

https://www.fanabc.com/archives/271281
ማዕከሉ ሰላምና ፍትህ ለማስፈን ተጨማሪ አቅም የሚሆን ነው – ኮ/ጄ ደመላሽ ገብረሚካኤል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራና ምርምር ልህቀት ማዕከል አስተማማኝ ሰላምና ፍትህ ለማስፈን ለሚከናወኑ ስራዎች ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራና ምርምር ልህቀት ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል፡፡ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በምረቃው…

https://www.fanabc.com/archives/271289
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለልጆቻችን ጠንካራ ሀገር ለማስረከብ ተቋም በመገንባት፣ በማስከበር እና በማስቀጠል ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሪፎርም ሥራዎች ኢትዮጵያን ያሻገሩ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በውስብስብ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊው አውድ ውስጥ የተካሄዱት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሪፎርም ሥራዎች ኢትዮጵያን ያሻገሩና ያጸኑ መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) እና ሌሎች አባላት እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ስትራቴጂክ አመራሮች በተገኙበት…

https://www.fanabc.com/archives/271300
Live stream finished (1 hour)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የታንዛኒን ብሔራዊ ቡድን ሳይመን ሀፒጎድ ምሱቫ እና ፋይሰል ሳሉም አብደላ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥሯል። በውጤቱ መሰረትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአምስት የማጣሪያ ጨዋታዎች በአራቱ…

https://www.fanabc.com/archives/271305
ኤ.ኤም ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ያመረታቸው ተሽከርካሪዎች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ በተገነባው ኤ.ኤም ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በድሬዳዋ ከተማ ያመረታቸው ተሸከርካሪዎች ተመረቁ፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር÷ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በድሬዳዋ በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስክ የሚሰማሩ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ብለዋል። ባለሃብቶቹ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች…

https://www.fanabc.com/archives/271308
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሳየች አይቼውና ቢኒያም መሐሪ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አትሌት አሳየች አይቼው እና አትሌት ቢኒያም መሐሪ አሸነፉ።

ውድድሩን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ያስጀመሩት ሲሆን፥ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በውድድሩ በሴቶች አትሌት አሳየች አይቼው በቀዳሚነት ስትገባ፤  አትሌት የኔዋ ንብረት ደግሞ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

በወንዶች ደግሞ ቢኒያም መሐሪ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ያሸነፈበትን ድል አስመዝግቧል።
የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ የስበት ማዕከል መሆን በጀመረችበት ወቅት የተካሄደ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ


አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል መሆን በጀመረችበት ወቅት የተካሄደ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የከተማችን አንዱ ድምቀት የሆነው 24ኛውን የታላቁ ሩጫ የጎዳና ውድድር ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ ብርቅዬ አትሌቶቻችን እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ማለዳ አስጀምረናል ብለዋል።

ታላቁ ሩጫ ላለፉት 24 ዓመታት ኢትዮጵያን ለዓለም እያስተዋወቀ የቆየ መሆኑን አስታውሰዋል።

የዘንድሮውን ውድድር ለየት የሚያደርገው አዲስ አበባ ተዉባ፣ መንገዶቿ ሰፍተዉ፣ አምረዉና ደምቀዉ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል መሆን በጀመረችበት ወቅት የተካሄደ መሆኑ ነው ሲሉም ገልጸዋል።