Ethio Verse
87 subscribers
57 photos
1 link
Read Design Share
@ethioverse
Download Telegram
አንዲት የውሃ ጠብታ
ገባች ከባህር ውስጥ ገብታ
ግን ያቺው ጠብታ ነች
ባህሩን ሙሉ ያደረገች
@ethioverse #Ethiopia #Tagor
በያንዳንዱ ሕፃን ልጅ ውስጥ አንድ ገና ያልተገለጸ ትልቅ ሰው አለ፡፡ ይህም ጊዜን የሚጠብቅ ነው፡፡ እኔ ግን ምንጩን መርምሬ በቅጡ ያልደረስኩበት ፤ በሄድሁበት ሁሉ የሚያጋጥመኝ በያንዳንዱ ትልቅ ሰው ውስጥ የሚወራጭ ሕፃን ልጅ ነው፡፡በተለይ “ሕፃናት” ወላጆችን እና የሀገር መሪዎችን ማየት በጣም ነው የሚያስፈራኝ፡፡ በያንዳንዱ ሕጻን ውስጥ የተሰወረውን ትልቅ ሰው በትክክል ካላሳደግነው ውሎ አድሮ በትልቅ ሰውነት ውስጥ የሚንፈራገጥ እንጭጭ ሕጻንን ማግኘታችን አይቀርም፡፡ በሕጻን ውስጥ የተሰወረውን ትልቅ ሰው ማሳደግ ደስታ ነው፡፡ በአዋቂ ሰውነት ውስጥ ከተደበቀ ሕጻን ጋር መኖር ግን ከሁሉ የከፋ መከራ ይመስለኛል፡፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ (የተቆለፈበት ቁልፍ)

@ethioverse #ethiopia #DrMihret #Attitude
በእኔ ልቅደም ትርክት የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን ጠቦ መሞት በቃን።
የጸደይ ወይን ሆኖ የሀቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!
@ethioverse #Pome #Ethiopia
Alem Emu Dere- Lefikrachin
Alem Emu Dere
ከአባል የተላከ

ርዕስ....ለፍቅራችን

@yeneta ግጥማችሁን መላክ ትችላላችሁ
Channel photo updated
እንኳን አደረሳችሁ

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው ቻናላችን በአዲሱ አመት በአዲስ ሎጎ በአዲስ አቀራረብ መመለሱን ስናበስር ከታላቅ ደስታ ጋር ነው።

አዲሱ አመት የሰላም እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ተመኘን።
ህይወት አንዳንዴ በከፍታ አንዳንዴ በዝቅታ ናት
አብርሀም ሊንከን

#EthioVerse
ፀሐይን እና ጨረቃን መመልከት የጠራ እይታ ምልክት አይደለም
የመብረቅ ነጎድጓድ ድምፅ መስማትም የብቁ ጆሮ ምልክት አይደለም ፡፡
ሰንዙ

#EthioVerse
ሌላ መንገድ በመፈለግ ጊዜህን አታጥፋ መንገድ በፊትህ ነው:: ተነስቶ መራመድ ያንተ ፋንታ
ነው::
ቅ/አውግሰጢኖስ

#EthioVerse
ትናንት ብልህ ስለነበርኩ አለምን ልለውጥ እጥር ነበር ዛሬ ግን ጥበብን ተማርኩና ራሴን ለመለወጥ በመስራት ላይ እገኛለሁ፡፡
— ሩሚ
@EthioVerse #Rumi #Change #Wisdom
ነገሮችን የምንመለከትበት መንገድ ከተለወጠ የምንመለከታቸው ነገሮች ይለወጣሉ፡፡
—— ዌይን ዳየር
#PointOfVIew #EthioVerse #WayneDyer
አንድ መጽሃፍ ፣ አንድ ብዕር ፣ አንድ ሕጻንና አንድ መምህር አለምን ሊለውጡ እንደሚችሉ ልናስተውል ይገባል
——— ማላላ ዩሳዛል
#OneBook #Book #Children #EthioVerse
ዕድሜያችን እየገፋ ስንሄድ የምንገነዘበው ነገር ሁለት እጅ የኖረን በአንዱ ራሳችንን በሌላው ደግሞ ሌሎችን እንድንረዳበት መሆኑን ነው
———- ኦድሪይ ሄበርን
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በጦርነት ከማሸነፍ የበለጠ ራስን ድል ማድረግ ትልቅ ድል ነው።
---- ደላይ ላማ
#Ethioverse #DalaiLama
ካለህ እንጂ ከሌለህ ነገር ጋር ደስታህን አታቆራኝ
——አለማየሁ ገላጋይ
ደሃው ወደ አንተ ሊለምን ሲመጣ ‘ራቁቱን ሆኖ የሚለምነው ሲያስመስል ነው‘ ትላለህ፡፡ እርሱን አታላይ ያደረገው ግን የአንተ ጭካኔ ነው፡፡ ርኅሩኅ ብትሆንለት ኖሮ አንተን ለማራራት ሲል እንዲህ ባልደከመ ነበር፡፡
እሱ እኮ በየቀኑ እየመጣ ይለምነኛል ብለህ አትበሳጭ በየቀኑ የሚለምንህ እርሱም እንደ አንተ በየቀኑ ስለሚበላ ነው’’
—— ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ከአምላክ ጋር የሚጓዙ ሁልጊዜም ቢሆን ካሠቡት ይደርሳሉ፡፡
—— ሔነሪ ፎርድ
ንግግርህ ምንም ያህል እውነተኛ ቢሆን በቁጣ ከተናገርክ ሁሉንም ነገር ታጠፋዋለህ
——ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ምስጢርህን ለራስህ ብቻ ያዘው
ወዳጅህ ሌላ ወዳጅ አለውና