TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአዳማ ከተማን ግብ ዮሴፍ ታረቀኝ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለወላይታ ድቻ የአቻነቱን ጎል ቢንያም ፍቅሩ አስቆጥሯል።

የአዳማ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ዮሴፍ ታረቀኝ በውድድር አመቱ ሰባት ግቦችን አስቆጥሯል።

አዳማ ከተማ በሰላሳ ሁለት ነጥቦች አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ በሰላሳ አንድ ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአርባምንጭ ከተማን ግብ ተመስገን ደረሰ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለፋሲል ከነማ የአቻነቱን ጎል በዛብህ መለዮ አስቆጥሯል።

የአርባምንጭ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ተመስገን ደረሰ በውድድር አመቱ ዘጠነኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ፋሲል ከነማ በሰላሳ አራት ነጥቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ አራት ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ሀይቆቹ በተከታታይ ያደረጓቸውን #አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም በሶስቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና በዚህ አመት በተመሳሳይ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው ስምንት አሸንፈው ሰባት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀድያ ሆሳዕና በሰላሳ ሁለት ነጥቦች #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ ሁለት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

አርባምንጭ ከተማ በተከታታይ ያደረጓቸውን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ወላይታ ድቻ በሰላሳ ሁለት ነጥቦች #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ አምስት ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀድያ ሆሳዕና በሰላሳ ሶስት ነጥቦች #ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልቂጤ ከተማ በሀያ ዘጠኝ ነጥብ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- አዳማ ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ ስድስት ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ቡናን ግብ መሐመድ ናስር ሲያስቆጥር ለለገጣፎ ለገዳዲ አማኑኤል አረቦ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ናስር በውድድር አመቱ አስረኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቦቹን ሰላሳ አምስት በማድረስ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ለገጣፎ ለገዳዲ በአስራ ሁለት ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ለገጣፎ ለገዳዲ ከ አዳማ ከተማ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ሀዋሳ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድን ግቦች ሲሞን ፒተር 2x ሲያስቆጥር ለሀዋሳ ከተማ የአቻነት ግቦችን ሰዒድ ሀሳን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ መድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ሲሞን ፒተር በውድድር አመቱ ስድስተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በሰላሳ አራት ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ መቻል ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ መቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክን ግቦች አብዱራህማን ሙባረክ 2x ሲያስቆጥር የመቻልን የአቻነት ግቦች እስራኤል እሸቱ እና ተሾመ በላቸው ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

መቻል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአስራ ሁለት ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአስራ ሁለት ነጥቦች ከኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊጉ መውረዳቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

ከደቂቃዎች በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ መካከል ሊካሄድ የነበረው የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በጣለው ከፍተኛ ዝናብ መዘዋወሩ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

ሀዋሳ ከተማ ከመቻል ጋር ያደረጉትን የሀያ ስድስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሀዋሳ ከተማን ግብ ተባረክ ሄፋሞ ሲያስቆጥር ለመቻል የአቻነቷን ግብ ምንተስኖት አዳነ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

መቻል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ በተመሳሳይ ሰላሳ አምስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ሀዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ መቻል ከባህርዳር ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በዛሬው ዕለት ከሚጠበቁ የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ ያገናኘው መርሐ ግብር ይገኝበታል።

ሁለቱ ቡድኖች በደጋፊዎቻቸው ፊት ታጅበው ያደረጉት ጨዋታ እስከ መጀመሪያው አጋማሽ ቢቀጥልም በስታዲየሙ በጣለው ዝናብ ጨዋታው ሊራዘም ችሏል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በነገው ዕለት ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ የሁለተኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እንደሚደረግ አክስዮን ማህበሩ አሳውቋል።

ከቀናት በፊት በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ባህርዳር ከተማ ሊያደርጉት የነበረው መርሐ ግብር በጣለው ከባድ ዝናብ ጨዋታውን ማካሄድ ሳይችል መቅረቱ የሚታወስ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ሲዳማ ቡና ከአራት ተከታታይ ድሎች በኋላ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሲዳማ ቡና በሰላሳ አራት ነጥብ #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ በሰላሳ ሶስት ነጥቦች አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ለአርባምንጭ ከተማ አህመድ ሁሴን ሲያስቆጥር የሲዳማ ቡናን የአቻነት ግብ አሸናፊ ፊዳ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሲዳማ ቡና በሰላሳ አምስት ነጥብ #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሰላሳ ነጥቦች አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

ፋሲል ከነማ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረገውን የሀያ ሰባተኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር መርሐ ግብር 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፋሲል ከነማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ስምንት ነጥቦችን በመሰብሰብ አምስተኛ ደረጃን ሲይዝ ወልቂጤ ከተማ በሰላሳ አራት ነጥብ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከመቻል ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአዳማ ከተማን ግቦች ዳዋ ሁቴሳ 2x እና አዲስ ተስፋዬ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለሀድያ ሆሳዕና የአቻነት ግቦችን ባዬ ገዛኸኝ 2x እና ሰመረ ሀፍተይ አስቆጥረዋል።

ባዬ ገዛኸኝ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ስምንት ከፍ ማድረግ ችሏል።

ሀድያ ሆሳዕና አርባ ነጥቦችን በመሰብሰብ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ በሰላሳ ሰባት ነጥቦች ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የፈረሰኞቹን ግቦች አቤል ያለው እና ቸርነት ጉግሳ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለጣናው ሞገድ አለልኝ አዘነ እና ፍራኦል መንግስቱ አስቆጥረዋል።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጨዋች ቸርነት ጉግሳ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቦቹን ሀምሳ ዘጠኝ በማድረስ ሊጉን መምራቱን ሲቀጥል ባህር ዳር ከተማ በሀምሳ አራት ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ መድን በአርባ ዘጠኝ ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፋሲል ከነማ በሰላሳ ዘጠኝ ነጥቦች ስድስተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ አዳማ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

ከቀናት በኋላ ሐሙስ በሚጀምረው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ላለመውረድ በሚደረገው አጓጊ ፉክክር ሁለት ጨዋታዎች በእኩል ሰዓት እንዲደረጉ አወዳዳሪው አካል ከውሳኔ ደርሷል።

ይህንንም ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ወልቂጤ ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በእኩል 9:00 ሰዓት እንዲደረጉ ከውሳኔ ተደርሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2015 ዓ.ም የውድድር አመት የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያደረጉት ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ ቡና የውድድር አመቱን አርባ ሶስት ነጥቦች በመሰብሰብ ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን በአመቱ ውስጥ አስራ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው አስር አሸንፈው ሰባት ደግሞ ሽንፈት አስተናግደዋል።

ፋሲል ከነማ በበኩሉ በተመሳሳይ አርባ ሶስት ነጥቦች በመሰብሰብ የውድድር አመቱን ያጠነቀቀ ሲሆን በአመቱ ውስጥ አስራ አንድ ጨዋታዎች አሸንፈው አስር አቻ ተለያይተው ዘጠኝ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

በሊጉ ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት ቡናማዎቹ አራተኛ እንዲሁም አፄዎቹ በግብ ክፍያ ተበልጠው አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe