ቼልሲ ሮሜሎ ሉካኩን መጥራት አይችልም !
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በጥር ወር በውሰት ለሮማ የሰጠውን ቤልጂየማዊ የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሎ ሉካኩ መጥራት እንደማይችሉ ተገልጿል።
ሰማያዊዎቹ በጥር ወር የፊት መስመሩን ለማጠናከር እያሰቡ የሚገኙ ሲሆን ሮሜሎ ሉካኩን በአማራጭነት እንዳይመለከቱ በውሉ ውስጥ በጥር የመጥራት አማራጭ እንደሌለ ተነግሯል።
ሮሜሎ ሉካኩ በዚህ አመት በሮማ ቤት እና በሀገሩ ብሔራዊ ቡድን በድምሩ አስራ ዘጠኝ ግቦች በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

" የትኛውንም ቡድን ማሸነፍ እንችላለን " ቴንሀግ
የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በድናቸው ነገ ምሽት ከባየር ሙኒክ ጋር ከሚያደርገው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ኤሪክ ቴን ሀግ በቆይታቸው ምን አሉ ?
- " አመቱን ስንጀምር ውድድሩን ስለማሸነፍ አላሰብንም መጀመሪያ ራሳችንን ማሸነፍ የምንችልበት ደረጃ ላይ ማስቀመጥ አለብን አሁን በሻምፒየንስ ሊግ ለመቆየት ማሸነፍ አለብን።
- ማንኛውንም ተጋጣሚ ማሸነፍ እንችላለን የኤቨርተን ፣ ቼልሲ እና ጋላታሳራይን ጨዋታ መመልከት ይቻላል ይህ ቡድን በትልቅ ደረጃ መንቀሳቀስ ይችላል።
- ቡድኑን ማሻሻል የእኔ ሀላፊነት ነው እኔ የተቻለኝን ሁሉ እሰጣለሁ ቡድኑም እንደዛው ፣ እንደ ባየር ሙኒክ አይነት ክለብ ስትገጥም ምርጡ አቋም ላይ መሆን አለብህ።
- ኦልድትራፎርድ ለተጋጣሚ ቡድን ጥሩ ቦታ አይደለም እኔ እስካለሁ ሁላችንም አብረን እንቆማለን ለቡድኑ ጉልበት ልንሰጠው ይገባል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

የካፍ አመታዊ ሽልማት ስነ ስርዓት ዛሬ ይካሄዳል !
ተጠባቂው የ 2023 የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ስነ ስርዓት ዛሬ ምሽት በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ የሚካሄድ ይሆናል።
የሽልማት ስነስርዓቱ በሞሮኮዋ ማራካሽ ከተማ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል።
በሽልማቱ ይፋ ይደረጋሉ ተብለው ከሚጠበቁ ሽልማቶች መካከል የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች የሚገኝበት ሲሆን ሞሀመድ ሳላህ ፣ ቪክቶር ኦሲሜን እና አሽራፍ ሀኪሚ በእጩነት ቀርበዋል።
ሌሎች የሚጠበቁ ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ?
- የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ
- የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ
- የአመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን

ኢብራሂሞቪች በአዲስ ሚና ወደ ሚላን ተመልሷል !
በቅርቡ ጫማውን የሰቀለው ስዊድናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ዝላታን ኢብራሂሞቪች በአዲስ ሚና ወደ ቀድሞ ክለቡ ኤሲ ሚላን መመለሱ ይፋ ተደርጓል።
ዝላታን ኢብራሂሞቪች በአዲሱ ሀላፊነት በኤሲ ሚላን ቤት አማካሪ ሆኖ መሾሙ ሲገለፅ ከክለቡ ከፍተኛ ባለድርሻ ጌሪ ካርዲናል ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተነግሯል።
ዝላታን ከሹመቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት " ለኤሲ ሚላን ያለኝ ፍቅር በጭራሽ አያበቃም በድጋሜ መመለስ ህልሜ ነበር።" ሲል ተደምጧል።

ዩናይትድ ተጨዋቾቹ ልምምድ አልሰሩም !
ማንችስተር ዩናይትድ ነገ ከባየር ሙኒክ ጋር ከሚያደርገው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፊት በሰራው የመጨረሻ ልምምድ ላይ ማርከስ ራሽፎርድ እና አንቶኒ ማርሻል አለመሳተፋቸው ተገልጿል።
የፊት መስመር ተጨዋቾቹ ማርከስ ራሽፎርድ እና አንቶኒ ማርሻል ልምምድ ያልሰሩት በህመም ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።
የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹ ቪክቶር ሊንድሎፍ በበኩሉ ወደ ልምምድ መመለሱ ተነግሯል።

TIKVAH-SPORT
የአርሰናል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል❓ በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የፕርሚየር ሊጉ መሪ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋች አራት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ቡካዩ ሳካ ፣ ካይ ሀቨርትዝ ፣ ሊያንድሮ ትሮሳርድ እና ዊሊያም ሳሊባ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸዉ። @tikvahethsport @kidusyoftahe
የአርሰናል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።
በዚህም መሰረት ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።
በዚህም መሰረት ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሲቲ ፉትቦል ግሩፕ አዲስ ክለብ ሊገዛ ነው !
የእንግሊዙን ክለብ ማንችስተር ሲቲ በባለቤትነት የያዘው ሲቲ ፉትቦል ግሩፕ ኢንቨስትመንት ተቋም አዲስ ክለብ ሊገዙ እንደሆነ ተገልጿል።
ተቋሙ የቱርኩን ክለብ ኢስታንቡል ባሻክሼሂር ክለብ ለመግዛት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
ሲቲ ፉትቦል ግሩፕ ኢንቨስትመንት ማንችስተር ሲቲ ፣ ጂሮና ፣ ሜልቦርን ሲቲ ፣ ሙምባይ ሲቲ ፣ ኒውዮርክ ሲቲ እና ሌሎች ክለቦችን በባለቤትነት ይዟል።

" ኦልድትራፎርድ መጫወት የብዙዎች ህልም ነው "
የባየር ሙኒክ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጀማል ሙስያላ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም መጫወት የብዙ ልጆች ህልም እንደሆነ ተናግሯል።
" ልጅ እያለሁ ኦልድትራፎርድ የሚደረግ ጨዋታ መመልከት ያስደስተኝ ነበር " ያለው ጀማል ሙስያላ " እዚህ ስታዲየም መጫወት የብዙ ልጆች ህልም ነው ነገ ምሽት ድባቡ ጥሩ እንደሚሆን አስባለሁ።"ብሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የባየር ሙኒክ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጀማል ሙስያላ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም መጫወት የብዙ ልጆች ህልም እንደሆነ ተናግሯል።
" ልጅ እያለሁ ኦልድትራፎርድ የሚደረግ ጨዋታ መመልከት ያስደስተኝ ነበር " ያለው ጀማል ሙስያላ " እዚህ ስታዲየም መጫወት የብዙ ልጆች ህልም ነው ነገ ምሽት ድባቡ ጥሩ እንደሚሆን አስባለሁ።"ብሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ማን ይሆናል ? የአፍሪካ የ2023 የአመቱ ምረጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ የመጨረሻ ሶስት እጩ ግብ ጠባቂዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት ካሜሮናዊው አንድሬ ኦናና ፣ ሞሮኳዊው ያሲን ቦኑ እና ግብፃዊው መሐመድ ኤል ሼናዊ በመጨረሻ እጩነት መቅረብ ችለዋል። የአፍሪካ የ2023 የአመቱ ምርጥ ሽልማት ስነስርዓት ሰኞ ታህሳስ 1/2016 ዓ.ም በሞሮኮዋ ማራከች ከተማ የሚካሄድ…
የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ታውቋል !
የአፍሪካ የ2023 የአመቱ ምረጥ ሽልማት ስነስርዓት በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት የአፍሪካ የ2023 የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመሆን ሞሮኳዊው የአል ሂላል ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኑ ማሸነፍ ችሏል።
ሌሎች ሽልማቶች ምን ይመስላሉ ?
- የአመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን :- ሞሮኮ
- የአመቱ ምርጥ ክለብ :- አል አህሊ ( ግብፅ )

ሮናልዶ በግብ አግቢነቱ ቀጥሏል !
የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ከአል ሸባብ ጋር ያደረገውን የሳውዲ ኪንግስ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ 5ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።
የአል ናስርን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሲዲዮ ማኔ ፣ ፎፋና ፣ ማራን እና ጋሬብ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ለአል ናስር ሀያ ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 ያስቆጠራቸውን ግቦች #ሀምሳ ማድረስ ችሏል።

የካፍ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ❓ የ2023 የውድድር ዘመን የአፍሪካ ( ካፍ ) የአመቱ ምርጥ ተጨዋች የመጨረሻ #ሶስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት ግብፃዊው ሞሀመድ ሳላህ ፣ ናይጄሪያዊው ቪክቶር ኦሲሜን እና ሞሮኳዊው አሽራፍ ሀኪሚ በእጩነት መቅረብ ችለዋል። ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሶስትዮሽ ዋንጫን ማሳካት የቻለው ሪያድ ማህሬዝ በመጨረሻ እጩ ውስጥ መካተት #ሳይችል ቀርቷል።…
የካፍ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !
የ2023 የውድድር ዘመን የአፍሪካ ( ካፍ ) የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በአሁኑ ሰዓት በሞሮኮ በመካሄድ ላይ በሚገኝ የሽልማት ስነስርዓት ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት ናይጄሪያዊው የናፖሊ የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን የአፍሪካ የ2023 የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን ማሸነፍ ችሏል።
በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ዘርፍ ይፋ ሲደረግ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉይ ማሸነፍ ችለዋል።

አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸናፊ ሆነች !
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ከስታዲየም ውጪ በተደረገ የሩጫ ውድድር ዘርፍ የአለም አትሌቲክ የ2023 የአመቱ ምርጥ ሴት አትሌት በመባል መመረጧ ይፋ ተደርጓል።
አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዘንድሮውን የበርሊን የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ እንደነበረች የሚታወስ ነው።
አትሌቷ ውድድሯን 2:11:53 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ በኬንያዊቷ ብሪጅድ ኮሴጊ ተይዞ የነበረውን የማራቶን ሪከርድ ከአምስት ዓመታት በኋላ በሁለት ደቂቃ ማሻሻሏ አይዘነጋም።
የአለም አትሌቲክ የዘንድሮው የአመቱ ምርጥ ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት አይነት ምድቦች የከፈለ ሲሆን አትሌቶችን የአመቱ ምርጥ " Track " ፣ Field እና " out of stadium " በማለት ሸልሟል።

የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች !
2:45 ፒኤስቪ ከ አርሰናል
2:45 ሌንስ ከ ሲቪያ
5:00 ኮፐንሀገን ከ ጋላታሳራይ
5:00 ባየር ሙኒክ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
5:00 ናፖሊ ከ ብራጋ
5:00 ዪኒየን በርሊን ከ ሪያል ማድሪድ
5:00 ኢንተር ሚላን ከ ሪያል ሶሴዳድ
5:00 ሳልዝበርግ ከ ቤንፊካ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
2:45 ፒኤስቪ ከ አርሰናል
2:45 ሌንስ ከ ሲቪያ
5:00 ኮፐንሀገን ከ ጋላታሳራይ
5:00 ባየር ሙኒክ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
5:00 ናፖሊ ከ ብራጋ
5:00 ዪኒየን በርሊን ከ ሪያል ማድሪድ
5:00 ኢንተር ሚላን ከ ሪያል ሶሴዳድ
5:00 ሳልዝበርግ ከ ቤንፊካ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዳኛ የመቱት የክለብ ፕሬዝዳንት !
ትላንት ምሽት በቱርክ ሱፐር ሊግ በተደረገ መርሐ ግብር በጭማሪ ደቂቃ 90+7 ላይ ግብ የተቆጠረባቸው የአንካራጉ ክለብ ፕሬዝዳንት ፋሩክ ኮካ የዕለቱን ዋና ዳኛ ሲማቱ ተስተውለዋል።
የፊፋ እና ዩፋ የዳኝነት ፈቃድ እንዳላቸው የታወቀው የዕለቱ ዋና ዳኛ ሀሊል ኡሙት ከጥቃቱ በኋላ በፊታቸው ላይ ጉዳት ደርሶም ታይቷል።
ድርጊቱን የፈፀሙት ፕሬዝዳንቱ በ 2022 የውድድር ዘመን የሊጉ የፌር ፕለይ ፕሬዝዳንት ሽልማትን ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
የተፈፀመውን ድርጊት በርካቶች በማውገዝ ላይ ሲገኙ የቱርክ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሀገሪቱ ሊግ መቋረጡን ገልጿል።
የሀገሪቱ የፍትሕ ሚንስትር ይልማዝ ቱንክ እንዳሳወቁት ድርጊቱን በፈፀሙት ሀላፊዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን ሲያሳውቁ ከድርጊቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቀዋል።

" ቀደም ብዬ ባለመምጣቴ አዝናለሁ " ሮናልዶ
ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ሳውዲ አረቢያ ቀደም ብሎ አለመምጣቱ እንደሚፀፅተው ተናግሯል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በንግግሩም " ወደ ሳውዲ አረቢያ አል ናስር ቀደም ብዬ ባለመምጣቴ አዝናለሁ አሁን ግን እዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ አውሮፓ ከማደርገው በእጥፍ ለአል ናስር አደርጋለሁ።"ሲል ተደምጧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ሳውዲ አረቢያ ቀደም ብሎ አለመምጣቱ እንደሚፀፅተው ተናግሯል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በንግግሩም " ወደ ሳውዲ አረቢያ አል ናስር ቀደም ብዬ ባለመምጣቴ አዝናለሁ አሁን ግን እዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ አውሮፓ ከማደርገው በእጥፍ ለአል ናስር አደርጋለሁ።"ሲል ተደምጧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ዛሬ ይጀመራል !
በሳውዲ አረቢያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የ 2023 የፊፋ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ዛሬ ምሽት አል ኢትሀድ ከኒውዝላንዱ ኦክላንድ ሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ማንችስተር ሲቲ በግማሽ ፍፃሜው የክለብ ሊኦን እና ኡራዋ ሬድስን አሸናፊ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ የሚገጥሙ ይሆናል።
የውድድሩ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?
👉 መጀመሪያው ዙር :-
ዛሬ ምሽት - አል ኢትሀድ ከ ኦክላንድ ሲቲ
👉 በሁለተኛው ዙር :-
አርብ - አል አህሊ ከ መጀመሪያው ዙር አሸናፊ
አርብ - ክለብ ሊኦን ከ ኡራዋ ሬድስ
👉 ግማሽ ፍፃሜ :-
ሰኞ - ፍሉሚኔንስ ከ አል አህል/ከመጀመሪያው ዙር አሸናፊ
ማክሰኞ - ማንችስተር ሲቲ ከ ክለብ ሊኦን / ኡራዋ ሬድስ
ሶስተኛውን ዙር ወይም ግማሽ ፍፃሜውን የሚያልፉ ሁለት ክለቦች ቀጣይ ሳምንት አርብ ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም የፍፃሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

"አዲስ ሲዝን ፣ አዲስ ቀን ፣ አዲስ የአሸናፊነት እድል! በቤቲካ እለታዊ ጃክፖት በየቀኑ የ አሸናፊነት ስሜትን ያጣጥሙ! ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! የዛሬውን ዕለታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/dailyjackpot)
የዛሬው የተመረጡ ዕለታዊ ጨዋታዎች ላይ ለመወራረድ - (betika.et)
"