TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
🤩 ለ5 ቀን የወጣ የ10% ቅንሽ 🤩

የወዳጅ ዘመዶን Photo እንዲህ ባማረ መልኩ በእንጨት ላይ እንሰራለን::

⭐️ Quality Matters @hanosengraving ⭐️

ዋጋ በMDF እንጨት ላይ: A3 1500, A2 2300, A1 4500

Free delivery in Addis Ababa
Contact: 0956447743 or @hanos_order

For more:- t.iss.one/hanosengraving
የሊቨርፑል እና ዩናይትድን ጨዋታ ማን ይመራል ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በዚህም መሰረት የፊታችን ዕሁድ በአንፊልድ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ማይክል ኦሊቨር በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፍራንክፈርት ቫን ዴቢክን ማስፈረም ይፈልጋል !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ኢንትራክት ፍራንክፈርት ዶኒ ቫን ዴቢክን በጥር ወር ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ውል ለማስፈረም በንግግር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የላሊጋው መሪ ጂሮና በበኩሉ ተጨዋቹን በውሰት ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸው ሲነገር ፍራንክፈርት እያደረጉ የሚገኙት ንግግር በጥሩ ደረጃ ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሬስ ጄምስ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል !

እንግሊዛዊው የሰማያዊዎቹ የመስመር ተጨዋች ሬስ ጄምስ ባደረገው የህክምና ምርመራ የ " hamstring " ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ አሳውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ሬስ ጄምስ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ እስከ ሶስት ወራት የሚደርስ ጊዜ ሊወስድበት እንደሚችል ተነግሯል።

ሬስ ጄምስ በሳምንቱ መጨረሻ ቼልሲ በኤቨርተን በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አላማችን ሊጉን ማሸነፍ ነው "

ብራዚላዊው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር የቡድናቸው የዚህ አመት የመጀመሪያ አላማ ሊጉን ማሸነፍ እንደሆነ ተናግሯል።

" አላማችን የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ማሳካት ነው " የሚለው አሊሰን ቤከር " ነገርግን ተረጋግተን ከጨዋታ ጨዋታ መሄድ አለብን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ ክለቦች ድምፅ ሰጥተዋል !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች አዲስ ኮንትራት የሚፈርሙ ተጨዋቾችን የዝውውር ገንዘብ በክለቡ ሂሳብ ውስጥ የመከፋፈል ስርዓት በአምስት አመት ጊዜ ለመገደብ ድምፅ መስጠታቸው ተገልጿል።

ክለቦቹ በሰጡት ድምፅ መሰረት ቼልሲን ጨምሮ አስራ አምስት ክለቦች ሀሳቡን ሲደግፉ ሁለቱ እንዳልተስማሙ እና ሶስቱ ደግሞ እንዳልተሳተፉ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ከዚህ በኋላ ተጨዋቾች በክለቡ ለምን ያህል ጊዜም ኮንትራት ቢፈርሙ የዝውውር ገንዘቡ ግን በክለቡ ሂሳብ ውስጥ የሚከፋፈለው ለ#አምስት አመት ብቻ እንደሚሆን ተገልጿል።

ክለቦቹ በሰጡት ድምፅ መሰረት ተጨዋቾች የሚፈልትን ጊዜ ያህል ውል መፈረም እንደሚችሉ እና ከዚህ በፊት የነበሩ ውሎችን እንደማይመለከት ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ የሻምፕየንስ ሊግ ጨዋታዎች ቀጥለዋል💥

የምድቦችን የመጨረሻ ጨዋታ በቀጥታ በዲኤስቲቪ ይከታተሉ!

🤔 የእርስዎን ግብ ትንበያዎች ያጋሩን!

👉 ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ፕላስ ያሳድጉ ፣ ሁሉንም ጨዋታ በላቀ ጥራት ይመልከቱ! 💥 የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋቾችን የሻምፕየንስ ሊግ ፍልሚያ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
ጆርጂዮ ቼሊኒ በይፋ ጫማውን ሰቅሏል !

ጣልያናዊው የቀድሞ የሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆርጂዮ ቼሊኒ በ 39ዓመቱ ጫማውን ለመስቀሉን ይፋ አድርጓል።

ባለፈው ክረምት የጁቬንቱስ ጋር የተለያየው ጆርጂዮ ቼሊኒ ወደ አሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር በማምራት ከሎስ አንጀለስ ጋር የዘንድሮውን የውድድር ዘመን አጠናቋል።

ጆርጂዮ ቼሊኒ በእግርኳስ ህይወቱ ምን አሳካ ?

1️⃣0️⃣ የጣልያን ሴርያ ዋንጫ

5️⃣ ሱፐር ኮፓ ፣ ኮፓ ኢጣልያ

1️⃣ የአውሮፓ ዋንጫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

2:45 ፒኤስቪ ከ አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
⭐️ #የ2016_የኢትዮጵያ_ሴቶች_ፕሪምየር_ሊግ የ3ኛ ሳምንት የዋናው ስፖርት የጨዋታ ኮከቦች ⭐️

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear‌‌
በሜሰን ግሪንውድ ውል ውስጥ ምን ተካቷል ?

የላሊጋው ክለብ ሄታፌ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከማንችስተር ዩናይትድ በቋሚነት ለማስፈረም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ሜሰን ግሪንውድን ለሄታፌ በውሰት ሲሰጥ በውሉ ውስጥ ከተጨዋቹ የወደፊት ሽያጭ ለሄታፌ 20% ክፍያ የሚያስገኝ ህግ ማካተቱ ተነግሯል።

ሄታፌ ሀያ በመቶ ክፍያውን የሚያገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ሜሰን ግሪንውድን ለሌላ ክለብ የሚሸጠው ከሆነ እንደሆነ ተገልጿል።

የስፔኑ ክለብ ሄታፌ ሜሰን ግሪንውድን መግዛት የሚፈልጉ ከሆነ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከሚስማሙበት ገንዘብ 80% ብቻ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቨርፑል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሚመራው የፕርሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል የወርሀ ህዳር የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ የወርሀ ህዳር የሊቨርፑል የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
42 ' ፒኤስቪ 0 - 1  አርሰናል

ኒኪታህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe