TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ማንችስተር ሲቲ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል !

በእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ በርንሌይን 6ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 3x ፣ አልቫሬዝ 2x እና ፓልመር ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በዘንድሮው የውድድር አመት #ስድስተኛ ሀትሪኩን መስራት ችሏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ በሁሉም ውድድሮች አርባ አንደኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ ባደረጋቸው ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች #ስምንት ግቦችን አስቆጥሮ #ሁለት ሀትሪኮችን መስራት ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፋቸውን ተከትሎ የኤፌ ካፕ ግማሽ ፍፃሜን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ሊሆን ይችላል ? የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች በነገው ዕለት ይፋ የሚደረግ ሲሆን አሸናፊው ተጨዋች ማን ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል። በዕጩነት ከቀረቡት ስድስት ተጨዋቾች መካከል እንግሊዛዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሊሆን እንደሚችል ለክለቡ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ይፋ አድርገዋል።…
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

ሀያ ስምንተኛው ሳምንቱ ላይ የደረሰው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

እንግሊዛዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል።

ሊጉን በመምራት ላይ ለሚገኘው አርሰናል ጥሩ ግልጋሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ቡካዩ ሳካ በውድድር አመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ክብርን ተቀዳጅቷል።

ቡካዩ ሳካ በመጋቢት ወር ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለ ሲሆን #ሶስት ግብ አስቆጥሮ #ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሉሲዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ? የ2024ቱ የሴቶች ኦሎምፒክ ውድድር ማጣሪያ ጨዋታዎች የምድብ ድልድል ነገ ማክሰኞ ይፋ የሚደረግ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ( ሉሲዎቹ ) ቋት አራት ውስጥ ተካተዋል። የምድብ ድልድሉ ቋት ምን ይመስላል ? 👉 ቋት አንድ :- ማሊ ፣ ጊኒ ፣ ሴራሊዮን እና ጊኒ ቢሳው 👉 ቋት ሁለት :- ቤኒን ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ አይቮሪኮስት እና ጋና 👉 ቋት ሶስት :…
ሉሲዎቹ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለፓሪሱ ኦሎምፒክ ለማለፍ ለሚያደርገው የማጣርያ ውድድር ተጋጣሚዎቹን አውቋል።

ብሔራዎ ቡድኑ በመጀመሪያ ዙር የማጣርያ ጨዋታ የቻድ አቻውን የሚገጥም ሲሆን ይህን ጨዋታ ከረታ በሁለተኛው ዙር ማጣርያ ከናይጄርያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወት ይሆናል።

በፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይ አፍሪካን በመወከል #ሁለት ሀገራት ብቻ ተሳታፊ ይሆናሉ።

የማጣርያ የመጫወቻ ጊዜያት ለመመልከት :- https://t.iss.one/tikvahethsport/41800

ሙሉ የማጣርያ መርሐ ግብሩ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሪከርዷ ተሰበረ !

በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ ተይዞ የነበረው የ 5,000 ሜትር የአለም ሪከርድ በኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን ተሰብሯል።

እልህ አስጨራሽ በነበረው ውድድር ፌዝ ኪፕዬጎን የአለም ሪከርድን የግሏ ስታደርግ ለተሰንበት ግደይ የውድድር ዓመቱን የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ #ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ #ሁለት_ሪከርዶችን በመስበር ( 1,500 እና 5,000 ሜትር ) የሪከርድ ባለቤት ለመሆን ችላለች።

ፌዝ ኪፕዬጎን ከሳምንት በፊት በተመሳሳይ በገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ 1,500ሜትር የአለም ሪከርድ መስበሯ ይታወሳል።

የ 5,000 ሜትር የምሽቱ ውጤት ምን ይመስላል ?

1ኛ ፌዝ ኪፕዬጎን - 14:05.20 ( የአለም ሪከርድ )

2ኛ ለተሰንበት ግደይ - 14:07.94 ( የውድድር ዓመቱ የግል ምርጥ ሰዓት )

3ኛ እጅጋየሁ ታዬ - 14:13.31 ( የውድድር ዓመቱ የግል ምርጥ ሰዓት )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ዛሬ በማን ትወከላለች ?

1⃣ - 3000ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣርያ 

👉 ጌትነህ ዋለ ( ምድብ አንድ ) ፣ አብርሀም ስሜ ( ምድብ ሁለት ) እና ለሜቻ ግርማ ( ምድብ አራት )

🇪🇹 አትሌት ለሜቻ ግርማ የወቅቱ የአለም እና የኦሎምፒክ ( ቶኪዮ ) የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን በዚህ ርቀት አዲስ ታሪክ ይፅፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ የማጣርያ ውድድር ከምድቡ ቀዳሚውን #አምስት ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላሉ።

2⃣ - 1500ሜትር የሴቶች ማጣርያ

👉 ድርቤ ወልተጂ ( ምድብ ሁለት ) ፣ ብርቄ ሀየሎም ( ምድብ ሶስት ) እና ሂሩት መሸሻ ( ምድብ አራት )

በዚህ የማጣርያ ውድድር ከምድቡ ቀዳሚውን #ስድስት ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላሉ።

የውድድር ዓመቱ የ1500ሜትር ምርጥ ሰዓት የማን ነው ?

1ኛ :- ፌዝ ኪፕዬጎን ( ኬንያ ) የአለም ሪከርድ ባለቤት ስትሆን በዚህ ርቀት በማጣርያ በምድብ #ሁለት ትገኛለች።

ጎዳፍ ፀጋይ ፣  ሂሩት መሸሻ ፣ ብርቄ ሀየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ተከታዩን አራት ደረጃዎች በመያዝ የአመቱ ምርጥ ሰዓት ባለቤት ናቸው።

3⃣ - የ10,000ሜትር ሴቶች ፍፃሜ

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ ፣ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ለምለም ሀይሉ

የውድድር መካሄጃ ሰዓት ለመመልከት :- https://t.iss.one/tikvahethsport/44027

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፕርሚየር ሊግ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በዘንድሮው የክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ከየትኛውም ታላላቅ ሊግ በበለጠ ከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች በዚህ ክረምት የዝውውር መስኮት #ሁለት ቢልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ በማውጣት ቀዳሚ መሆናቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሳውዲ ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? አራተኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የሳውዲ አረቢያ ሊግ የወርሀ ነሀሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አራት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት ክርስቲያኖ ሮናልዶ ( አል ናስር ) ፣ ሪያድ ማህሬዝ ( አል አህሊ ) ፣ ማልኮም ( አል ሂላል ) እና ኢጎር ኮሮናዶ ( አል ኢትሀድ ) በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸዉ። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮናልዶ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

ፖርቹጋላዊው የአል ናስር የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በወሩ ውስጥ ባደረጋቸው #ሶስት የሳውዲ ሊግ ጨዋታዎች #አምስት ግቦች አስቆጥሮ #ሁለት ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪክቶር ኦሲሜን ክለቡን ሊከስ ነው !

ከሰላሳ ዓመታት በኋላ ክለቡ ናፖሊ የሴርያውን ዋንጫ እንዲያሳካ ትልቁን ድርሻ የተወጣው ቪክቶር ኦሲሜን በክለቡ የቲክ ቶክ ገፅ ላይ ያልተገባ #ሁለት ተንቀሳቃሽ ምስል ሲሰራጭበት ታይቷል።

በተንቀሳቃሽ ምስሉ እንደታየው በፀገሩ ሲቀለድበት እንዲሁም የፍፁም ቅጣት ምት ሲስት የሚያሳይ ቪድዮዎች ክለቡ ለተመልካች አጋርቶ ተስተውሏል።

በጉዳዩ ላይ ደስተኛ እንዳልሆነ የተነገረው ቪክቶር ኦሲሜን እና ወኪሉ ሮቤርቶ ካሌንዳ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድላቸው እንደሚፈልጉ በወኪሉ በኩል ተገልጿል።

" የተደረገው ነገር ተቀባይነት የለውም " የሚለው ወኪሉ ካሌንዳ " በኦሲሜን ላይ ትልቅ ጉዳት የሚያደርስ ድርጊት ነው ፣ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድልን እንጠይቃለን " ብሏል።

ድርጊቱ መነሻውን ምንድነው ?

ናፖሊ በሳምንቱ መጨረሻ ከቦሎኛ ጋር በነበራቸው የሴርያው መርሐ ግብር 0ለ0 ሲወጡ ቪክቶር ኦሲሜን የፍፁም ቅጣት ምት ስቶ ነበር።

ቪክቶር ኦሲሜን ምን ምላሽ ሰጠ ?

ቪክቶር ኦሲሜን ክለቡ ይህን ድርጊት ከፈፀመበት በኋላ በክለቡ ማልያ የተነሳቸውን እና በኢንስታግራም ገፁ ያጋራቸውን መረጃዎች በሙሉ አጥፍቷል።

የሴርያው ክለብ ናፖሊ ጉዳዩ ከተፈጠረ በኋላ በሁነቱ ላይ የሰጡት ምንም አይነት ምላሽ እስከአሁን የለም።

ናይጄርያዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን በናፖሊ ቤት እስከ 2025 የውድድር ዓመት ድረስ የሚያቆይ ኮንትራት አለው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወርቅ አገኘች !

በሪጋ እየተካሄደ በሚገኘው የአለም የጎዳና ላይ የአለም ሻምፒዮና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ኬንያዊቷን የ 1500ሜ የአለም ሪከርድ ባለቤት ፌዝ ኪፕዬጎን በመርታት ለሀገሯ ወርቅ አምጥታለች።

ድርቤ ወልተጂ ከማሸነፍ ባለፈም የአለም የአንድ ማይል ሪከርድን 4:21.00 በመግባት በመስበር ልታሸንፍ ችላለች።

በርቀቱ የተካፈለችው ሌላኛዋ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።

ድርቤ ወልተጂ በቡዳፔሽት የዓለም ሻምፒዮና በ 1500ሜ በፌዝ ኪፕዬጎን ተቀድማ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ ማምጣቷ የሚታወስ ነው።

ፌዝ ኪፕዬጎን በ 2023 የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ልትሸነፍ ችላለች።

የዚህ ውድድር አሸናፊዎች ምን ያህል ያገኛሉ ?

1️⃣ኛ. አስር ሺህ ዶላር

2️⃣ኛ. ስድስት ሺህ ዶላር

3️⃣ኛ. ሶስት ሺህ አምስት መቶ ዶላር

ሀገራችን ኢትዮጵያ እስከአሁን በተደረጉ ሶስት የፍፃሜ ውድድሮች #ሁለት ወርቅ ፣ #ሁለት ብር እና #አንድ የነሀስ ሜዳልያ በማስመዝገብ የሜዳልያ ሰንጠረዡን በመምራት ላይ ትገኛለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe