TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ዩናይትድ ተጨዋቹ ወደ ሜዳ ይመለሳል !

ማንችስተር ዩናይትድ በነገው ዕለት ከዎልቭስ ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ የሊግ መርሐ ግብር የወሳኝ ተጫዋቹን ግልጋሎት እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ፈረንሳዊው ተከላካይ ራፋኤል ቫራን ቀያዮቹ ሴጣኖች ከዎልቭስ ጋር በሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አያይዘውም የፊት መስመር ተጨዋቹ ማርከስ ራሽፎርድ ጉዳት እንዳጋጠመው እና በነገው ጨዋታ ላይደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አርሰናል ሁሉንም ያሸንፋል " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በቀጣይ ጨዋታዎች አርሰናል ነጥብ ይጥላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ከኤቨርተን ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን አሉ ?

- " እውነቱን ስናገር አርሰናል በሚቀጥሉት ጨዋታዎች ነጥብ እንዲጥል ተስፋ አደርጋለሁ ነገር ግን አርሰናል በእርግጠኝነት ቀሪዎቹን ጨዋታዎች ያሸንፋል።

- በሪያል ማድሪድ ጨዋታ ላይ ትኩረቴን መከፋፈል አልፈልግም ለእሱ ጊዜ አለን ከኤቨርተን ጋር የምናደርገው ጨዋታ አሁን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

- ወደ ጉዲሰን ፓርክ በመሄድ ከኤቨርተን ጋር መጫወት ሁል ጊዜም በጣም ደስ ይለኛል እሱ የእንግሊዝ ባህላዊ ስታዲየም ነው።

- ኤርሊንግ ሀላንድ የውድድር አመቱ የእግር ኳስ ፀሀፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች መባሉ ይገባዋል እንኳን ደስ አለህ ለማለት እፈልጋለሁ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሊቨርፑል አያሰጋንም " ቴን ሀግ

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ሊቨርፑል የሻምፒየንስ ሊግ ቦታን ይቀማናል ብለው እንደማይሰጉ በሰጡት አስተያየት ተናግሯል።

ኤሪክ ቴንሀግ በንግግራቸውም :-

" ዴህያ ጥሩ ተጨዋች ነው የሰራው ስህተት ሊጠፋ አይችልም ነገር ግን የግለሰብ ስህተት የእግርኳስ አንዱ አካል ነው ሊከሰት የሚችል ነው።

ሊቨርፑል ከኋላችን እንደሆነ እናውቃለን ነገር ግን ምንም አንሰጋም ሁሉም ነገር በእጃችን ነው የሚገኘው ራሳችንን ማሻሻል አለብን።

የነገ ተጋጣሚያችን ዎልቭስ ጥሩ ቡድን ነው በዚህ አመት ጥሩ ነገር ማሳየት ችለዋል ጨዋታው ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል።

ጋርናቾ ተጨማሪ አንድ ሳምንት የሚቆይ ልምምድ አድርጓል ፣ ስለዚህ ለጨዋታው ዝግጁ ነው ፣ በቡድኑ ውስጥ ተጨማሪ ነገር ማምጣት እንደሚችል አሳይቶናል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የምንጫወተው ለዋንጫ ነው "

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ለሊጉ ዋንጫ በሚደረገው ፉክክር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በንግግራቸውም :-

" ዚንቼንኮ ከውድድር አመቱ ውጪ መሆኑ አልተረጋገጠም ፣ ዊልያም ሳሊባ በብራይተን ጨዋታ አይኖርም በኖቲንግሀም ፎረስቱም ጨዋታ ይመለሳል ተብሎ አይጠበቅም።

እኛ እየተጫወትን የምንገኘው ሻምፒዮን ለመሆን ነው ፣ በዚህ ላይ ሙሉ በሙሉ ትኩረት ማድረግ እንፈልጋለን ትኩረታችንን በሚያጠፉ ነገሮች ላይ ማሳለፍ የለብንም።

ከብራይተን ጋር የምናደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ እንፈልጋለን ከቀሩን ወሳኝ መርሐግብሮች አንዱ ነው።

ለሚነገሩ ታሪኮች ሁሉ ምላሽ አልሰጥም ነገር ግን በግራኒት ዣካ በጣም ደስተኞች ነን ጥሩ የውድድር አመት እያሳለፈ እንደሆነ አስባለሁ እሱ ስላለ ደስተኛ ነኝ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አርሰናል ለዋንጫ መፎካከር ይገባዋል "

የብራይተኑ ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለሊጉ ዋንጫ መፎካከር እንደሚገባው ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በንግግራቸውም " አርሰናል ብዙ ነገሮች እየተሻሻለ ነው ድንቅ እግር ኳስ ይጫወታሉ ፣ አርሰናል ትልቅ ቡድን ነው።

እነሱ ለፕርሚየር ሊጉ ዋንጫ መጫወት ይገባቸዋል ፣ ማን እንደሚያሸንፍ አላውቅም ፣ ነገር ግን ለእነሱ ትልቅ ክብር አለን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ልዩ ቻናል 471 እና ልዩ2 ቻናል 472 ላይ ይመልከቱ ።

ጨዋታዎቹን ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ በ290 ብር ብቻ ያገኛሉ።

አንድም ጨዋታ፣ አንድም ጎል አያምልጥዎ!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ950 ብር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!

https://bit.ly/2WDuBLk

የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ!

👇

https://bit.ly/3D2O1t4

#EthiopianPremierLeague #DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfServiceET
" በፀሎት ነው የሚቆመው "

የቀድሞ ጣልያናዊ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ፋብዮ ካናቫሮ ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ሊቆም የሚችለው በፀሎት ብቻ መሆኑን ተናግሯል።

የቀድሞ ጣልያናዊ ተጨዋች ፋብዮ ካናቫሮ በንግግሩም " ቪንሰስ ጁኒየርን ተጋጣሚዎች እንዴት ሊያቆሙት ይችላሉ ? " ለሚለው ጥያቄ መልሱ " ፀሎት " በማድረግ ብቻ ነው በማለት ገልፆታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማርሴሎ ቤልሳ ወደ ዩራጓይ ሊያመሩ ነው !

አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድንን በሀላፊነት ለመረከብ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ከሊድስ ጋር ከተለያዩ በኋላ ያለ ሀላፊነት የሚገኙት አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ አሰልጣኝ ዲያጎ አሎንሶን በመተካት የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድንን ለመረከብ መቃረባቸው ተዘግቧል።

የ 67ዓመቱ አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድንን የሚረከቡ ከሆነ በቀጣይ ክረምት የሚደረገው የኮፓ አሜሪካ ውድድር ብሔራዊ ቡድኑን የሚመሩ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አክሴል ዊትስል ራሱን አግልሏል !

ቤልጄማዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች አክሴል ዊትስል በ 34ዓመቱ ከኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

የ 34ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አክሴል ዊትስል ለቤልጄም ብሔራዊ ቡድን አንድ መቶ ሰላሳ ጨዋታዎች ማድረግ የቻለ ሲሆን አስራ ሁለት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

አክሴል ዊትስል ባስተላለፈው የስንብት መልዕክትም " ይህንን ውሳኔ የወሰንኩት በጥንቃቄ ካሰሰብኩ በኋላ ነው ለአመታት ሀገሬን መወከል በመቻሌ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ከሪያል ማድሪድ ጋር ይጫወታል !

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ክረምት በአሜሪካ በሚኖራቸው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ከሪያል ማድሪድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ በአሜሪካ ሆስተን "NRG" ስታዲየም ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ከባርሴሎና ጋር ይጫወታል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቀጣይ ክረምት በአሜሪካ በሚኖራቸው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

መድፈኞቹ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ሶፊ ስታዲየም ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤል ክላሲኮ በአሜሪካ ይደረጋል !

ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና በአሜሪካ በሚኖራቸው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት የወዳጅነት ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይፋ አድርገዋል።

ሁለቱ ክለቦች በአሜሪካ የሚያደርጉት የኤል ክላሲኮ ጨዋታ ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም ዳላስ " AT&T " ስታዲየም እንደሚደረግ ይፋ ተደርጓል።

ሪያል ማድሪድ በተጨማሪም በአሜሪካ በሚኖራቸው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ከማንችስተር ዩናይትድ ፣ ጁቬንቱስ እና ኤሲ ሚላን ጋር የወዳጅነት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን።

ባርሴሎና በበኩላቸው በአሜሪካ በሚኖራቸው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ከጁቬንቱስ ፣ አርሰናል እና ኤሲ ሚላን ጋር የወዳጅነት ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይፋ አድርገዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
"በአጓጊው ሳምንታው ጃክፖት ጨዋታ የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊ ይሁኑ! ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! የዛሬውን ዕለታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/weeklyjackpot)
የዛሬው የተመረጡ ዕለታዊ ጨዋታዎች ላይ ለመወራረድ - (betika.et)
የሳምንታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/weeklyjackpot)"
የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች !

8:30 ሊድስ ዩናይትድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

10:30 ባየር ሙኒክ ከ ሻልክ 04

11:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ዎልቭስ

11:00 ቼልሲ ከ ኖቲንግሀም ፎረስት

11:00 አስቶን ቪላ ከ ቶተንሀም

1:00 ስፔዝያ ከ ኤሲ ሚላን

1:30 ዶርትመንድ ከ ሞንችግላድባች

3:45 ኢንተር ሚላን ከ ሳሱሎ

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ጌታፌ

4:00 ፒኤስጂ ከ አጃሲዮ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ባሎን ዶር ለሜሲ ይገባዋል "

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች በርናርዶ ሲልቫ የዘንድሮው የውድድር አመት የባሎን ዶር ሽልማት እስካሁን ባለው ነገር ለሊዮኔል ሜሲ እንደሚገባው ገልጿል።

በርናርዶ ሲልቫ በንግግሩም " በዚህ ሰዓት ሆነን የባሎን ዶር ሽልማት ለሊዮኔል ሜሲ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም የዓለም ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል።

ነገር ግን እኛ የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ከቻልን ኤርሊንግ ሀላንድ ይገባዋል ቪንሰስም ሪያል ማድሪድ ማሸነፍ ከቻለ ይገባዋል።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሀላንድን እንዲያስፈርሙ ደውዬ ነበር "

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ አሊ ጎነር ሶልሻየር  ሞልድ እያሉ ያሰለጥኑት የነበረውን ኤርሊንግ ሀላንድ ማንችስተር ዩናይትድ እንዲያስፈርሙ ደውለውላቸው እንደነበር ተናግረዋል።

አሊ ጎነር ሶልሻየር በንግግራቸውም " ማንችስተር ዩናይትድን ለማሰልጠን ከመረከቤ ስድስት ወራት በፊት ለማንችስተር ዩናይትድ ደውዬላቸው ነበር ፣ እናም ስለ አጥቂያችን ኤርሊንግ ሀላንድ ነግሬያቸው ነበር ነገር ግን እነሱ ሊሰሙኝ አልፈለጉም።

እኛ በወቅቱ ሀላንድን ለመሸጥ የጠየቅነው አራት ሚልዮን ፓውንድ ብቻ ነበር ነገር ግን እነሱ ሊያስፈርሙት አልፈለጉም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳውዝሀምፕተን ዛሬ መውረዱን ሊያረጋግጥ ይችላል !

በአሰልጣኝ ሩበን ሴሌስ የሚመራው ሳውዝሀምፕተን ዛሬ ከፉልሀም ጋር የሚያደርገውን ወሳኝ የሊግ መርሐ ግብር ማሸነፍ የማይችል ከሆነ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱን ያረጋግጣል።

ሳውዝሀምፕተን በፕርሚየር ሊግ የመቆየት ዕድሉን ለማለምለም በዛሬው ጨዋታ ፉልሀምን የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ የገባ ሲሆን በጨዋታው የሚሸነፍ ወይም አቻ የሚለያይ ከሆነ ከወዲሁ መውረዱን ያረጋግጣል።

ሳውዝሀምፕተን ዛሬ የሚሸነፍ ከሆነ በውድድር አመቱ ሀያ አራት ጨዋታዎችን በመሸነፍ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ አዲስ ቁጥር ሆኖ ይመዘገባል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ነገ የሚደርስ ማልያዎን ዛሬ ይዘዙ !

የተዘጋጁ ማሊያዎችን በ 499 ብር ብቻ በእጅዎ ያስገቡ።

ዋናው ወደ ፊት . . . . .

📞 ይደውሉን :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

ነገ የሚደርስ ማልያዎን ዛሬ ይዘዙ !
" ተጨዋች ለማስፈረም ቀላል ይሆናል "

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ በዚህ አመት ከባለፈው በተሻለ አዳዲስ ተጨዋቾችን ለማስኮብለል ቀላል እንደሚሆንላቸው ተናግረዋል።

ኤሪክ ቴን ሀግ በንግግራቸውም " በዚህ አመት ተጨዋቾችን ማስፈረም ከባለፈው አመት የበለጠ ቀላል ይሆንልናል ምክንያቱም ዋንጫ አሸንፈናል ፣ የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ላይም ደርሰናል።

ከዚህ በፊት በምናናግርበት ወቅት ጥርጣሬዎች ነበሯቸው አሁን እየሄድን ያለንበትን መንገድ እና የክለቡን ምኞት ተመልክተዋል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

ሊጉን በመምራት ላይ የሚገኙት ማንችስተር ሲቲዎች የዘንድሮው የውድድር አመት ምርጥ ተጫዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ኬቨን ዴብሮይነ እና ናታን አኬ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች የመጨረሻ #ሶስት እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ነው ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe