TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
" ሊጉ እንዳለቀ አድርጌ አስቤ አላውቅም "

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከምሽቱ የዌስትሀም ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸውም " እንዴት አንደሚሰራ አውቃለሁ ፣ አርሰናልን ስናሸንፍ ሁሉም ሰው ሊጉ አለቀ ብሎ ነበር ትላንት አርሰናል ሲያሸንፍ ደግም ገና ነው ተብሏል።

እኛ ግን እውነታውን እናውቃለን ፣ ከአርሰናል ጨዋታ በኋላ ሊጉ እንዳለቀ አድርጌ ለሰከንድም ቢሆን አስቤ አላውቅም።

ዴብሮይነ ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ፣ በቀጣይ ጨዋታ እንደሚመለስ ተስፋ አደርጋለሁ ፣ ኤደርሰንን ያላሰለፍነው እረፍት ለመስጠት ነው ፣ በሞሬኖ እንተማመናለን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አራት ውስጥ መጨረስ በጣም አስቸጋሪ ነው "

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ተከላካይ ቨርጅል ቫን ዳይክ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው ተናግሯል።

ቫን ዳይክ በንግግሩም " በዚህ አመት የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው ፣ እውነት ለመናገር የመሳተፍ ዕድሉ በእጃችን አይገኝም።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ሊቨርፑል 0-0 ፉልሀም

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ዌስትሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
17' ሊቨርፑል 0-0 ፉልሀም

16' ማንችስተር ሲቲ 0-0 ዌስትሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
31' ሊቨርፑል 0-0 ፉልሀም

30' ማንችስተር ሲቲ 0-0 ዌስትሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
39' ሊቨርፑል 1-0 ፉልሀም

ሳላህ

38' ማንችስተር ሲቲ 0-0 ዌስትሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ሊቨርፑል 1-0 ፉልሀም

ሳላህ

እረፍት | ማንችስተር ሲቲ 0-0 ዌስትሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
50' ሊቨርፑል 1-0 ፉልሀም

ሳላህ

50' ማንችስተር ሲቲ 1-0 ዌስትሀም

ናታን አኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
64' ሊቨርፑል 1-0 ፉልሀም

ሳላህ

63' ማንችስተር ሲቲ 1-0 ዌስትሀም

ናታን አኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
71' ሊቨርፑል 1-0 ፉልሀም

ሳላህ

70' ማንችስተር ሲቲ 2-0 ዌስትሀም

ናታን አኬ
ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
84' ሊቨርፑል 1-0 ፉልሀም

ሳላህ

83' ማንችስተር ሲቲ 2-0 ዌስትሀም

ናታን አኬ
ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
84' ሊቨርፑል 1-0 ፉልሀም

ሳላህ

85' ማንችስተር ሲቲ 3-0 ዌስትሀም

ናታን አኬ
ሀላንድ
ፎደን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረክቧል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ዌስትሀምን 3ለ0 እንዲሁም ሊቨርፑል ፉልሀምን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

- የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ናታን አኬ እና ፊል ፎደን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግብ ሞሐመድ ሳላህ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ሞሀመድ ሳላህ በውድድር አመቱ አስራ ስምንተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ አምስት ግቦችን በማስቆጠር የአንድ የውድድር አመት የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።

- ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰባ ዘጠኝ በማድረስ የሊጉን መሪነት ከአርሰናል መረከብ ሲችል ሊቨርፑል በሀምሳ ዘጠኝ ነጥብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ሊድስ ዩናይትድ እንዲሁም ሊቨርፑል ከ ብሬንትፎርድ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
RUN in the "Town of runners" HIKE  in the beautiful highlands of Arsi!

You don't want to miss this - Register now for the ultimate running experience in Bokoji!

🟢 2023 Ethio Telecom Great Bokoji Run
📆 14 May 2023
📍 Bokoji, Ethiopia

Don't miss out on this amazing opportunity to challenge yourself, have fun, and experience the journey!

The full package is available in the link below👇
https://drive.google.com/file/d/1O_Y33f6mugB7zl_IDcK9mVsOna9co4Vm/view?usp=sharing

#2023GreatBokojiRun #EthioTelecom #LandofOrigins
"የጨዋታዎችን ብዛት በመጨመር የሚያሸንፉትን ገንዘብ እስከ 300% ያሳድጉ! ቤቲካ ላይ ይወራረዱ! ያሸንፉ!
የዛሬውን ዕለታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/dailyjackpot)
የዛሬው የተመረጡ ዕለታዊ ጨዋታዎች ላይ ለመወራረድ - (betika.et)
የሳምንታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/weeklyjackpot)"
" ዋናው ሶስት ነጥብ ነው "

ማንችስተር ሲቲ ትላንት ምሽት ዌስትሀምን ባሸነፈበት ጨዋታ ከጉዳት መልስ ግብ ያስቆጠረው ተከላካዩ ናታን አኬ ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ናታን አኬ በንግግሩም " ምናልባት ጥሩ ጨዋታ ነበር ነገር ግን ዋናው ነገር ሶስት ነጥብ ማግኘት ነው ፣ ሀላንድ የሚያደርገው ያልተለመደ ነገር ነው።

እሱ በልምምድም ሆነ በሜዳ ላይ ያለውን ሁሉ ይሰጣል ፣ ለእኛ ትልቅ ተጨማሪ ሀይል ነው ወደፊትም ተጨማሪ ጎሎችን እንደሚያስቆጥር ተስፋ እናደርጋለን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሀላንድ ክብር ይገባዋል "

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ቡድኑ ለቀጣይ ጨዋታ በፍጥነት መዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸውም " በፍጥነት ዝግጅት መጀመር አለብን ምክንያቱም በቀጣይ የምንገጥመው የሳም አላርዳይስን ቡድን ነው ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ በርካታ ግቦች በማስቆጠሩ ክብር ይገባዋል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፔፕ ጋርዲዮላን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ "

በትላንት ምሽቱ ጨዋታ የሊጉን የአንድ የውድድር አመት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ሪከርድ መስበር የቻለው ኤርሊንግ ሀላንድ ከጨዋታው በኋላ አስተያየት ሰጥቷል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በንግግሩም " የሚገርም ምሽት ነበር በጣም ተደስቻለሁ ፣ ተጨማሪ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም ፣ ከጨዋታው በፊት ከግሪሊሽ ጋር አውርተን ነበር ሪከርድ የምሰብርበትን ጎል አመቻችቶ ማቀበል ይፈልግ ነበር።

በፔፕ ጋርዲዮላ ስር መጫወት በጣም ነው የምወደው ፣ በጣም ጥሩ ነው ፣ እንደ እሱ አይነት አሰልጣኝ በማግኘቴ የእውነት ደስተኛ ነኝ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጣልያን ሴርያ የአራት ውስጥ ፉክክር !

በቀጣይ የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ፉክክር በጣልያን ሴርያ አጓጊ ሆኖ ቀጥሏል።

በሳምንቱ መጨረሻ አራት ውስጥ በመጨረስ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት እየተፎካከሩ የሚገኙ ክለቦች እርስበርስ የሚገናኙ ይሆናል።

በሳምንቱ መጨረሻ የሚጠበቁ ጨዋታዎች :-

👉 ኤሲ ሚላን ከ ላዝዮ

👉 ሮማ ከ ኢንተር ሚላን

👉 ጁቬንቱስ ከ አታላንታ የሚገናኙ ይሆናል።

ማን ለሻምፒየንስ ሊግ ያልፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe