TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
" እስከመጨረሻው እንፋለማለን "

መድፈኞቹ ትላንት ምሽት ቼልሲን ሲያሸንፉ ሁለት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ የቻለው ማርቲን ኦዴጋርድ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ማርቲን ኦዴጋርድ በንግግሩም " በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገን ነበር ፣ በሁለተኛው አጋማሽ ከአቋማችን ትንሽ ወርደናል ነገር ግን ዛሬ ዋናው ነገር ድል ማስመዝገብ ነው ፣ ሊጉን ለማሳካት እስከመጨረሻው እንፋለማለን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አሁን የሊጉ መሪ እኛ ነን "

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሀል ሜዳ ተጨዋች ግራኒት ዣካ ከትላንት ምሽቱ ጨዋታ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ግራኒት ዣካ በንግግሩም " ጨዋታውን ማሸነፍ ይገባናል ብዬ አስባለሁ ፣ ከእረፍት በኋላ ጥሩ አልነበርንም ነገር ግን ከስህተታችን እንማራለን።

በቀጣይ መርሐግብር ከኒውካስል ዩናይትድ ጋርከባድ ጨዋታ አለብን ፣ ሶስት ነጥብ ለማሳካት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ድሉን ወደ ለንደን እንመልሰዋለን።

አሁን የሊጉ መሪ እኛ ነን ቀጣይ ጨዋታዎችንም ማሸነፍ አለብን ፣ አሁንም የሊጉን ዋንጫ እንደምናሳካ አምናለሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በራስ መተማመናቸው ወርዷል "

የሰማያዊዎቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ትላንት ምሽት በአርሰናል ሽንፈት ሲገጥማቸው ተጨዋቾቹ በራስ መተማመን እንዳልነበራቸው ተናግረዋል።

ፍራንክ ላምፓርድ በንግግራቸውም " መናገር እጠላለሁ ነገር ግን የተጨዋቾቹ በራስ መተማመን ዝቅተኛ ነው ፣ የተሻለ መስራት አለብን ፣ በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ ነበርን ነገር ግን ውጤቱ አስቀድሞ ተወስኗል።

ነገሮች በአንድ ምሽት ሊቀየሩ አይችሉም ፣ ነገር ግን በፍጥነት መቀየር ይኖርብናል ፣ ምንም መሻሻል አላሳየንም ውጤቱ ይናገራል ፣ ቼልሲን ለሚያክል ክለብ ውጤቱ ጥሩ አይደለም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋናው የሻምፒዮኖቹ ምርጫ 🏆

ዋናው የሻሸመኔ የእግር ኳስ ክለብ ቀሪ መርሐ ግብሮች እየቀሩት በ 2016ዓ.ም የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ተሳታፊ በመሆናቸው እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።

ዋናው የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ ከሻሸመኔ እግር ኳስ ክለብ ጋር አብሮ በመስራቱ ኩራት ሲሰማው በቀጣይ ጓዛቸው ላይ ስኬታማ ጊዜን እንዲያሳልፉ ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

ዋናው ወደ ፊት. . . . .

📞 ይደውሉ :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

📌 አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት
ማድሪድ ተጨዋቾቹ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ !

ሪያል ማድሪድ ቅዳሜ በሚያደርገው የኮፓ ዴላሬ ጨዋታ ሉካ ሞድሪችን ጨምሮ የወሳኝ ተጨዋቾቹን ግልጋሎት እንደሚያገኝ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ አስታውቀዋል።

በፍፃሜ ጨዋታው ለሎስ ብላንኮዎቹ ግልጋሎት የማይሰጠው ፌርላንድ ሜንዲ ብቻ እንደሆነ አሰልጣኙ አያይዘው ተናግረዋል።

አሰልጣኙ በንግግራቸውም " ሉካ ሞድሪች ልምምዱን ሰርቷል ፣ ለቅዳሜው ጨዋታ የመድረስ ትልቅ ዕድል አለው ፣ ከ ፌርላንድ ሜንዲ ውጪ ሁሉም ተጨዋቾች ይመለሳሉ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ ታሪካዊ ቀኑን በበጎ ተግባር !

የጣልያን ሴርያው መሪ ናፖሊ ነገ ምሽት ከሜዳው ውጪ ከዩዲኒዜ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ደጋፊዎቹ እንዲታደሙ በአርማንዶ ማራዶና ስታዲየም ትልልቅ ስክሪኖች ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

በጨዋታው ሶስት ነጥብ የሚያሳካ ከሆነ የሊጉን አሸናፊነት የሚያረጋግጠው ናፖሊ በስታዲየሙ በተዘጋጀው ስክሪን ጨዋታ ለማስመልከት ትኬቶችን በአምስት ዩሮ በመሸጥ ላይ መሆኑ ተነግሯል።

ናፖሊ በስታዲየሙ ካዘጋጃቸው ስክሪኖች ትኬት ሽያጭ የሚያገኘውን ሙሉ ገቢ ለእርዳታ ድርጅቶች ለመለገስ ማሰቡ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ክለቡ የሊጉን አሸናፊነት የሚያረጋግጥበትን ታሪካዊ ጨዋታ ለመታደም ከ 11,000 በላይ የናፖሊ ደጋፊዎች ወደ ዩዲን ከተማ እንደሚያመሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና የሊጉን አሸናፊነት መቼ ያረጋግጣል ?

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሰማንያ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታያቸው ሪያል ማድሪድ በአስራ አራት ነጥቦች ርቀው ላሊጋውን በመምራት ላይ ይገኛሉ።

በአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የሚመራው ባርሴሎና የፊታችን ዕሁድ ከኢስፓኞል ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ አራት ጨዋታዎች እየቀሩት ከወዲሁ የሊጉ አሸናፊነቱን ማረጋገጥ ይችላል።

በተጨማሪም በቀጣይ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ነጥብ የሚጥል ከሆነ ባርሴሎና የሊጉን አሸናፊነት ያረጋግጣል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የአርሰናል ደጋፊዎች መደሰት አለባቸው "

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአርሰናል ደጋፊዎች ቡድናቸው የውድድር አመቱ ሳይጠናቀቅ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን በማግኘቱ ሊደሰቱ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸውም " አርሰናል ከሰባት አመታት በኋላ ለሻምፒየንስ ሊግ በማለፍ ለክለቡ አስፈላጊ የሆነ ዋንጫ አሸንፈዋል ፣ ደጋፊዎቹ በዚህ መደሰት አለባቸው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊድስ ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል !

በሊጉ ደካማ ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኘው ሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ጃቪ ጋርሽያን በማሰናበት አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስን በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 68ዓመቱ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ሊድስ ዩናይትድን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ለመምራት ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ለሁለት አመታት ካለ ሀላፊነት ከቆዩ በኋላ ሊድስ ዩናይትድን ለቀጣዮቹ አራት ጨዋታዎች ለመምራት ወደ አሰልጣኝነት ስራቸው መመለስ ችለዋል።

አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ሊድስን እየመሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሳምንቱ መጨረሻ ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🟢 የ2015 ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ
📆 ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም.
📍 ቦቆጂ፣ ኢትዮጵያ

የሯጮች ምድር በሆነችው ቦቆጂ ከተማ ኑ! እንሩጥ!

ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ተራራ የመውጣት እና የካምፒንግ ምሽት ሲኖር፣ እንዲሁም እሁድ ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም.  የ2ተኛው ዙር ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡

የመመዝገቢያ ዋጋ: 350ብር
መመዝገቢያ ቅፅ👇
https://drive.google.com/file/d/1O_Y33f6mugB7zl_IDcK9mVsOna9co4Vm/view?usp=sharing

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን👇
☎️ +251116635757/+251116185841

📸Image: The Bekoji Track Classic

#2023GreatBokojiRun #EthioTelecom #LandofOrigins
TIKVAH-SPORT
ሊድስ ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል ! በሊጉ ደካማ ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኘው ሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ጃቪ ጋርሽያን በማሰናበት አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስን በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል። የ 68ዓመቱ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ሊድስ ዩናይትድን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ለመምራት ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ለሁለት አመታት ካለ ሀላፊነት ከቆዩ በኋላ…
ሳም አላርዳይስ ሊድስን ያተርፉ ይሆን ?

ሊድስ ዩናይትድን በሀላፊነት የተረከቡት አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ከዚህ በፊት በውድድር አመቱ አጋማሽ ተሾመው ለቡድናቸው ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል።

አሰልጣኝ ሳም አላርዳይስ ከዚህ በፊት በውድድር አመቱ አጋማሽ በአምስት ክለቦች የተሾሙ ሲሆን የአራቱን ክለቦች ደረጃ አሻሽለዋል።

አሰልጣኙ በክለቦቹ በነበራቸው ቆይታ :-

👉 ብላክበርን ሮቨርስን :- ከ አስራ ዘጠነኛ ወደ አስራ አምስተኛ ደረጃ

👉 ሰንደርላንድን :- ከ ከአስራ ዘጠነኛ ወደ አስራ ሰባተኛ ደረጃ

👉 ክሪስታል ፓላስን :- ከ አስራ ሰባተኛ ወደ አስራ አራተኛ ደረጃ

👉 ኤቨርተንን :- ከ አስራ ሶስተኛ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ማሻሻል ችለዋል።

አሰልጣኙ ከዚህ በፊት በውድድር አመቱ አጋማሽ በሀላፊነት ተሾመው ወደ ታችኛው ሊግ እንዳይወርድ ማትረፍ ያልቻሉት እ.ኤ.አ 2020 ዌስትብሮምን ብቻ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋቹ ወደ ሜዳ ይመለሳል !

የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን የውድድር አመቱ ሳይጠናቀቅ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ተጨዋቹ በቀጣይ ክለቡ በሚያደርጋቸው የብራይተን እና ዌስትሀም ጨዋታዎች እንደማይደርስ አሰልጣኙ አስታውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሁሉንም ውድድሮች ማሸነፍ እንፈልጋለን "

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድናቸው በነገው ዕለት ከ ብራይተን ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በንግግራቸውም :-

- " ብራይተን እኛን ለማሸነፍ ትልቅ ተነሳሽነት አላቸው ነገር ግን እኛ የበለጠ ማድረግ አለብን ከእነሱ በተሻለ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ እንፈልጋለን።

- ሁሉንም ጨዋታዎች እና ሁሉንም ውድድሮች ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ በሻምፒየንስ ሊግ ውድድር መሳተፍ እንፈልጋለን ፣ አሁን ትኩረት የምናደርገው እሱ ላይ ነው።

- አሌሀንድሮ ጋርናቾ ወደ ልምምድ ተመልሷል ፣ ነገር ግን ነገ ወደ ሜዳ ለመመለስ ትንሽ ሊፈጥንበት ይችላል።

- በሜዳችንም ሆነ ከሜዳችን ውጪ መጫወት ምንም ለውጥ አያመጣም ሁሉንም ጨዋታ ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ ነገም ተመሳሳይ ማሸነፍ እንፈልጋለን።

-ነገ ከብራይተን ጋር የምናደርገው ጨዋታ ጦርነት ነው ሁሉም ሰው ለጦርነቱ መዘጋጀት አለበት።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቻል ድል አድርጓል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የመቻልን የማሸነፊያ ግቦች ከነዓን ማርክነህ እና እስራኤል እሸቱ ከመረብ ሲያሳርፉ ለድሬዳዋ ከተማ ሙኸዲን ሙሳ አስቆጥሯል።

- መቻል ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ድሬዳዋ ከተማ በሀያ ሰባት ነጥብ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር መቻል ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ቪክቶር ሊንድሎፍ እና ሉክ ሾው የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው ቀርበዋል።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ነው ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የ22ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በሱፐርስፖርት ልዩ ይመልከቱ።

በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ልዩ ቻናል ቁጥር 471 እና ሱፐርስፖርት ልዩ2 ቻናል ቁጥር 472 ላይ በአማርኛ ኮሜንተሪ!

አንድም ጨዋታ አንድም ጎል አያምልጥዎ!

ክፍያ ለመፈፀም፣ፓኬጅዎን ለመቀየር እንዲሁም ሌሎች የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ታች ያለውን

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!

👇

https://bit.ly/2WDuBLk


የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ!

👇

https://bit.ly/3D2O1t4

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #EthiopianPremierLeague #SSልዩ #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
ሊዮኔል ሜሲ በቀጣይ ወዴት ያመራል ?

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር ያለው ውል በውድድር አመቱ መጨረሻ ሲጠናቀቅ ከክለቡ ጋር ሊለያይ እንደሚችል ታማኝ የመረጃ ምንጮች በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።

የአለም ሻምፒዮኑ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከቀናት በፊት የክለቡን ፍቃድ ሳያገኝ ወደ ሳውዲ አረቢያ ማምራቱን ተከትሎ ክለቡ የሁለት ሳምንታት እገዳን እንደጣለበት ተነግሯል።

አሁን ላይ እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች ሊዮኔል ሜሲ ከዚህ በፊት የዝውውር ጥያቄ ካቀረበለት የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ጋር ንግግር ማድረግ እንደጀመረ ጠቁመዋል።

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል በአዲስ መልክ ለአርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በአመት 400 ሚልዮን ዶላር የሚያስገኝለትን ውል ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን አሸንፏል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች ሐቢብ ከማል እና ብሩክ ሙሉጌታ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ አብዱልራህማን ሙባረክ አስቆጥሯል።

- የኢትዮጵያ መድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ሀቢብ ከማል በውድድር አመቱ አስረኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ኢትዮጵያ መድን ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአስራ አንድ ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊዮኔል ሜሲ በቀጣይ ወዴት ያመራል ? አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር ያለው ውል በውድድር አመቱ መጨረሻ ሲጠናቀቅ ከክለቡ ጋር ሊለያይ እንደሚችል ታማኝ የመረጃ ምንጮች በመዘገብ ላይ ይገኛሉ። የአለም ሻምፒዮኑ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከቀናት በፊት የክለቡን ፍቃድ ሳያገኝ ወደ ሳውዲ አረቢያ ማምራቱን ተከትሎ ክለቡ የሁለት ሳምንታት እገዳን እንደጣለበት ተነግሯል።…
ሊዮኔል ሜሲ ከፍተኛ ትችት አስተናገደ !

የአለም ሻምፒዮኑ የሰባት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በክለቡ ፒኤስጂ ደጋፊዎች ከፍተኛ ትችትን ማስተናገዱ ተገልጿል።

ተጫዋቹ ወደ ሳውዲ አረቢያ ማቅናቱ የክለቡ ደጋፊዎችን ያስቆጣ ሲሆን በአሁን ሰዓት ከክለቡ ስታዲየም አቅራቢያ አፃያፊ ስድቦችን በተጫዋቹ ላይ እያሰሙ ይገኛሉ።

ደጋፊዎቹ ካሳሙት የተቃውሞ መልዕክቶች መካከል " ሊዮኔል ሜሲን ልናባርረው ይገባል ከእሱም በተጨማሪ ናስር አል ካላይፊ ክለቡን መልቀቅ አለበት " ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe