TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
“ ማሸነፍ ይገባን ነበር “ ሚኬል አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በምሽቱ ጨዋታ ማሸነፍ ይገባው እንደነበር ገልፀዋል።

“ በጨዋታው የተሻልነው ቡድን እኛ ነበርን “ ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ጨዋታውን ማሸነፍ ይገባን ነበር “ ብለዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም “ በተጨዋቾቹ ኮርቻለሁ “ ሲሉ በጨዋታው ባሳዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በጨዋታው ስለነበረው ዳኝነት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አያይዘው ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•iMac (M1 Chip)

2022 Year
24’ Retina Display
512 GB Storage
8GB RAM

290,000 birr

0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የቼልሲ እና ኒውካስል ጨዋታ

1ኛ @Danielkumsa
2ኛ @Abiiti
3ኛ @iku_chelsea

የማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስትሀም ጨዋታ

1ኛ @TURE1221
2ኛ LKT
3ኛ @Abelabera12

የአርሰናል እና ሊቨርፑል ጨዋታ

1ኛ CH
2ኛ @Dkt_1992
3ኛ Mesay tsige

የኢንተር ሚላን እና ጁቬንቱስ

1ኛ @Zbiuv
2ኛ @Liverpool7y
3ኛ @Abish5

🔴 አሸናፊዎች @Kidusyoftahe ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ ሽልማታቸውን መውሰድ ይችላሉ።

@tikvahethsport
“ አርቴታ ወደ ሞሪንሆ መንገድ ተቀይሯል “ ካራገር

የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጄሚ ካራገር አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በትላንቱ ጨዋታ የአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን የአጨዋወት መንገድ መምረጣቸውን ተናግሯል።

“ አርቴታ የአሰልጣኝነት ህይወቱን ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር እንደመጀመሩ የእሱን መንገድ ይከተላል ብለን ገምተን ነበር “ ያለው ጄሚ ካራገር “ ነገርግን ትላንት ወደ ጆዜ ሞሪንሆ ቀይሮታል “ ብሏል።

በጎደሎ ተጨዋቾች ይሄንን ቢያደርግ እንረዳዋለን ነገርግን በሜዳው በሚያደርገው ጨዋታ ላይ አይደለም ሲል ጄሚ ካራገር ተናግሯል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
ተጠባቂው የባሎን ዶር ሽልማት ዛሬ ይካሄዳል !

በፍራንስ ፉትቦል ጋዜጣ እየተዘጋጀ ለስልሳ ስምንተኛ ጊዜ የሚካሄደው ተጠባቂው የ2024 የባሎን ዶር ሽልማት ስነ ስርዓት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።

የሽልማት ስነስርአቱ ዛሬ ምሽት በፈረንሳይ ርዕሰ መዲና ፓሪስ " Théâtre du Châtelet " አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።

የዘንድሮው የ2024 የባሎን ዶር ሽልማት ያለፈውን የውድድር ዘመን ብቻ ያከተተ መሆኑ ተነግሯል።

በስነስርዓቱ የሚጠበቁ ሽልማቶች ምን ይመስላሉ ?

- የወንዶች ባሎን ዶር አሸናፊ

- የሴቶች ባሎን ዶር አሸናፊ

- የኮፓ ትሮፊ ( ከ 21ዓመት በታች )

- ያሲን ትሮፊ ( የግብ ጠባቂ )

- ገርድ ሙለር አዋርድ ( የአመቱ ምርጥ አጥቂ )

- የአመቱ ምርጥ ክለብ

እነማን ያሸንፋሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በዌስትሀም ጨዋታ ምርጥ እግርኳስ ተጫውተናል “ ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው በምሽቱ የዌስትሀም ጨዋታ ምርጥ እግርኳስ ተጫውቶ እንደነበር ገልፀዋል።

“ በመጀመሪያ ደቂቃዎች ቡድናችንን ማየት በጣም አስደሳች ነበር “ ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ ቡድኑ በርካታ የግብ እድሎች መፍጠሩን እና ጥሩ መጫወቱን ተናግረዋል።

የቡድኑ መሰረታዊ ችግር ግብ በማስቆጠር ጨዋታውን መግደል አለመቻሉ መሆኑን አሰልጣኙ አያይዘው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ የገንዘብ ቅጣት ይጣልበታል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በውድድር አመቱ በሶስት ጨዋታዎች ከስድስት በላይ ቢጫ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተገልጿል።

ቼልሲ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ በአንድ የውድድር ዘመን በሶስት ጨዋታዎች ላይ ከስድስት በላይ ቢጫ ካርድ ያስመዘገበ የመጀመሪያው ክለብ ሆነዋል።

በዚህም ምክንያት በኤፍኤው የ 75,000 ፓውንድ ገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ዴይሊ ሜል ዘግቧል።

ሰማያዊዎቹ

- በበርንማውዝ ጨዋታ ዘጠኝ ቢጫ ካርድ

- በኖቲንግሀም ጨዋታ ስድስት ቢጫ ካርድ

- በኒውካስል ጨዋታ ሰባት ቢጫ ካርዶችን ተመልክተዋል።

ቼልሲ በውድድር ዘመኑ በዘጠኝ ጨዋታዎች ሰላሳ ስድስት የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ተመልክተዋል።

@tikvahethsport        @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ አትሌት እጩዎች ይፋ ሆኑ !

የአለም አትሌቲክስ የ 2024 ከስታዲየም ውጪ በተደረገ የሩጫ ውድድር ዘርፍ የአመቱ ምርጥ አትሌት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በወንዶች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ታምራት ቶላ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ በምርጥ አምስት በእጩዎች ውስጥ መካተት ችለዋል።

አትሌት ታምራት ቶላ በአመቱ ውስጥ የኦሎምፒክ ሪከርድ በማሻሻል የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ማሸነፉ ይታወሳል።

አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በበኩሉ በአመቱ የአለም ግማሽ ማራቶን ሪከርድ በማሻሻል ማሸነፍ ችሏል።

በሴቶች አትሌት ሱቱሜ አሰፋ እና አትሌት ትግስት ከተማ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ናቸው።

አትሌት ሱቱሜ አሰፋ የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊ ስትሆን በ 2024 ምርጥ ሁለተኛ የማራቶን ሰዓት ማስመዝገብም ችላለች።

አትሌት ትግስት ከተማ በበኩሏ የበርሊን እና ዱባይ ማራቶንን በበላይነት ማጠናቀቅ የቻለች አትሌት ነች።

ተመልካቾች የአመቱ ምርጥ አትሌቶችን በአለም አትሌቲክስ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እየገቡ ድምፅ መስጠት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሙሉ የእጩዎች ዝርዝር ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በይፋ ተሰናበቱ !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ከሀላፊነት ማሰናበታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምትክ ሩድ ቫን ኔስትሮይን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት መሾማቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን በሀላፊነት እየመሩ በሊጉ ደካማ ጉዞ በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በይፋ ተሰናበቱ ! ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ከሀላፊነት ማሰናበታቸውን በይፋ አስታውቀዋል። ማንችስተር ዩናይትድ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምትክ ሩድ ቫን ኔስትሮይን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት መሾማቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን በሀላፊነት እየመሩ በሊጉ ደካማ ጉዞ በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። @tikvahethsport    …
ቴንሀግ የመጀመሪያ ተሰናባች አሰልጣኝ ሆነዋል !

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከማንችስተር ዩናይትድ ሀላፊነት መሰናበታቸውን በክለቡ ዛሬ ጠዋት እንደተነገራቸው ተገልጿል።

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በዘንድሮው የውድድር አመቱ የፕርሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ተሰናባች አሰልጣኝ ሆነዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ አዲስ አሰልጣኝ በቋሚነት እስከሚቀጥር ሩድ ቫን ኔስትሮይ ከሌሎች አባላት ጋር ቡድኑን እንዲመራ እንደተጠየቀ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ ወዲህ ለዝውውር 650 ሚልዮን ዩሮ ማውጣታቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ በክለቡ ቆይታቸው የኤፌ ካፕ እና ሊግ ካፕ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል።

አሰልጣኙ ቡድኑን በመሩባቸው አመታት

- በ 2022/23 #ሶስተኛ

- በ 2023/24 #ስምንተኛ ( በክለቡ ታሪክ አስከፊ ደረጃ ) ደረጃዎችን ይዘው አጠናቀዋል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች በኋላ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በይፋ ተሰናበቱ ! ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ከሀላፊነት ማሰናበታቸውን በይፋ አስታውቀዋል። ማንችስተር ዩናይትድ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምትክ ሩድ ቫን ኔስትሮይን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት መሾማቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን በሀላፊነት እየመሩ በሊጉ ደካማ ጉዞ በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። @tikvahethsport    …
“ ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ “ ብሩኖ ፈርናንዴዝ

የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የስንብት መልዕክቱን አስተላልፏል።

“ ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ “ ሲል መልዕክቱን ያስተላለፈው ፈርናንዴዝ የተጋራናቸውን ጊዜያት አደንቃለሁ መልካሙን እመኝልሃለሁ ሲል ተናግሯል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ አክሎም ቡድኑ በጥሩ ሁኔታ ላይ ባይገኝም የክለቡ ደጋፊዎች ኤሪክ ቴንሀግ ለክለቡ የሰሯቸውን ጥሩ ነገሮች እንዲያቆዩ ጠይቋል።

የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ስንብት ያወቁት ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ሲያደርገው መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንቶኒዮ ሩዲገር ጉዳት አላጋጠመውም !

ጀርመናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አንቶኒዮ ሩዲገር በተደረገለት ምርመራ ጉዳት እንዳላጋጠመው መረጋገጡ ተገልጿል።

አንቶኒዮ ሩዲገር ሪያል ማድሪድ ከባርሴሎና ባደረጉት ጨዋታ የጉዳት ስሜት እንዳለው ተገልጾ ነበር።

ተጨዋቹ በቀጣይ ሎስ ብላንኮዎቹ ከቫሌንሽያ ጋር በሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ መሰለፉ በሚኖረው ስሜት ላይ የተመረኮዘ እንደሚሆን ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የባርሴሎናው ዋና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ የስፔን ላሊጋ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን መመረጥ ችለዋል።

አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በወሩ ባርሴሎናን እየመሩ ያደረጓቸውን ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፍ ሊጉን በመምራት ላይ ናቸው።

አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ የላሊጋ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው መመረጥ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
#Wanaw_Premium

በመላው አለም ያላቹ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላቹ! የዋናውን ማሊያዎች በኤክስፖርት እስታንዳርድ በ2199 ብር ብቻ ከእኛ ዘንድ የምታገኙ ይሆናል።

👉🏾 በብዛት ስታዙ ደግሞ የተለያዩ ስጦታዎች የሚኖራችሁ ይሆናል፡፡ 👈🏾

🌍 Made in Africa 🌍

Contact us!
📞 8289


Instagram | Facebook | TikTok  | X  | Youtube

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የባሎን ዶር ሽልማት ማን ሊያሸንፍ ይችላል ?

ሪያል ማድሪድ ተጨዋቾቹ የዘንድሮውን የባሎን ዶር ሽልማት አያሸንፉም የሚል እምነት እንዳለው ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ቪንሰስ ጁኒየር ወይም ዳኒ ካርቫል ሽልማቱን እንደማያሸንፉ ማወቃቸውን የክለቡን ታማኝ የመረጃ ምንጭ ጠቅሶ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ይህንንም ተከትሎ ሪያል ማድሪድ በዛሬ ምሽቱ የባሎን ዶር ሽልማት ስነ ስርዓት ላይታደሙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሽልማቱን ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ሮድሪ ያሸንፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪያል ማድሪዶች መናገራቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport        @kidusyoftahe
“ አሰልጣኝ ስራውን ሲያጣ ያሳዝናል “  ቶማስ ፍራንክ

የብሬንትፎርዱ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ከማንችስተር ዩናይትድ የተሰናበቱት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ አሰልጣኝ መሆናቸውን ገልፀዋል።

“ አሰልጣኝ ስራውን ሲያጣ ያሳዝናል “ ያሉት ቶማስ ፍራንክ ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ አሰልጣኝ ነው ጥሩ የአሰልጣኝነት ህይወት አለው በማለት ተናግረዋል።

ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ ስራ መስራቱን ያነሱት ቶማስ ፍራንክ " ሁለት ዋንጫ አሸንፏል ያለውን ሁሉ እንደሰጠ እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

ስማቸው ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ስለመያያዙ የተጠየቁት አሰልጣኙ " እዚህ ሀላፊነት አለኝ የሚፈጠረው አይታወቅም ነገርግን እዚህ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
  🆕አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል 🍏 ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📣 https://t.iss.one/sellphone2777

📞 0929008292

✉️ inbox @bina27

📌 አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
የባሎን ዶር አሸናፊዎች ደረጃ ይፋ ተደረገ !

በአሁን ሰአት ይፋ እየተደረገ በሚገኘው የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች ሽልማት ከሰላሳ የመጨረሻ ተጫዋቾች እጩ ውስጥ አሸናፊዎች ደረጃቸው በመታወቅ ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት :-

29ኛ - ማትስ ሁሜልስ

29ኛ - አርቴም ዱቭቢክ

28ኛ - አሌሀንድሮ ግሪማልዶ

27ኛ - ቪቲንሀ

26ኛ - ዴክላን ራይስ

@tikvahethsport         @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባሎቴሊ የህክምና ምርመራውን ያደርጋል ! ጣልያናዊው የፊት መስመር አጥቂ ማሪዮ ባሎቴሊ በድጋሜ ወደ ጣልያን ሴርያ ውድድር ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል። ማሪዮ ባሎቴሊ የጣልያን ሴርያውን ክለብ ጂኖኣ ለአንድ የውድድር አመት ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱን የጣልያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ተጨዋቹ በሚቀጥሉት ሰዓታት የህክምና ምርመራውን በማጠናቀቅ ጂኖኣን በይፋ እንደሚቀላቀል ይጠበቃል። ማሪዮ ባሎቴሊ…
ባሎቴሊ በይፋ ጂኖኣን ተቀላቀለ !

ጣልያናዊው የፊት መስመር አጥቂ ማሪዮ ባሎቴሊ የጣልያን ሴርያውን ክለብ ጂኖኣ በይፋ ተቀላቅሏል።

የ 34ዓመቱ የፊት መስመር አጥቂ ማሪዮ ባሎቴሊ የሴርያውን ክለብ ጂኖኣ ለአንድ የውድድር አመት መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ማሪዮ ባሎቴሊ ባለፈው አመት ካሳለፈበት የቱርኩ ክለብ ዴሚርስፖር ጋር ከተለያየ ወዲህ ያለ ክለብ ይገኝ ነበር።

ማሪዮ ባሎቴሊ በጂኖኣ በአመት 500,000 ዩሮ እንደሚያገኝ የጣልያን መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የባሎን ዶር አሸናፊዎች ደረጃ ይፋ ተደረገ ! በአሁን ሰአት ይፋ እየተደረገ በሚገኘው የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች ሽልማት ከሰላሳ የመጨረሻ ተጫዋቾች እጩ ውስጥ አሸናፊዎች ደረጃቸው በመታወቅ ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት :- 29ኛ - ማትስ ሁሜልስ 29ኛ - አርቴም ዱቭቢክ 28ኛ - አሌሀንድሮ ግሪማልዶ 27ኛ - ቪቲንሀ 26ኛ - ዴክላን ራይስ @tikvahethsport         @kidusyoftahe
#Update

በአሁን ሰአት ይፋ እየተደረገ በሚገኘው የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች ሽልማት ስነስርዓት ከሰላሳ የመጨረሻ ተጫዋቾች እጩ ውስጥ አሸናፊዎች ደረጃቸው በመታወቅ ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት :-

25ኛ - ኮል ፓልመር

24ኛ - ዊሊያም ሳሊባ

23ኛ - ሩበን ዲያስ

22ኛ - አንቶኒዮ ሩዲገር

21ኛ - ቡካዩ ሳካ

@tikvahethsport               @kidusyoftahe