TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#Paris2024           #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍፃሜ እና ማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የወንዶች 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ እንዲሁም የወንዶች 5000ሜ እና የሴቶች 1500ሜ "repêchage" ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- ቀን 6:10 :- 5000ሜ ወንዶች ማጣሪያ (ሀጎስ ገብረህይወት ፣ ቢኒያም መሀሪ እና አዲሱ ይሁኔ)

- ቀን 7:45 :- 1500ሜ ሴቶች "repêchage"
ማጣሪያ ( አትሌት ብርቄ ሀየሎም )

- ምሽት 4:40 :- 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ፍፃሜ ( አትሌት ለሜቻ ግርማ ፣ ጌትነት ዋሌ እና ሳሙኤል ፍሬው )

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 5000ሜ ወንዶች ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ምድብ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት ለፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።

አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት የማጣሪያ ውድድሩን 14:08:18 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ጀረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።

በሁለተኛው ምድብ አትሌት ቢኒያም መሀሪ እና አዲሱ ይሁኔ ኢትዮጵያን በመወከል የማጣሪያ ውድድራቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

የ 5,000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:00 ሰዓት ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 5000ሜ ወንዶች ማጣሪያ ውድድር በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ቢኒያም መሀሪ እና አዲሱ ይሁኔ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጧል።

አትሌት ቢኒያም መሀሪ የማጣሪያ ውድድሩን 13:51:82 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን እንዲሁም አዲሱ ይሁኔ  የማጣሪያ ውድድሩን 13:52:62 በሆነ ሰዓት በመግባት #ስምንተኛ  ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

የ 5000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:00 ሰዓት የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
#TeamEthiopia

አትሌት ብርቄ ሀየሎም የማጣርያ ውድድሯን ዳግም አድርጋ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለግማሽ ፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

አትሌት ብርቄ ሀየሎም በአዲሱ የ “ repechage “ህግ መሰረት ውድድሯን ዳግም አድርጋ ነው ማለፍ የቻለችው።

የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ነገ ከምሽቱ 2፡45 ጀምሮ ይደረጋል።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና ድርቤ ወልተጂ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፉ ሌሎች አትሌቶቻችን ናቸው።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

የ 3000 ሜትር መሰናክል ሪከርድ ባለቤቱ አትሌት ለሜቻ ግርማ ከደቂቃዎች በፊት ባጋጠመው የመውደቅ አደጋ ከባድ ሁኔታ እንደነበር ዘገባዎች ያመላክታሉ።

አትሌት ለሜቻ ግርማ ከወደቀ በኋላ ጭንቅላቱን እንደመታው ከስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ከወደቀ በኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የህክምና እርዳታ ተደርግለት በፍጥነት ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በአንደኛው ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ብርቄ ሀየሎም ለፍፃሜ ሳታልፍ ቀርታለች።

አትሌት ብርቄ ሀየሎም የግማሽ ፍፃሜ ውድድሩን #አስረኛ  ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

በመቀጠል በሁለተኛው ምድብ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ ውድድራቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:25 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በሁለተኛው ምድብ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

አትሌት ድርቤ ወልተጂ የማጣሪያ ውድድሩን  3:55:10  በሆነ ሰዓት ውድድሩን #አንደኛ ደረጃን እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋዬ የማጣሪያ ውድድሩን  3:56:41 በሆነ ሰዓት #አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:25 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

ሊጠናቀቅ የቀናት እድሜ በቀሩት የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ሁለት የብር ሜዳሊያ ብቻ አግኝታ 6️⃣7️⃣ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ እስከ አሁን በሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ መግባት የቻሉ ሀገራት 8️⃣0️⃣ ብቻ ናቸው።

የአትሌቲክስ ቡድናችን በበሪሁ አረጋዊ እና ፅጌ ድጉማ ብቻ ሜዳሊያ ውስጥ መግባት ችሏል።

ቀሪ የፍፃሜ ውድድሮች ምን ይመስላሉ ?

- ሴት እና ወንድ ማራቶን

- 5000ሜትር ወንድ

- 1500ሜትር ሴቶች የሚቀሩ የፍፃሜ ውድድሮች ናቸው።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#TeamEthiopia🇪🇹

ለ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው ታምራት ቶላ ሜዳሊያውን ተረክቧል።

ኢትዮጵያ በወቅታዊ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንድ ወርቅ እና ሁለት ብር 4️⃣4️⃣ኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

ዛሬ በፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገራችን የምትሳተፍበት የመጨረሻ የፍፃሜ ውድድር ይደረጋል።

ከታምራት ቶላ የማራቶን የወርቅ ድል መልስ ከደቂቃዎች በኋላ ከጠዋቱ 3:00 ላይ የሴቶች የማራቶን ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ ፦

🇪🇹በአለም ሪከርድ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ
🇪🇹በአትሌት አማኔ በሬሶ
🇪🇹በአትሌት መገርቱ አለሙ የምትወከል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን " ቀይ ቀበሮዎቹ " በዛሬው ዕለት የመጨረሻ ልምምዳቸውን ሰርተዋል።

ታንዛኒያ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ በ "KMC" ስታዲየም ከ 2:30 እስከ 3:30 ልምምዱን መስራት ችሏል።

በልምምድ ወቅት ሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች በመልካም ጤንነት መሆናቸውን ለመመልከት ተችሏል።

ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ነገ ከዩጋንዳ ጋር በ አዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም ምሽት 12:00 ሰዓት የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከቡሩንዲ አቻው ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ሶስተኛ ጨዋታ ተሸንፏል።

የቡሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን 3ለ2 ሲያሸንፍ የኢትዮጵያን ግብ አንተነህ ተፈራ እና ሚኪያስ ፀጋዬ አስቆጥረዋል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የምድብ ሶስት ጨዋታዎችን መሸነፉን ተከትሎ ከውድድሩ ውጪ ለመሆን ተገዷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe