TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
አል ናስር ድል አድርጓል !

በሳውዲ አረቢያ ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር ከአል ታኢ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው አንድ ግብ በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር የአል ናስርን የመጀመሪያ ግብ ላስቆጠረው ታሊስካ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 አርባ ሶስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

- አል ናስር በሊጉ አስራ ስምንት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሰባት የሉጉ ጨዋታዎች #አስር ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ የሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃን በመምራት ላይ ይገኛል።

- ሮናልዶ አጠቃላይ በሊጉ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአስራ አምስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ሲችል ይህም በሊጉ ከፍተኛው ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንድርያ ፒርሎ ከሀላፊነት ሊነሳ ይችላል !

በቅርቡ የጣልያን ሴሪ ቢውን ክለብ ሳምፕዶሪያ በሀላፊነት የተረከበው የቀድሞ የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ አሰልጣኝ እና ተጨዋች አንድርያ ፒርሎ ከሀላፊነት ሊነሳ እንደሚችል ተገልጿል።

በሳምፕዶሪያ አሰልጣኝነት ቆይታው ያልተሳካ የውድድር ጅማሮ በማድረግ ላይ የሚገኘው አንድርያ ፒርሎ ቡድኑ ነገ በሚያደርገው ጨዋታ ሽንፈት የሚያስተናግድ ከሆነ ሊሰናበት እንደሚችል ተነግሯል።

ሳምፕዶሪያ በፒርሎ ስር ያለው ቁጥር ምን ይመስላል ?

- በሜዳው ያደረጋቸውን ተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ተሸንፏል።

- ከሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ጨዋታ ብቻ ነው።

- አስራ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል #ስድስት ግቦች ሲያስቆጥር #አስር ግቦች ተቆጥረውበታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ናስር ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል !

በእስያ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከታጅኪስታኑ ክለብ ኢስቲክሎል ጋር ጨዋታውን ያደረገው የሳውዲው ክለብ አል ናስር 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ታሊስካ ( 2x ) የአል ናስርን ሶስት ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የእስያ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ ያስቆጠረችውን ግቦች ወደ ስምንት መት ሀምሳ አምስት ከፍ ማድረግ ችሏል።

አል ናስር በሁሉም ውድድሮች ያደረጋቸውን ያለፉት - #አስር ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችሏል።

ያደረጋቸውን ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ያሸነፈው አል ናስር ምድቡን በስድስት ነጥብ ሲመራ በቀጣይ ከኳታሩ ክለብ አል ዱሀይል ጋር ይጫወታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቻል ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመቻልን ብቸኛ ግብ ያሬድ ከበደ በጨዋታው መገባደጃ ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

መቻል በውድድር አመቱ የሰበሰባቸውን ነጥቦች #አስር በማድረስ ደረጃውን ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ችለዋል።

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ኢትዮጵያ መድን ከመቻል

- ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የካፍ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የ2023 የውድድር ዘመን የአፍሪካ ( ካፍ ) የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሰላሳ እጩ ተጨዋቾች ይፋ ተደርገዋል። በእጩዎች ውስጥ እነማን ተካተዋል ? ሞሀመድ ሳላህ ፣ ቪክቶር ኦሲሜን ፣ ሳዲዮ ማኔ ፣ ሞሀመድ ኩዱስ ፣ ሪያድ ማህሬዝ ፣ ሴኮ ፎፋና ፣ አሽራፍ ሀኪሚ ፣ ቶማስ ፓርቴ ፣ ሀኪም ዚየች እና ሶፍያን አምራባት በእጩ ውስጥ ተካተዋል። የእጩዎች ሙሉ ዝርዝር…
የካፍ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

የ2023 የውድድር ዘመን የአፍሪካ ( ካፍ ) የአመቱ ምርጥ ተጨዋች የመጨረሻ #አስር እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት ሞሀመድ ሳላህ ፣ ቪክቶር ኦሲሜን ፣ ሳዲዮ ማኔ ፣ ሪያድ ማህሬዝ ፣ አሽራፍ ሀኪሚ ፣ ሶፍያን አምራባት ፣ ቪንሰንት አቡበከር ፣ ፍራንክ አንጉይሳ ፣ ያሲን ቦኑ እና ዮሱፍ ኢን ነስሪ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

የአፍሪካ የ2023 የአመቱ ምርጥ ሽልማት ስነስርዓት ታህሳስ 1/2016 ዓ.ም በሞሮኮዋ ማራከች ከተማ የሚካሄድ ይሆናል።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤቨርተን የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ተጣለበት !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ከፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጋር በተያያዘ በሰራው የህግ ጥሰት #አስር ነጥቦች እንዲቀነሱበት በፕርሚየር ሊጉ ገለልተኛ ኮሚሽን ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

ይህንንም ተከትሎ ኤቨርተን ከአስር ነጥብ ቅነሳ ቅጣቱ በኋላ አሁን ካለበት አስራ አራተኛ ደረጃ ወደ አስራ ዘጠነኛ ደረጃ ዝቅ ለማለት የሚገደድ ይሆናል።

ኤቨርተን በበኩሉ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ የተላለፈበት የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ውሳኔ ፍትሀዊ ነው ብሎ #እንደማያምን እና ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች በሜዳው አንፊልድ ስታዲየም ያደረጋቸውን #አስር ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሚመሩት ሊቨርፑሎች በአስር ጨዋታዎች ሰላሳ አንድ ግቦችን በተጋጣሚያቸው መረብ ላይ ሲያሳርፉ በአንፃሩ አራት ግቦች ብቻ ተቆጥረውባቸዋል።

ሊቨርፑል ነገ ቀን 11:00 ከፉልሀም ጋር በአንፊልድ ስታዲየም የሊግ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮማ ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን ቀጥሏል !

በቅርቡ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን በማሰናበት አሰልጣኝ ዳንኤል ዴ ሮሲን በሀላፊነት የሾመው የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ ባለፉት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

ሮማ በአሰልጣኝ ዳንኤል ዴ ሮሲ እየተመራ በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው #አስር ጨዋታዎች ስምንቱን ሲያሸንፍ በአንዱ ተሸንፈው በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

ሮማ ባለፉት አስር ጨዋታዎች ሀያ ስድስት ግቦችን በተጋጣሚያቸው መረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል።

ሮማ በሊጉ አርባ ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለመረከብ ተቃረበ ! የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በሚቀጥሉት ቀናት ባየር ሙኒክን በሀላፊነት ለመረከብ ሙሉ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባየር ሙኒክ አሁን ላይ በአሰልጣኙ የውል ካሳ ክፍያ ዙሪያ ከበርንሌይ ጋር…
ባየር ሙኒክ ለበርንሌይ ስንት አቀረበ ?

የቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ወደ ክለባቸው ለመውሰድ ለስምምነት እንደተቃረቡ መገለፁ ይታወቃል።

ከበርንሌይ ጋር በአሰልጣኙ ካሳ ክፍያ ዙሪያ ንግግር ላይ የሚገኙት ባየር ሙኒኮች #አስር ሚልዮን ዩሮ ማቅረባቸው ተገልጿል።

በርንሌይ በበኩላቸው የቀረበውን ሒሳብ ለመቀበል አለመፈለጋቸው እና #ሀያ ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንዲፈፀምላቸው እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርቴታ ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኝ ሊሆኑ ይችላሉ !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚቀጥለው የውድድር አመት ከመጀመሩ አስቀድሞ በአርሰናል ቤት ያላቸውን ውል ለተጨማሪ አመታት ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በክለቡ የአንድ አመት ውል ያላቸው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአዲሱ የኮንትራት የአርሰናል የምንግዜም ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተነግሯል።

አሰልጣኙ በአመት #አስር ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ የደሞዝ ክፍያ ሊቀርብላቸው ይችላል የተባለ ሲሆን ይህም ከፕርሚየር ሊጉ ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኞች አንዱ ያደርጋቸዋል።

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በአመት 20 ሚልዮን ፓውንድ በሆነ ክፍያ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኝ ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe